MAP

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ ከረዴምቶሪስ እና ከካላብሪዚ ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ ከረዴምቶሪስ እና ከካላብሪዚ ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ለኤጲስ ቆጶሳት፡- ለጌታ መንጋ መልካም ሥራ መሥራታችሁን ቀጥሉ ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ችግሮች ቢኖሩትም ለረዴምቶሪስ እና ለካላብሪዚ ማሕበር አባላት ጳጳሳት ራሳቸውን በመሠዋት የእግዚአብሔርን መንጋ ለማገልገል ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የጌታ ሥራ ሁል ጊዜ እንደሚቀድመን በማስታወስ አእምሯችንን በልግስና እና ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ ተስማምተን ለመላው የክርስቶስ መንጋ እንስራ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከረዴምቶሪስ እና ከካላብዚ ማሕበር አባላት ጳጳሳት ጋር ሐሙስ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ይህንን ተናግረዋል።

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ንግግራቸውን የጀመሩት ሁለት ሃይማኖታዊ ጉባኤያትን በማሰባሰብ በጳጳሳት መካከል ውይይት በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የሐሳብ ልውውጡ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ባስተማረው መሠረት፣ የተገኙትን ጳጳሳት፣ ማኅበረሰቦቻችሁንና መላውን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያበለጽግ ልምድ ነው ብለዋል።

ጉልህ መስዋዕቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “ቤተክርስቲያኗ ከአባሎቻችሁ ጳጳሳት በመሾም ከፍተኛ መስዋዕትነት ለከፈሉት ተቋማቶቻችሁ ምስጋና አቀርባለሁ፣ በተለይም መንፈሳዊ ጥሪዎች እየቀነሱ በመጡበት በአሁኑ ወቅት ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ “በተለያዩ በቅድስት መንበር ጽ/ቤቶች ውስጥ የተሰማሩ አባላት መከልከል  “ትንንሽ ችግሮች መታየታቸው አይቀርም” ብለዋል ።

"በተመሳሳይ ጊዜ ግን ቤተክርስቲያኗ ለጉባኤዎቻችሁ ታላቅ ስጦታ አድርጋለች፣ ምክንያቱም የእናንተ መስራቾች በእርግጠኝነት እንደሚናገሩት ለአለም አቀፋዊው ቤተክርስትያን አገልግሎት ለማንኛውም ሃይማኖታዊ ቤተሰብ ታላቅ ጸጋ እና ደስታ ነው" ብለዋል።

ጠቃሚ ባህሪዎች

በተለይም በኤጲስ ቆጶስ እና ብፁዕን ካርዲናሎች መካከል ለአገልግሎት የመረጡት እና የተቀደሱ ስካላብሪዚ ማሕበር አባላት መሪዎች ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት "ለአገልግሎታቸው የሁለት ጠቃሚ መስህቦችን ውርስ በተለይም በእኛ ጊዜ አስፈላጊ የሆኑትን ለስደተኞች የሚደርገው አገልግሎት እና ለድሆች እና በሩቅ ላሉ ሰዎች ወንጌልን መስበክን" አስታውሰዋል ።

ወደ ረድምቶሪስ ማሕበር መስራች ወደ ቅዱስ አልፎንሰስ ማሪያ ደ ሊጉሪ ሐሳባቸውን ዘወር በማድረግ ቅዱስ አባታችን በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን በኔፕልስ ውስጥ በጣም ችላ በተባሉ ሰፈሮች ውስጥ መከራ ሲያጋጥመው፣ ወንጌልን ወደ ትንሹ የህብረተሰብ ክፍል የማድረስ ተልእኮውን ለመቀበል የተመቻቸ ኑሮ እና ተስፋ ሰጪ ስራን ትቶ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከመቶ አመት በኋላ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ባፕቲስት ስካላብዚ፣ የተናግረውን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስታውሰው፣ በሩቅ አገሮች ለራሳቸው እና ለቤተሰባቸው የተሻለ የወደፊት ዕድል ፍለጋ ሁሉንም ነገር ትተው የብዙዎችን ተስፋ እና መከራ ሰምተው የራሳቸውን ተስፋ ማድረግ ችለዋል ሲሉ ተናግረዋል።

"ሁለቱም መስራቾች ነበሩ፣ ሁለቱም ጳጳስ ሆኑ፣ ሁለቱም በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስርአቶች ተግዳሮቶች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ይህም በተለያዩ ደረጃዎች አዳዲስ ድንበሮችን ሲከፍት" በተጨማሪም "ብዙ ያልተሰሙ መከራዎችን እና ብዙ ያልተፈቱ ችግሮችን ትቶ ማንም ሊፈታው የማይፈልገውን የቸልተኝነት ኪሶች ፈጥሯል" ብለዋል ።

“እኛም” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጽንኦት ሰጥተው ሲናገሩ “በተመሳሳይ ታላቅ እድሎችን እንዲሁም ችግሮችን እና ተቃርኖዎችን በሚያቀርብበት ታሪካዊ ወቅት፣ የተስፋ ኢዮቤልዩ በዓልን ስናከብር፣ ዛሬም እንደትናንቱ ሁሉ፣ ምን ማድረግ እንዳለብን ለመረዳት ማዳመጥ ያለብን ድምፅ በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በልባችን ውስጥ የፈሰሰው ‘የእግዚአብሔር ፍቅር’ ወደ ልባችን የፈሰሰው መሆኑን ነው ብለዋል።

ለአሁኑ ማበረታቻ

ሆኖም፣ ቅዱስ አባታችን አጽንኦት ሰጥተው እንደ ተናገሩት ከሆነ “በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን ውስጥ፣ የጌታ ሥራ ሁል ጊዜ ይቀድመናል፡ በጥበብ ማስተዋል አእምሮአችንን እና ልባችንን እንድናስማማ ተጠርተናል፣ እናም እናንተ ያስተዋወቃችሁት ውይይት በዚህ ረገድ ጠቃሚ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።

“ስለዚህ፣ እኔ፣” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “እነዚህን የጋራ መደጋገፍ ወንድማማችነት ትስስር እንድትጠብቁ እና እንድታሳድጉ አበረታታችኋለሁ፣ በልግስና እና ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ፣ ለመላው የክርስቶስ መንጋ የሚጠቅም ነው ያሉ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ስላደረጉት ታላቅ ሥራ አመስግነው ለእነርሱና ለመላው ማኅበረሰባቸው ሐዋርያዊ ቡራኬ ከሰጡ በኋላ ውይይቱ አብቅቷል።

 

26 Jun 2025, 15:39