MAP

ር.ሊ.ጳ ሊዮ "የተጠራነው እንጀራችንን እንድናካፍል፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድናውጅ ነው"!

በቅዱስ ዮሐንስ ላተራን የሮማ ካቴድራል ባሲሊካ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የክርስቶስ ክቡር ሥጋ እና ክቡር ደም የተከበረበትን ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ሥረዓት መርተዋል፣ በመቀጠልም ወደ ቅድስት ማርያም ሜጀር ባሲልካ የተካሄደውን ሁደት መርተዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የተጠራነው እንጀራችንን እንድናካፍል፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድናውጅ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለክርስቶስ ክቡር ሥጋ እና ክቡር ደም (ለኮርፐስ ክሪስቲ) እሁድ ባደረጉት ስብከት፣ በወንጌል ውስጥ፣ ኢየሱስ ያስተማራቸውና ሕሙማኖቻቸውን የፈወሳቸው ሰዎች ለማየት ስለተሰበሰቡት ሰዎች፣ የጌታን መከራና ርኅራኄ በማሳየት፣ “ሊያድነን ወደ ዓለማችን የሚመጣው የእግዚአብሔር ፍቅራዊ መቀራረብ” እንደሚያንጸባርቅ እንዴት እንደተሰማን አስታውሰዋል። እና "እግዚአብሔር በሚነግስበት ቦታ ከክፉ ነገር ሁሉ ነፃ ወጥተናል" ሲሉ ገልጿል። እናም በችግራችን ጊዜ፣ በረሃብ፣ በህመም ወይም በምድራዊው የህይወታችን ፍጻሜ፣ “ኢየሱስ በመካከላችን ይኖራል” የሚለውን ማስታወስ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

"ጌታ ባለበት ለሕይወታችን ጥንካሬ እና ትርጉም ለመስጠት የሚያስፈልገንን ሁሉ እናገኛለን" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኢየሱስ የተገኘውን በማካፈል እንጀራውንና ዓሦቹን እንዴት እንዳበዛና ሁሉም ሰው በአሥራ ሁለት መሶብ የተረፈውን ረሃቡን እንዲያረካ አስችሎታል ብለዋል።

“ኢየሱስ የሕዝቡን ረሃብ የሚያረካው በዚህ መንገድ ነው፤ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ያደርጋል፤ እኛንም እንዲሁ እንድናደርግ ያስተምረናል" ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ “ከራሳቸው ርሃብ ይልቅ በሌሎች ስግብግብነት” እየተሰቃዩ ያሉትን መላውን ሕዝቦች ማስታወስ ጠቃሚ ነው ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በጥቂቶች ከተሰበሰበው ሀብት ሊመጣ የሚችለውን ድህነት የመካፈል መንፈስ ጋር ፍጹም ተቃርኖ የምናይ ሲሆን ይህም “ስቃይና ኢፍትሐዊነትን የሚያመጣ የትዕቢት ግድየለሽነት” ምልክት ነው ብለዋል።

“በተለይ በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት፣ የጌታ ምሳሌ ተግባራችንን እና አገልግሎታችንን ሊመራን የሚገባው መለኪያ ነው፡ የተጠራነው እንጀራችንን እንድንካፍል፣ ተስፋን እንድናበዛ እና የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት እንድናውጅ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቀጠል ኢየሱስ ሁሉንም ሰው ከሞት የሚያድነው የሕይወት እንጀራ መሆኑን፣ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ የምናከብረው የእምነት ምሥጢር መሆኑን አስታውሰዋል። " ረሃብ በዚህ ህይወት ውስጥ የሚገኝ ፍላጎታችን ምልክት እንደሆነ ሁሉ እንጀራ መቁረስም የእግዚአብሔር የድነት ስጦታ ምልክት ነው" ብለዋል።

"ወዳጆች ሆይ፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ርሃብ የእግዚአብሔር መልስ ነው፣ ምክንያቱም አካሉ የዘላለም ሕይወት እንጀራ ነውና፤ ይህን ተቀብላችሁ ከእርሱ ብሉ!... ሕያውና እውነተኛውን ኅብስት የሆነውን ኢየሱስን ስንበላ ለእርሱ እንኖራለን። ራሱን ሙሉ በሙሉ በማቅረብ የተሰቀለውና ከሙታን የተነሣው ጌታ ራሱን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል፣ እኛም ከእግዚአብሔር እንድንካፈል እንደተፈጠርን እንገነዘባለን ብለዋል።

ከክርስቶስ ጋር ህብረት

"እግዚአብሔር በሚሰጠን መብል እየበረታን ኢየሱስን ወደ ሁሉም ልብ እናምጣው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ እያንዳንዳችን በማዕድ እንድንቀመጥ በመጥራት ሁሉንም ሰው በማዳን ስራው ውስጥ ያሳትፋል።የተጠሩ ብፁዓን ናቸው የዚህ ፍቅር ምስክሮች ናቸውና!"

23 Jun 2025, 12:10