MAP

ር.ሊ.ጳ ከእዚህ አለም ድካም በሞት ከተለዩ በኋላ ምን ይከሰታል? ር.ሊ.ጳ ከእዚህ አለም ድካም በሞት ከተለዩ በኋላ ምን ይከሰታል?   (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ከእዚህ አለም ድካም በሞት ከተለዩ በኋላ ምን ይከሰታል?

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሞት መጨረሻው ስብሰባ እንዲጀመር እና የቅዱስ ጴጥሮስ አዲስ ተተኪ እንዲመረጥ የሚያደርጓቸው ተከታታይ ክስተቶች መጀመሪያ ነው ። ወደ አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ የሚመራውን ክስተቶች በዝርዝር እናቀርባለን።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሞት የእንቅስቃሴ ሰንሰለትን ያበጃል- ከጳጳሱ ሞት እና የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እስከ ስብሰባው መጀመሪያ እና የተተኪው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ድረስ ያሉትን ጊዜያት የሚያመለክቱ ወጎች በተከታታይ የሚከናወኑበት ወቅት ነው።

ነገር ግን በቫቲካን በዚህ "ሴዴ ቫካንቴ" ወይም "ክፍት ቦታ" ወቅት ምን እየተከናወነ ነው?

እ.ኤ.አ. በ 1996 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ በ"ዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሬጂስ" ሐዋርያዊ ሕገጋት ያስተዋወቀው ዋና ለውጦች እ.አ.አ በየካቲት 22/1996 ዓ.ም በጳጳስ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ የታወጀው የጴጥሮስ መንበር ሁኔታ የሚገልጸው ሰነድ ታወጀ፣ የሐዋርያዊ ሕግጋት ሰነድ በላቲን ቋንቋ 'ዩኒቨርሲቲ ዶሚኒሲ ግሬጂስ' በጳጳስ ጳውሎስ ስድስተኛ ሐዋርያዊ ሕገጋት አሁንም በላቲን ቋንቋ "Romano Pontifici Eligendo" (የሮማ ጳጳስ ምርጫ) በተመለከተ የተደነገገውን የጴጥሮስን መንበር በተመለከተ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በሥራ ላይ ያሉትን ደንቦች አሻሽሏል።

ሰነዱ በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡-

-የመጀመሪያው የሐዋርያዊ መንበር ወይም "ሴዴ ቫካንቴ" (ባዶ መንበር) ያስተዳድራል፣ ይህም ማለት የቤተክርስቲያኗ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተዳደር በተቋረጠበት እና በተተኪው ምርጫ መካከል ያለው ጊዜ ነው።

- ሁለተኛው የሮማን ጳጳስ ምርጫን የማዘጋጀት እና የማካሄድ ሂደቶችን ይዘረዝራል።

በመግቢያው ላይ እንደተገለጸው፣ የእነዚህ ደንቦች ማሻሻያ የተነሣሣው “ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የምትኖርበትን የተለወጠውን ሁኔታ በመገንዘብ እና አጠቃላይ የቀኖና ሕግ ክለሳን ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን [...] በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ተነሳሽነቱን ያገኘ ነው።

ሐዋርያዊ ሕገጋቱ የአዲሱን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫን በተመለከተ ቀደም ሲል የነበሩትን ደንቦች በከፊል ያረጋግጣል።

ቁልፍ ነጥቦች፡-

የካርዲናሎች ኮሌጅ (የካርዲናሎች ሕብረት) በትክክለኛ ቀኖናዊ ደንቦች የተደነገገውን የሺህ ዓመት ባህል በመከተል አዲሱን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ የመምረጥ ኃላፊነት ያለው አካል ሆኖ ይቆያል፡- “በእርግጥም፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ሥልጣን በምድር ላይ እንደራሴ ከሆነው ከክርስቶስ በቀጥታ የተገኘ የእምነት ትምህርት ከሆነ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ከፍተኛ ስልጣን ለእርሱ የተሰጠው በህጋዊ ምርጫ፣ በእርሱ ተቀባይነት ያለው፣ ከኤጲስቆጶስ ቅድስና ጋር መሆኑ አያጠራጥርም"።

