MAP

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ አንድነትን በወንጌል ምስክርነት እና በይቅርታ ለመፍጠር ሞክሩ ማለታቸው ተገለጸ!

በቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ አመታዊ በዓል ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በሰማዕትነት የጋራ ምስክርነት እና በይቅርታ የመለወጥ ኃይል ላይ የተመሠረተውን የክርስቲያናዊ አንድነት ዘላቂ ጥሪ አጉልተው መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት ደግሞ እሁድ ሰኔ 22/2017 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካደረጉ በኋላ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት አስተንትኖ መሆኑ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእለቱ የቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ አመታዊ በዓል ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል፣  በዚህ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምእመናን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካደረጉ በኋላ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት አስተንትኖ ቤተ ክርስቲያንን ጥልቅ በሆነ እና ብዙ ጊዜ በተደበቀ ሕብረት ውስጥ የሚያስተሳስረውን የክርስቲያናዊ አንድነት፣ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እና የሰማዕትነት ምስክርነት ላይ አስተንትኖ አድርገዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስተንትኖዋቸውን የጀመሩት በሐዋርያው ​​ጴጥሮስና ጳውሎስ ምስክርነት እና ደም የተመሰረተውን የሮም ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማስታወስ ነው። በክርስቶስ ላይ ላሳዩት እምነት መከራን ከሚቀበሉ አልፎ ተርፎም በሚሞቱት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች ከሚያቀርቡት ቀጣይነት ያለው መሥዋዕትነት ጋር በማያያዝ ዘላቂ ቅርስ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሥነ መለኮት ስምምነት ብቻ ሳይሆን በአማኞች የጋራ ስቃይ በእምነት ምስክርነት መስመር የተፈጠረውን አንድነት ሲገልጹ “ስለ ደም ክርስቲያናዊ አንድነት መናገር እንችላለን” ብለዋል።

"ይህ የማይታይ ግን ጥልቅ የሆነ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ገና ያልተሟላ እና የማይታይ ህብረት" ነው ሲሉ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም የጳጳስ ተልዕኮ እምብርት ነው “የሮም ቤተ ክርስቲያን፣ በቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በፈሰሰው ደም የሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በፍቅር ለማገልገል ቃል ገብታለች” ሲሉ በድጋሚ አረጋግጧል።

ኢየሱስ እውነተኛው ዓለት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወንጌል እና በቅዱስ ጴጥሮስ መሠረታዊ ሚና ላይ በማሰላሰል ኢየሱስን እንደ እውነተኛ ዓለት ገልጸውታል፣ “ግንበኞች የናቁት ዓለት እግዚአብሔር የማዕዘን ራስ ያደረገው እርሱ ነው" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን የጴጥሮስና የጳውሎስ ባዚሊካ በአሁኑ ጊዜ የክርስትና ማንነት ማዕከል የሆነው ታላቅነት በአንድ ወቅት በኅብረተሰቡ ሕይወት ላይ እንዴት እንደነበረ አመላክተዋል። “ከአጥር ውጪ” በማለት የሮማውያንን ባህላዊ አገላለጽ በመጠቀም ምሥክርነታቸው የጀመረበት ቦታ ነው ሲሉ ተናግሯል፤ ይህም የወንጌል ታላቅነት ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው ዓለም ከንቱ ነው በሚላቸው ቦታዎች ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ክርስቶስን የሚከተሉ በአስቸጋሪ መንገድ ማለትም ክርስቶስ በተራራ ላይ ባስተማረው የብጽዕና መንገድ እንደሚሄዱ ተናግረዋል። የመንፈስ ድህነት፣ የዋህነት እና የፍትህ ጥማት ብዙ ጊዜ ተቃውሞ እንደሚያጋጥማቸው ጠቁመዋል። ሆኖም፣ የእግዚአብሔር ክብር የተገለጠው በዚህ መንገድ ላይ ነው። "የእግዚአብሔር ክብር በወዳጆቹ ላይ ያበራል እና ከመለወጥ ወደ መለወጥ በመሸጋገር በየመንገዱ እየቀረጻቸው ይቀጥላል" ሲሉ ገልጸዋል።

ቅድስና የሚወለደው በይቅርታ ነው።

ቅድስና በይቅርታ እንጂ በፍጽምና ብቻ እንደማይወለድ አስረድተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “አዲስ ኪዳን እንደ ታላላቅ ሐዋርያት የምናከብራቸው ሰዎች ስሕተታቸውን፣ ግጭቶችን እና ኃጢአቶችን አይደብቅም” በማለት የተናገሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ  “ታላቅነታቸው የተቀረጸው በይቅርታ ነው” ብለዋል።

ክርስቶስ ለጴጥሮስ እና ለጳውሎስ ደጋግሞ እንደደረሰ ሁሉ፣ እያንዳንዱን ሰው አንድ ጊዜ ሳይሆን ደጋግሞ መጥራቱን ቀጥሏል፣ "ለዚህ ነው ሁልጊዜ ተስፋ ማድረግ የምንችለው፣ ኢዮቤልዩ ራሱ ለዚህ ማስታወሻ ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማጠቃለያ ላይ ምእመናን ከቤተሰብ እና ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጀምሮ የአንድነት ገንቢዎች እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። "በቤተክርስቲያኗ እና በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው አንድነት በይቅርታ እና በጋራ መተማመን ይገነባል" ብለዋል፣ "ኢየሱስ እኛን ማመን ከቻለ፣ በእርግጠኝነት እርስ በርሳችን በስሙ ልንተማመን እንችላለን" ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

በመጨረሻም ቤተክርስቲያን አሁንም በቁስልና መለያየት ባለበት ዓለም ውስጥ “ቤትና የኅብረት ትምህርት ቤት” እንድትሆን ጥሪ በማቅረብ ለድንግል ማርያም እና ለሐዋርያቱ ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ጸሎት በማቅረብ አስተንትኗቸውን አጠናቀዋል።

 

30 Jun 2025, 14:05

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >