MAP

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ ከጠፈር ተመራማሪው ቡዝ አልድሪን ጋር በስልክ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ ከጠፈር ተመራማሪው ቡዝ አልድሪን ጋር በስልክ ውይይት ባደረጉበት ወቅት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከጠፈር ተመራማሪው ቡዝ አልድሪን ጋር መነጋገራቸው ተገለጸ

አፖሎ 11 ታሪካዊ በሆነው ወቅት በጨረቃ ላይ ካረፈች ከ56 ዓመታት በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የጠፈር ተመራማሪው አቶ በዝ አልድሪን ጋር ስለ ታሪካዊ ስኬት መነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን በእለቱ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ዳይሬክተር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እስከ ማክሰኞ ድረስ በካስቴል ጋንዶልፎ እንደሚቆዩና በዚያው ዕለት ማምሻውን ወደ ቫቲካን እንደሚመለሱ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

አፖሎ 11 ጨረቃ ላይ ካረፈች ከ56 ዓመታት በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እሁድ ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ የጠፈር ተመራማሪው በዝ አልድሪን ጋር መነጋገራቸውን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ በቴሌግራም ዘግቧል።

ናሳ አፖሎ 11ን በጨረቃ ላይ የማሳረፍ የመጀመሪያ ተልእኮውን እ.አ.አ በሐምሌ 16 ቀን 1969 ዓ.ም አስጀመረ። እ.አ.አ በሐምሌ 20/1969 ዓ.ም ኒል አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ የተራመደ የመጀመሪያው ሰው ሆነ፣ ከእዚያም በመቀጠል ቡዝ አልድሪን በጠፈር ላይ የተራመደ ሁለተኛው ሰው ሆነ።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የፕሬስ ቢሮው አክሎ እንደገለጸው “የሰው ልጅ ጥበብ የሚመሰክረውን ታሪካዊ ስኬት ትዝታ ለቅዱስነታቸው አካፍሏል፣ እናም በመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 8 ውስጥ የተጠቀሱትን ቃላት ተጠቅመው ስለ ፍጥረት ምስጢር፣ ታላቅነት እና ደካማነት አንፀባርቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በስልክ የነበራቸውን ቆይታ ከማብቃታቸው በፊት የጠፈር ተመራማሪውን፣ ቤተሰቡን እና ተባባሪዎቹን ባርከዋል።

ከውይይቱ በኋላ ቡዝ አልድሪን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል፣ "እኔ እና አንካ ከቅዱስነታቸው ሊቀ ጳጳስ ሊዮ አሥራ አራተኛ ጋር አፖሎ 11 ጨረቃ ላይ ያረፈችበትን 56ኛ ዓመት በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት  ከብፁዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከፍተኛውን ቡራኬ በማግኘታችን በጣም እናመሰግናለን፣ ይህ ቡራኬ ልባችንን ነክቶታል" ሲሉ በመልእክታቸው መግለጻቸው ተዘግቧል።

እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓ.ም የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ ያረፈበትን 56ኛውን አመት ምክንያት በማድረግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሐምሌ 13/2017 ዓ.ም በቀትር የመልአከ እግዚአብሕእር ሰላምታ ጸሎት ካደረጉ በኋላ ፣ በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የቫቲካን የጠፍር ምርምር ተቋም ጉልላት ውስጥ የሚገኙትን ቴሌስኮፖች እና መሳሪያዎችን ጎብኝተዋል።

በእለቱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ዳይሬክተር ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ማትዮ ብሩኒ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመጀመሪያ እንደታሰበው እሁድ ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም ወደ ቫቲካን ከመመለስ ይልቅ እስከ ማክሰኞ ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም በካስቴል ጋንዶልፎ እንደሚቆዩ እና ምሽት ላይ ወደ ቫቲካን እንደሚመለሱ አስታውቀዋል።

21 Jul 2025, 14:44