እ.ኤ.አ. ከየካቲት 21/2025 ዓ.ም ጀምሮ የካርዲናሎች ኮሌጅ 135 ካርዲናሎች መራጮችን አካቷል (የካርዲናሎች ኮሌጅ ማለት (በላቲን ቋንቋ፡ ኮሌጂየም ካርዲናሊዩም)፣ እንዲሁም የብፁዕን ካርዲናሎች ኮሌጅ ተብሎ የሚጠራው፣ የሁሉም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካርዲናሎች አካል ነው)፣ (ዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሪጂስ የ120 ካርዲናል መራጮችን ገደብ አቋቋመ) ከነዚህም 108ቱ በነፍስዬር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ  የተሾሙ እና 117 መራጮች ያልሆኑ ካርዲናሎች ስብስብ ይገኝበታል።

"ሴዴ ቫካንቴ" (ክፍት የሥራ ቦታ) ምርጫ በሚጀምርበት ቀን 80 ዓመት የሞላቸው ካርዲናሎች እጩ ሆነው አይካተቱም። ነገር ግን ከ80 አመት በላይ የሚሆኑ ካርዲናሎች አሁንም በመሰናዶ ስብሰባዎች ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ (ከምርጫው በፊት ያሉት አጠቃላይ ጉባኤዎች) ላይ ማለት ነው።

ምርጫው የካርዲናሎች ኮሌጅ አባላትን ብቻ ያቀፈ ነው፡-

“በእነሱ ውስጥ ፣ በሚያስደንቅ ውህደት ፣ የሮማን ጳጳስ ምስል እና ሹመት የሚያሳዩት ሁለት ገጽታዎች ተገልጸዋል፡- የሮም -- ምክንያቱም እሱ በሮም የሚገኘው የቤተክርስቲያን ኤጲስቆጶስ ተብሎ ስለሚታወቅ እና ስለሆነም ከዚች ከተማ ቀሳውስት ጋር የጠበቀ ዝምድና ስላለው፣ በሮማ ቄሳውስት እና ዲያቆናታዊ ማዕረጎች ካርዲናሎች የተወከለው እና ከካርዲናሎች እና ጳጳሳት ጋር ተጠርተዋል ። መላውን መንጋ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የግጦሽ መስክ የሚመራውን የማይታየውን እረኛን ይወክላል፣ በተጨማሪም የቤተክርስቲያኗ ዓለም አቀፋዊነት፣ በካርዲናሎች ኮሌጅ ስብጥር ውስጥ በሚገባ ተወክሏል፣ ይህም አባላትን ከሁሉም አህጉር ይሰበስባል።

ምስጢራዊ ምርጫ "ጥንታዊው ተቋም" የአዲሱ ጳጳስ ምርጫ መቼት እንደሆነ ተረጋግጧል። ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አስፈላጊ መዋቅሩን አረጋግጠው ሁሉም የምርጫ ሂደቶች በሐዋርያዊ ሕግጋት መሰረት በሲስቲን የጸሎት ቤት ውስጥ ብቻ እንዲከናወኑ አዟል።

"ጥንቃቄ የተሞላው ታሪካዊ ምርመራ ይህ ተቋም በተከሰተባቸው ሁኔታዎች ምክንያት ወቅታዊውን ተገቢነት ብቻ ሳይሆን ለምርጫው ሥርዓት፣ ፈጣን እና ትክክለኛ ምርጫ በተለይም በውጥረት እና በግርግር ጊዜ የሚሰጠውን የማያቋርጥ ጠቀሜታ ያረጋግጣል። በትክክል በዚህ ምክንያት በእያንዳንዱ ዕድሜ ላይ ያሉ የነገረ መለኮት ሊቃውንት እና የቀኖና ሊቃውንት ግምገማ እያወኩ፣ ይህንን የሮማውያን ተቋም በባሕርይው መሠረት ምርጫው ትክክለኛ መሆኑን በአንድ ድምፅ ዘላቂነት አረጋግጣለሁ”።

የድርጊቱን የተቀደሰ ባህሪ እና የድርጊቱን ተገቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአምልኮ ተግባራት ከህጋዊ ሥነ-ሥርዓቶች ጋር በሚጣጣሙበት እና መራጮች የመንፈስ ቅዱስን ውስጣዊ እንቅስቃሴዎች ለመቀበል ነፍሳቸውን በተሻለ ሁኔታ ለማዘጋጀት በሚችሉበት ቦታ ላይ መደረጉን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምርጫው በእያንዳንዱ ቀን በእግዚአብሔር ፊት ማን እንደሚቆም ግንዛቤን ለማጎልበት በሲስቲን የጸሎት ቤት ውስጥ መካሄዱን እንዲቀጥል አዝዣለሁ" (ገጽ 9 UDG)።

