MAP

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ለብሔራዊ የጣሊያን-አሜሪካን ፋውንዴሽን አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ለብሔራዊ የጣሊያን-አሜሪካን ፋውንዴሽን አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።  (@Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ “የካቶሊክ እምነት ወደ አሜሪካ ለተሰደዱት ብዙ ጣሊያኖች መለያቸው ነበር”

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ረቡዕ ግንቦት 27/2017 ዓ. ም. ጠዋት በቫቲካን የሚገኝ ብሔራዊ የጣሊያን-አሜሪካን ፋውንዴሽን አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል። “የካቶሊክ እምነት ከጣሊያን ወደ አሜሪካ ለተሰደዱት ብዙ ሰዎች ዋና መለያቸው ነው” ብለው ይህም በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ እንደረዳቸው አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“የካቶሊክ እምነት ከጣሊያን ወደ አሜሪካ ለተሰደዱት በርካታ ጣሊያኖች ዋና መለያ ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ የረዳቸው እና በአዲሱ አገራቸው የብልጽግና ተስፋን ይዘው ስለመጡ ነበር” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በዚህ ትዝታ ውስጥ ሆነው፥ የፋውንዴሽኑን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ረቡዕ ግንቦት 27/2017 ዓ. ም. ጠዋት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያቀረቡትን ሳምንታዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለተከታተሉ የፋውንዴሽኑ አባላት አቀባበል በማድረግ፥ ለፋውንዴሽኑ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሰላምታ አቅርበው ጥረታቸውንም አድንቀዋል።

እምነታቸው ደግፏቸዋል

“እንደምታውቁት ምንም እንኳን ቅድመ አያቶቻቸው ከትውልዶች በፊት ወደ አሜሪካ ቢገቡም በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ስለ ጣሊያን ቅርሳቸው በኩራት ይናገራሉ” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እነዚህ ስደተኞች ወጣት ልጆቻቸውን ስለ ጣሊያን ባሕል እና ታሪክ ማስተማራቸውን እና እንዲሁም በሁለቱም ሀገራት መካከል የነጻ ትምህርት ዕድልን እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ድጋፎችን በማድረጋቸው አመስግነዋል። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ ተጠቃሚነት እና ተጨባጭ ትስስር እንዲኖር ይረዳል ብለዋል።

የጣሊያን ስደተኞች በካቶሊክ እምነት ውስጥ ሆነው በአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የሚለማመዷቸው መንፈሳዊ በዓላት እና የአምልኮ ሥነ-ሥርዓቶች የከበሩ ናቸው” ብለው፥ በአዲሱ አገራቸው ለመበልጸግ ተስፋን ይዘው የመጡ በመሆናቸው በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ እጅግ የረዳቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ብሔራዊ የጣሊያን-አሜሪካን ፋውንዴሽን አባላትን በቫቲካን ሲቀበሉ
ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ብሔራዊ የጣሊያን-አሜሪካን ፋውንዴሽን አባላትን በቫቲካን ሲቀበሉ   (@Vatican Media)

ውርስን ማክብር

የቡድኑ የቫቲካን ጉብኝት በኢዮቤልዩ የተስፋ ዓመት ወቅት መካሄዱን የተመለከቱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የሮምን መንፈሳዊ ሃብት እንዲቀስሙ በመጋበዝ፥ “የሐዋርያው ​​ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ መቃብር እንዲሁም በአስቸጋሪ የታሪክ ዘመናት ቤተ ክርስቲያንን ያጸኑ ብዙ ቅዱሳን የኖሩበት ነው” ብለዋል።

“ብዙ ፈተናዎች በከበቡት ዘመን ይህ ጉብኝታችሁ የተስፋ ስሜታችሁን እንዲያድስ” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከመስጠታቸው በፊት፥ “ከእናንተ በፊት ከነበሩት አባቶች የወረሳችኋቸው መንፈሳዊ እና ባሕላዊ ቅርሶችን እያንዳንዳችሁ ከቤተሰቦቻቸሁ ጋር ሁል ጊዜ እንድትመለከቷቸው እጸልያለሁ” በማለት አጽናንተዋል።

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ብሔራዊ የጣሊያን-አሜሪካን ፋውንዴሽን አባላትን በቫቲካን ሲቀበሉ
ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ብሔራዊ የጣሊያን-አሜሪካን ፋውንዴሽን አባላትን በቫቲካን ሲቀበሉ   (@Vatican Media)

 

04 Jun 2025, 16:57