MAP

2025.06.26 Partecipanti all'Incontro per Sacerdoti promosso dal Dicastero per il Clero

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለካህናቱ፡- እዚህ ማንም ብቻውን አይደለም ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከካህናት ጋር በተካሄደው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ለተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት የወንድማማችነት ክህነት የሕነጻ ትምህርት እና ሕይወት አስፈላጊነትን በማሳሰብ ካህናት ብቻቸውን እንዳልሆኑ አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከሰኔ 17 እስከ 20 የሚካሄደው የካህናት ኢዮቤልዩ አካል በሆነው ስብሰባ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ “ደስተኛ ካህናት—ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ” በሚል ርዕስ በሮም በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከካህናት፣ ከሴሚናርስቶች እና የሴሚናሪ አለቆች ጋር ተገናኝተው እንደ ነበረ ተገልጿል።

የወንድማማችነት ልምድ

ወደ 1,700 የሚጠጉ ተሰብሳቢዎች በአዳራሹ ውስጥ ተሰብስበው የነበረ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር ከብፁዕ ካርዲናል ላዛሮ ዩ ሄንግ-ሲክ በቅድስት መንበር የካህናትን ጉዳይ የሚመለከተው የቫቲካን ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ ንግግር አድርገዋል።

ይህ ስብሰባ “ከኮንፈረንስ ወይም ከሕነጻ ትምህርት ክፍለ ጊዜ” የበለጠ መሆኑን ካርዲናሉ በወቅቱ ተናግረዋል። ይልቁንም “ከሁሉም በላይ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን፣ የሲኖዶስ እና የወንድማማችነት ልምድ” ነበር ሲሉ አጥብቆ ተናግሯል።

ካርዲናል ላዛሮ ግቡ ወደ ክህነት ሕይወት ልብ መመለስ ነው ሲሉ አሳስበዋል። ከኢየሱስ ጋር ጓደኛ መሆን ማለት ነው። ደስተኛ ቄስ መሆን መፈክር ሳይሆን “እውነተኛ፣ ተጨባጭ አጋጣሚ፣ ከቀን ወደ ቀን የሚኖር ነገር ነው” በማለት አብራርተዋል።

በክህነት ውስጥ ሦስት ግንዛቤዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለተሳታፊ ካህናት ባስተላለፉት መልእክት የካርዲናሉን ቃል አስተጋብተዋል። ኢየሱስ “ወዳጆች ብያችኋለሁ” ያለው ጥሩ አባባል እንደ ሆነ ጎላ አድርጎ ገልጿል። ይልቁንም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ “የክህነትን አገልግሎት ለመረዳት እውነተኛ ቁልፍ” መሆናቸውን ተጋርተዋል።

ይህን በማሰላሰል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስለ ክህነት ሦስት የሕነጻ ትምህርት ጊንዛቤዎችን አቅርበዋል። የመጀመሪያው ሕነጻ የግንኙነት መንገድ ሲሆን ይህ ማለት “በችሎታ ብቻ ሳይሆን ግንኙነት መፈጠር” ማለት ነው ብለዋል።

ስለዚህ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሕነጻ ትምህርት በቀላሉ እውቀትን በማግኘት ላይ ብቻ እንዲያተኩር ሳይሆን ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በቅርበት በማደግ ላይ እንዲያተኩር አስጠንቅቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የተጋሩት ሁለተኛው ግንዛቤ ወንድማማችነት የክህነት ሕይወት ወሳኝ አካል እንደሆነ ነው። ካህናትና ሴሚናርስቶች ወንድማማች ሆነው እንዲኖሩ እንጂ ተቀናቃኝ ወይም የተገለሉ እንዳይሆኑ አበረታቷቸዋል።

“በመካከላችን እውነተኛ እና ቅን ወንድማማችነት ከሌለ እኛ አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን ንቁ ማኅበረሰቦችን እንዴት መገንባት እንችላለን?” በሚለው ጥያቄ ይህ ግንዛቤ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አበክሮ ገልጿል።