እንደበፊቱ ሁሉ የሮማን ጳጳስ ምርጫን ከውጫዊ ተጽእኖዎች መጠበቅ እና ብቁ እና አስቀድሞ የተወሰነ የምርጫ አካል መስጠት አስፈላጊነቱ ይታወቃል።

በተጨማሪም የምስጢራዊ ምርጫ ሂደቶች ነፃነታቸውን ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱን ካርዲናል መራጭ ነፃነታቸውን ለማረጋገጥ ፣ያልተገባ የማወቅ ጉጉት እና ተገቢ ካልሆኑ ጫናዎች ለመጠበቅ ያለመ ነው።

ዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሪጂስ ሕጋግት ሦስት ዋና ለውጦች ቀርበዋል፡-

1. በምርጫው ጊዜ በሙሉ የካርዲናል መራጮች መኖሪያ ቤቶች እና የምርጫውን ትክክለኛ አካሄድ ለማረጋገጥ የተሳተፉት በቫቲካን ግዛት በሚገኘው በቅድስት ማርታ ሕንጻ ውስጥ ውስጥ ይገኛሉ (ገጽ 42 UDG)። እንደዚህ ቀደም ካርዲናሎች በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በሙሉ ከሲስቲን የጸሎት ቤት እንዲወጡ አይፈቀድላቸውም።

2. ካርዲናል መራጮች ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ድምጻቸውን መስጠት የሚችሉት በሚስጢር በሚሰጥ ድምጽ (ገጽ 9 UDG) ነው። ይህ በቀደሙት ደንቦች ለምርጫ በአድናቆት ወይም በተመስጦ በላቲን ቋንቋ (quasi ex inspiratione) የተሰጡ አማራጮችን ይሰርዛል፣ ይህም ሰፊ እና የተለያየ የምርጫ አካልን ሐሳቦች ለማንፀባረቅ ተስማሚ አይደሉም ተብሎ ይታሰባል። ምርጫው በስምምነት (በቅንጅት) ለማድረግ ከዚህ ቀደም ተወስኖ የነበረው ሕግ እንዲሁ ተሰርዟል፣ ምክንያቱም ለመተግበር አስቸጋሪ ስለሆነ እና በመራጮች መካከል የተወሰነ ኃላፊነት የጎደለው ነገር ሊፈጠር ስለሚችል፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የግል ድምጽ መስጠት አይጠበቅባቸውም (ገጽ 9 UDG)። በዚህ የምርጫ ዘዴ፣ በርካታ ዙሮች የድምፅ አሰጣጥ የሚፈለገው አብላጫ ድምጽ ያለው እጩ ካላቀረበ፣ ካርዲናል መራጮች የተለየ አብላጫ መስፈርት በማዘጋጀት በአንድ ድምፅ ስምምነት ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።

3. ለአዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ትክክለኛ ምርጫ የሚያስፈልጉትን ድምፆች በተመለከተ የዩኒቨርሲው ዶሚኒሲ ግሪጂስ አንቀጽ 75 መጀመሪያ ላይ ከ 33 ኛው ወይም 34 ኛ ድምጽ በኋላ መግባባት ላይ ካልተደረሰ ድምጽ መስጠት የሚቻለው በአብላጫ ድምጽ ብቻ ነው ። ነገር ግን ይህ ድንጋጌ እ.አ.አ በሰኔ 11 ቀን 2007 ዓ.ም የተፈረመው "በሞቱ ፕሮፕሪዮ" (ሞቱ ፕሮፕሪዮ በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም (አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ በመሆኑ፣ በእዚህ በተሰጠው መንፈሳዊ ስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የሚጽፋቸው ሰነዶች፣ የሚያደርጋቸው ሹመቶች፣ ውሳኔዎች የተመለከቱ ጉዳዮችን ያመለክታል)   "አሊኩቡስ ሙቴቴቢስ" በኩል በጳጳስ በነዲክቶስ 16ኛ ተሻሽሎ፣ እ.አ.አ ሰኔ 11 ቀን 2007 ዓ.ም የተፈረመ እና በዚያው ዓመት ሰኔ 26 ላይ ተግባራዊ ሆኗል። ይህም ለአዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ትክክለኛ ምርጫ፣ ከተገኙት ካርዲናል መራጮች መካከል ብቁ የሆነ ሁለት ሦስተኛው አብላጫ ድምፅ ሁል ጊዜ እንደሚያስፈልግ የሚገልጽ ባህላዊ ደንብ የመለሰ ውሳኔ ነበር።

ባዶ መንበር

“ሴዴ ቫካንቴ” (በላቲን ቋንቋ Vacant See) የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሊቀ ጳጳሱ የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ማብቂያ እና በተተኪው ምርጫ መካከል ያለውን ጊዜ ነው።

ይህ ጊዜ የሚቆጣጠረው እ.አ.አ በየካቲት 22 ቀን 1996 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በወጣው ሐዋርያዊ ሕግጋት "ዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሪጂስ" ነው።

ባዶ የሆነውን መንበርን "የሚያስተዳድረው" ማነው?

