ር.ሊ.ጳ ሊዮ አብያተ ክርስቲያናት በስቃይ ውስጥ ወንጌል መስብከ ይቀጥላሉ አሉ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የምስራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት የእርዳታ ኤጀንሲዎች (ROACO) ዓመታዊ ስብሰባውን በሮም ሲያካሂዱ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ሐሙስ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም በቫቲካን ከተሳታፊዎች ጋር ተገናኝተዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ለምስራቅ ካቶሊካዊት አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት አወድሰው የድርጅቱን ተልእኮ “የደስታ አዋጅ” ብለውታል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጦርነትና “በጥላቻ ደመና” ውድመት ደርሶባቸዋል ያሉትን “በምሥራቅ አከባቢዎች የሚገኙ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት የተስፋ ዘርን በመዝራት” የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና በጎ አድራጊዎቻቸውን አመስግነዋል።
"ለብዙ ሰዎች፣ ድሆች ነገር ግን በእምነት ባለ ጠጎች፣ እናንተ በጨለማው የጥላቻ ጥላ መካከል የምታበሩ ብርሃን ናችሁ" ብሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካቶሊክ ማህበረሰብ ውስጥ እንኳን ጭቆና እና አለመግባባቶች በታሪክ እንደሚከሰቱ ጠቁመዋል፣ ይህም አንዳንድ ጊዜ የምስራቃውያን ክርስቲያናዊ ባህሎችን ዋጋ ማድነቅ አለመቻል ንፉግነት ነው ብለዋል።
የምስራቃዊው ስርዓት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ በደንብ እንዲታወቅ ያላቸውን ፍላጎት የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጉባኤዎች፣ ሴሚናሮች በካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲካሄዱ ያላቸውን ፍላጎት ጠቁመዋል፣ የላቲን አምልኮ ካቶሊኮች ስለ ምስራቃዊ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለማሳወቅ ይህ ተግባር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
“እንዲሁም የሐዋርያዊ እንክብካቤ ሥራን መጋፈጥና መካፈል ያስፈልጋል” ሲሉ ተናግሯል፣ “የምሥራቃዊ ካቶሊኮች ዛሬ የሩቅ የአጎት ልጆች ሆነው የማያውቁትን ሥርዓት የሚያከብሩ፣ ነገር ግን በግዳጅ ስደት ምክንያት የጎረቤቶቻችን ጎረቤቶች የሆኑት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ናቸው" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ክርስቲያኖችን "የቅዱስ ስሜት፣ ጥልቅ እምነታቸው በመከራ የተረጋገጠው፣ እና መንፈሳዊነታቸው፣ መለኮታዊ ምስጢራትን የሚደግፉ" በማለት አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቀጠል በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ግጭት አንዳንድ የROACO አባላት ለዓመታዊው ስብሰባ ወደ ሮም መምጣት እንዳልቻሉ በመግለጽ በምሥራቅ አከባቢዎች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለውን ዓመፅ “ከዚህ በፊት ባልታወቀ ሁኔታ” አስታውሰዋል።
"ስለ ዩክሬን ስናስብ ልባችን ይደማል፣ በጋዛ ውስጥ ስላለው አሰቃቂ እና ኢሰብአዊ ሁኔታ እና በመካከለኛው ምስራቅ በጦርነት መስፋፋት አደጋ ይታያል" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለውም እያንዳንዱ ግለሰብ የነዚህን ግጭቶች መንስኤዎች በመመርመር ለመፍታት መፈለግ አለባቸው፣ ነገር ግን አጭበርባሪ ወይም ሐሰት የሆኑ ማብራሪያዎችን ውድቅ ያደርጋሉ።
"የራስን ጥቅም ማሳደድን ሕጋዊ ለማድረግ ሲባል 'ይስተካክል ይሆናል' የሚለው መርህ ዛሬ በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ሲሰፍን ማየት በእውነት በጣም ያሳዝናል" ብሏል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጦርነት እና በሽብር ምክንያት ለደረሰው ሞት እና ስቃይ አዝነው በቅርቡ በሶሪያ ደማስቆ በማር ኤልያስ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ በዋቢነት ጠቅሰዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ እንዳሉት የሰው ልጅ በጦርነት ድርጊቶች ላይ ተመስርቶ ለወደፊቱ ጠንካራ መሠረት ለመጣል ተስፋ ማድረግ አይችልም ብለዋል።
በትብብር እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፋዊ ራዕይ ብቻ ነው ሰላም ሊያስገኝ የሚችለው ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ ዘላቂ ሰላም መምጣት የሚቻለው በዚሁ መንገድ ብቻ ነው ብለዋል።
"ሰዎች በሞት ነጋዴዎች ኪስ ውስጥ የሚገባውን የገንዘብ መጠን መገንዘብ ጀምረዋል" ብለዋል። "አዳዲስ ሆስፒታሎችን እና ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚውል ገንዘብ አሁን ያሉትን ለማጥፋት እየዋለ ነው!" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዩ በመጨረሻ የምስራቃዊ አብያተ ክርስቲያናትን ምስክርነት አመስግነዋል፣ ጥሪያችን “እራሳችንን በስልጣን መዳፍ ውስጥ እንዳንወድቅ በመጠንቀቅ ለኢየሱስ ታማኝ ሆነን እንድንኖር ነው” ብለዋል።
"ልቦችን ከጥላቻ ነፃ ያወጣውን ክርስቶስን እንከተል እና ከመከፋፈል እና ከበቀል አስተሳሰብ እንዴት መላቀቅ እንደምንችል በአርአያአችን እናሳይ" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።