MAP

MAP Leo XIV� Angelus prayer in Vatican MAP Leo XIV� Angelus prayer in Vatican  (ANSA)

ር.ሊ.ጳ በባንጉዊ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰው አደጋ ሰለባዎች ጸሎት ማድረጋቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በሚገኘው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በተከሰተው ግጭት ለተጎዱት ሁሉ ያላቸውን ቅርበት በመግለጽ ለተጎጂዎች ጸሎታቸውን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም ዓለምን ለሚያሰቃዩት ጦርነቶች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካደርጉ በኋላ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ያደረጉትን አስተንትኖ ካገባደዱ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት “በባንጉዊ ለሚገኘው የባርቴሌሚ ቦጋንዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ በተማሪዎች ላይ ለደረሰው አሰቃቂ አደጋ እና ሞት አዝኛለሁ” ብለዋል።

"ጌታ ቤተሰቦችን እና መላውን ማህበረሰቡን ያጽናና" ሲሉ ጸሎት አድርሰዋል።  

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ባንጊ በሚገኘው ትምህርት ቤት ውስጥ በተፈጠረ ግጭት በትንሹ 29 ተማሪዎች ሲሞቱ ከ260 በላይ ቆስለዋል።

በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰው ፍንዳታ የአመቱን የመጨረሻ ፈተና በመውሰድ ላይ የነበሩ ከ5,000 በላይ ተማሪዎች ላይ ነበር አደጋው የተከሰተው። አብዛኞቹ ተጎጂዎች በቦታው ህይወታቸው አልፏል። ከ260 ያላነሱ ሰዎች ቆስለው በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ድርጊቱ የተከሰተው ባለፈው ሳምንት እሮብ እለት በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር በመበላሸቱ የተነሳ መሆኑ ተገልጿል።

'መሳሪያ ዝም ይበል'

ቅዱስ አባታችን የመልአከ ሰላም ጸሎት ካደረጉ በኋላ ያደርጉትን ንግግራቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት ሃሳባቸውን በጦርነት እየተሰቃዩ ወደሚገኙ በርካታ የአለም ህዝቦች በማዞር ለተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲደረግ ተማጽነዋል።

"ወንድሞች እና እህቶች የጦር መሳርያ ትጥቅ በየቦታው ዝም እንዲል እና ሰላም በውይይት እንዲቀጥል ጸሎታችንን ማድረግ እንቀጥል" ብለዋል።

 

30 Jun 2025, 14:09