በተደነገገው መሠረት፣ በሐዋርያዊ መንበር ክፍት የሥራ ቦታ ወቅት፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለካርዲናሎች ኮሌጅ በአደራ ተሰጥቷል። ሆኖም ሥልጣናቸው ተራ ወይም አስቸኳይ ጉዳዮችን ብቻ በማስተናገድ እና ለአዲሱ ጳጳስ ምርጫ በመዘጋጀት ላይ ብቻ የተገደበ ነው።

የካርዲናሎች ኮሌጅ የቫቲካን ግዛት መንግሥት በተመለከተ የሊቀ ጳጳሳትን ሲቪል ስልጣኖች ሁሉ ይወሰዳል።

ነገር ግን፣ በህይወት ዘመናቸው የጳጳሱ ልዩ መብት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስልጣን የላቸውም።

በሴዴ ቫካንቴ (ባዶ መንበር) ወቅት የሮማን ኩሪያ ራሶች ምን ይሆናሉ?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሲሞቱ ሁሉም የሮማን ኩሪያ የቅድስት መንበር ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች የቫቲካን መደበኛ ሥራን ለማስቀጠል ከተወሰኑ በስተቀር ሥልጣናቸውን ይለቃሉ።

ተግባራቸውን የሚጠብቁት፡- ብፁዕ ካርዲናል ካመርሌንጎ  (ካሜርሌንጎ የአንድ ማህበረሰብ ንብረት እና ፋይናንስ ጠባቂ እና አስተዳዳሪ ነው፣ በተለይም በሃይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ)  (ካርዲናል ኬቨን ፋሬል)፣ የሐዋርያዊ መንበር ንብረቶችን እና መብቶችን የመቆጣጠር እና የማስተዳደር ተግባር ያላቸው፣ ሐዋርያዊ መንበሩ ክፍት በሆነበት ጊዜ፣ በሮማን ኩሪያ ውስጥ የሚገኙ የፍርድቤቶች ዋና ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ በተለይም በሐዋርያዊ ማረሚያ ቤት ውስጥ፣ በቫቲካን ምህረት እና ጸጋ ላይ ያተኮረ ፍርድ ቤት ዋናው ማረሚያ ቤት (ካርዲናል አንጀሎ ደ ዶናቲስ)፣ የሮማ ሀገረ ስብከት ብፁዕ ካርዲናል ቄሰ (ካርዲናል ባልዳሳሬ ሬይና)፣ የቫቲካን ባዚሊካዎች አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል፣ ሊቀ ካህናት እና የቫቲካን ግዛት ሊቀ ጳጳስ (ካርዲናል ማውሮ ጋምቤቲ) የቅዱስነታቸውን ገንዘብና እርዳታ ለተረጂዎች የሚያከፋፍል ሹም (ካርዲናል ኮንራድ ክራጄቭስኪ)፤ የቫቲካን ግዛት ጽሕፈት ቤት አጠቃላይ ጉዳዮች ምትክ (ሊቀ ጳጳስ ኤድጋር ፔና ፓራ)፣ ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና አለም አቀፍ ድርጆቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቫቲካን ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ (ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር)፣ እና የጳጳሳዊ ሥርዓተ አምልኮ እና የዓላት አከባበር መምህር (ሊቀ ጳጳስ ዲዬጎ ጆቫኒ ራቭሊ)፣ እንዲሁም የቅድስት መንበር የተለያዩ ጽ/ቤቶች ፀሐፊዎች በቦታቸው ይቆያሉ።

በክፍት መንበር ወቅት የካርዲናሎች ኮሌጅ ምን ያደርጋል?

