MAP

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታ ጋር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታ ጋር   (@VATICAN MEDIA)

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንትን በሐዋርያዊ መንበራቸው ተቀብለው አነጋገሩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታን ዓርብ ግንቦት 29/2017 ዓ. ም. በቫቲካን በሚገኘው ሐዋርያዊ መንበራቸው ተቀብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የምክር ቤቱ ፕሬዝደንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታ በመቀጠል፥ ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር ያካሄዱት ስብሰባ ዋና ሃሳብ፥ ረሃብን ከዓለም ማስወገድ፣ የድሃ አገራት ልማትን ለማስተዋወቅ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዕርዳታ ተቋም ማቋቋም እና እንዲሁም በዩክሬን እና በጋዛ የሚካሄዱ ጦርንርቶችን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ያካተተ እንደ ነበር ታውቋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ጋር በጽሕፈት ቤታቸው
ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ጋር በጽሕፈት ቤታቸው   (ANSA)

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታ ከዚህ ስብሰባ በኋላ፥ በቅድስት መንበር ከመንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ሚሮስሎው ዋቻስኪ ጋርም ተገናኝተዋል።

በቅድስት መንበር እና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው መልካም የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በጋራ ጉዳዮች ላይ በተለይም ረሃብን ከዓለም ማስወገድ እና የድሃ አገራትን ልማት ለማስፋፋት ዓለም አቀፍ ፈንድ ለማቋቋም የቀረበውን ሃሳብ በተመለከተ በቅድስት መንበር እና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ላለው መልካም የሁለትዮሽ ግንኙነት ዕውቅና ተሰጥቶታል። ውይይቱ በተለይ በዩክሬን እና በጋዛ ያለውን ጦርነት በመጥቀስ ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ አውድ የተመለከተ እንደሆነ ታውቋል።

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት አቶ አንቶኒዮ ኮስታ በኤክስ ገጻቸው ባሠፈሩት ጽሑፍ እንደገለጹት፥ የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት ቅድስት መንበር ጠቃሚ አጋር መሆኗን አፅንዖት ሰጥተዋል።

 

07 Jun 2025, 15:04