በሦስተኛ ደረጃ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የካህናትን የሕነጻ ትምህርት ማለት በአንድነት ለመዋደድ፣ ለመስማት፣ ለመጸለይ እና ለማገልገል የሚችሉ ሰዎችን መፍጠር ማለት እንደሆነ ተናግረዋል። ለዚህም "የሕነጻ ትምህርት የሚሰጡ ሰዎችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን" ብለዋል።

የካህናት የሕነጻ ትምህርት በማኅበረሰብ ውስጥ እንጂ በተናጥል ሊካሄድ እንደማይችል ራሱ ሴሚኔሪው ትልቅ ማስታወሻ ነው ብለዋል።

አትፍሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስለ መንፈሳዊ ጥሪዎች እና “በካህናት ሕይወት እና ተልዕኮ ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ የችግር ምልክቶች” ሲናገሩ ወንዶች ወደ ክህነት መጠራታቸውን እና ተልእኳቸውን በታማኝነት ለመወጣት እንደሚጥሩ አጉልተው ገልጸዋል።

ወጣቶች መንፈሳዊ ጥሪ እንዲሰማቸው የሚያነሳሱ ሁሉንም ካህናት “ደፋር እና ነፃ አውጪ ሀሳቦችን ለማቅረብ እንዳይፈሩ” አበረታቷቸዋል።

ይህ ዓለም አቀፋዊ ስብሰባ የተካሄደው በኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱስ ልብ ክብረ በዓል ዋዜማ ሲሆን ጳጳሱም አጋጣሚውን ተጠቅመው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ጳጳሳዊ መልእክት በላቲን ቋንቋ  "ዲሌክሲት ኖስን" (እርሱ ወደደን) አስታውሰዋል፣ ይህም እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር መፈጠሩን ለማስታወስ ነው።

“አንድ ሰው በእውነት ሲያምን፣ የአገልጋዩ ደስታ ከክርስቶስ ጋር ያለውን ግንኙነት ያሳያል” ምክንያቱም ካህናት የተልእኮውን ጉጉት እንደገና እንዲያውቁ አሳስቧቸዋል።

አንድ ካህን ስብሰባው ከመዘጋቱ በፊት ሊቀ ጳጳሱን እንዲያቅፉት ጠየቁት። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ይህ አንድ ማቀፍ ለሁሉም እንደሚሆን ለሕዝቡ ተናግሯል ። በመቀጠልም ስለ ካህኑ መንፈሳዊ ሕይወት አስፈላጊነት ከንግግራቸው የተላለፈውን መልእክት ደግመዋል።

“እዚህ ብቻውን ማንም የለም” ሲሉ ተናግሯል፣ ምክንያቱም አንድ ካህን “ጥሩ አጃቢ፣ መንፈሳዊ ዳይሬክተር፣ ጥሩ አናዛዥ” የሚፈልግበት ብዙ ጊዜ ይኖራል። ይህ ደግሞ ወንድማማችነትን በሕነጻ ትምህርት እና በክህነት ሕይወት ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት በድጋሚ አጽንኦት ሰጥቷል።

በጣም ርቀው በሚገኙ እና ርቀው በሚገኙ የተልእኮ መስኮች ውስጥ እንኳን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማንም መቼም ቢሆን ብቻውን አይደለም ያሉ ሲሆን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ብዙ ጊዜ የሚጠሩትን “መቀራረብ” እንዲኖሩ አዘጋጆቹን፣ ካህናትን እና ሴሚናርስቶችን አበረታቷቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንደተናገሩት፣ “ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ጸጋ እና በእኔ ቅርበት ላይ ተማመኑ፣ እናም አብረን በእውነት ይህ ድምጽ በዓለም ውስጥ መሆን እንችላለን ካሉ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

27 Jun 2025, 14:14