በሴዴ ቫካንቴ ወቅት፣ የካርዲናሎች ኮሌጅ (ከጤና ጋር በተያያዙ ችግሮች ካልሆነ በስተቀር ሁሉም በሮም የሚሰበሰቡት) በሁለት ዓይነት ካርዲናል ጉባኤዎች ይገናኛሉ።

1.    ጠቅላላ ጉባኤዎች፡- እነዚህም መላውን የካርዲናሎች ኮሌጅ (አዲሱን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ ከዕድሜ በላይ የሆኑትን ጨምሮ) ያጠቃልላል። እነዚህ ጠቅላላ ጉባኤዎች የሚካሄዱት በሐዋርያዊ መንበር ጽ/ቤት ሲሆን በኮሌጁ ዲን (ካርዲናል ጆቫኒ ባቲስታ ሬ) የሚመሩ ናቸው። ዲኑ እና ንዑስ ዲኑ መምራት ካልቻሉ፣ በፍተኛ ምርጫ ድምጽ ያገኙ ካርዲናል ቦታውን ይረከባሉ።

2.    ልዩ ጉባኤዎች፡- እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

¨    የቅድስት ሮማ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ካርዲናል ካሜርሌንጎ እና ሦስት ካርዲናሎች ከእያንዳንዱ ትዕዛዝ (ኤጲስ ቆጶሳት፣ ካህናት እና ዲያቆናት) አንዱ ከካርዲናል መራጮች መካከል በዕጣ ይመረጣል።

¨    እነዚህ ሦስቱ ረዳት ካርዲናሎች ለሦስት ቀናት ያገለግላሉ ፣ ከዚያ በኋላ በአዲስ መደበኛ ምርጫ ይተካሉ ይህ ሂደት በምርጫ ወቅት እንኳን ይቀጥላል።

¨    ልዩ ጉባኤው የዕለት ተዕለት ጉዳዮችን የሚያስተናግድ ሲሆን ይበልጥ አሳሳቢ ጉዳዮች ደግሞ ለጠቅላላ ጉባኤው መቅረብ አለባቸው።

በጠቅላላ ጉባኤዎች የተደረጉት በጣም አስቸኳይ ውሳኔዎች የትኞቹ ናቸው?

ጠቅላላ ጉባኤዎች (ከምርጫው ሂደት በፊት የተካሄዱት) በሚከተሉት ቁልፍ ውሳኔዎች (ከጳጳሱ ሞት ጋር የተያያዙ ሂደቶችን ሳይጨምር) ወዲያውኑ መምከር አለባቸው።

¨    ለካርዲናሎች በላቲን ቋንቋ በ "Domus Sanctae Marthae" (የቅድስት ማርታ ቤት) ውስጥ ማረፊያዎችን ማዘጋጀት እና ለምርጫ ሂደቶች የሲስቲን ጸሎት ቤት ማዘጋጀት፣

¨    ሁለት የተከበሩ እና በሥነ ምግባር የታነጹ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን በመመደብ በቤተክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ፈተናዎች እና በብሩህ የአዲሱ ጳጳስ ምርጫ ላይ ሁለት አስተንትኖዎችን ለካርዲናሎች የማቅረብ እና የእነዚህን የአስተንትኖ ቀን መወሰን።

¨    ሐዋርያዊ መልእክቶችን ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ የዋለውን የአሳ አጥማጁ ቀለበት እና የሊድ ማህተም ማስወገድ፣

¨    የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ የሚጀመርበትን ቀን እና ሰዓት ማዘጋጀት።

ምርጫው ከመጀመሩ በፊት ወዲያውኑ ምን ይሆናል?

ከምርጫው በፊት ካርዲናል መራጮች በተገኙበት በላቲን ቋንቋ "Mass Pro Eligendo Papa" (ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመምረጥ የሚከናውን ቅዳሴ) ጋር በቅዱስ ቁርባን አከባበር ይቀርባል። ከሰአት በኋላ፣ ካርዲናል መራጮች አዲሱን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ በምስጢር ድምጽ መስጫ ወደሚከናወንበት ሲስቲን የጸሎት ቤት በተከበረ ሁደት ይሄዳሉ።

በሲስቲን የጽሎት ቤት ውስጥ በተደረገው ሁደት መጨረሻ እያንዳንዱ ካርዲናል መራጭ በዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሬጂስ አንቀጽ 53 ላይ በተደነገገው መሰረት ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ። በዚህ ቃለ መሐላ፣ ከተመረጡ፣ በላቲን ቋንቋ "ሙንስ ፔትሪነምን" (የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር) የአለማቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን መጋቢ ሆነው ተግባራቸውን በታማኝነት ለመፈጸም ቃል ይገባሉ። በተጨማሪም ከሮማን ጳጳስ ምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ፍጹም ምስጢራዊነትን ለመጠበቅ እና በምርጫው ውስጥ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃገብ ሙከራዎችን ከመደገፍ ለመቆጠብ ቃል ይገባሉ።

በዚህ ጊዜ፣ የጳጳሳዊ ሥርዓተ አምልኮ እና የበዓላት አከባበር መምህር ተጨማሪ በላቲን ቋንቋ "ኤክስታራ ኦሜኒስ" (ሁሉም ወደ ውጭ) የሚለውን ያውጃል፣ ይህም ማለት የምስጢራዊው ምርጫ አካል ያልሆኑ ሁሉም ግለሰቦች ከሲስቲን የጸሎት ቤት መውጣት አለባቸው ማለት ነው። ሁለተኛውን አስተንትኖ ለማድረግ የተሰየመው መምህሩ እና ቤተ ክህነት ብቻ ነው የሚቀሩት። ይህ አስተንትኖ በመራጮች ላይ ባለው ከባድ ኃላፊነት ላይ ያተኩራል እናም ለአለም አቀፋዊ ቤተክርስቲያን ጥቅም በንጹህ አላማዎች መተግበር እና እግዚአብሔርን ብቻ በዓይኖቻቸው ፊት በመጠበቅ ላይ ያተኩራል (አንቀጽ 52)።

አስተንትኖ ካበቃ በኋላ ሁለቱም ቤተ ክህነት እና የጳጳሳዊ ሥርዓተ አምልኮ እና የበዓላት አከባበር ሊቀ ጳጳሳት ሥፍራውን ይለቃሉ። ከዚያም ካርዲናል መራጮች በላቲን ቋንቋ "በኦርዶ ሳክሮም ሪቱም ኮንክላቪስ" (የምስጢራዊ ምርጫ አሰጣጥ የቅዱሳት ሥርዓቶች  ቅደም ተከተል) መሰረት ጸሎቶችን ያደርጋሉ እና ካርዲናል ዲኑን ያዳምጣሉ፣ በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ወይም በ"ዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሪጂስ" ውስጥ የተዘረዘሩትን ህጎች እና ሂደቶችን በተመለከተ ማብራርያ ያስፈልግ እንደሆነ ይጠይቃሉ።

ሚስጥራዊነትን ለማረጋገጥ እና የውጭ ጣልቃገብነትን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች

ሁሉም የምርጫ ሂደቶች የሚከናወኑት በቫቲካን ሐዋርያዊ መንበር ጽ/ቤት ውስጥ በሚገኘው በሲስቲን የጸሎት ቤት ውስጥ ብቻ ነው ፣ ይህም ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ይቆያል።

የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሐዋርያዊ ሕገጋት በጉባኤው ወቅት የሚፈጸሙትን ነገሮች እና ከጳጳሱ ምርጫ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከቱ ጉዳዮችን በተመለከተ ፍጹም ምስጢራዊነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ይሰጣል። ሰነዱ ምስጢራዊነትን ለማረጋገጥ እና የውጭ ጣልቃገብነትን ለመከላከል ሁሉንም ጥንቃቄዎች በዝርዝር ይዘረዝራል (አንቀጽ 51-61)።

በምርጫው ሂደት በሙሉ፣ ካርዲናል መራጮች በጣም አስቸኳይ ካልሆነ በስተቀር፣ የስልክ ጥሪዎችን ጨምሮ ደብዳቤዎችን ከመላክ፣ ከመቀበል ወይም ከውይይት መቆጠብ አለባቸው። ምንም ዓይነት መልእክት መላክም ሆነ መቀበል፣ ምንም ዓይነት ተፈጥሮ ያላቸውን ጋዜጦችን ወይም መጽሔቶችን መቀበል፣ የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን ስርጭቶችን መከታተል አይፈቀድላቸውም።

ለምርጫ የሚያስፈልገው የድምፅ ብዛት እና አብላጫ ድምጽ

አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን በትክክል ለመምረጥ፣ ከተገኙት መራጮች ውስጥ ሁለት ሦስተኛው አብላጫው ያስፈልጋል። የመራጮች ጠቅላላ ቁጥር ለሶስት እኩል የማይከፋፈል ከሆነ ተጨማሪ ድምጽ አስፈላጊ ነው (ዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሪጂስ አንቀጽ 62)።

ድምጽ መስጠት የሚጀምረው በመጀመሪያው ቀን ከሰአት በኋላ ከሆነ አንድ ድምጽ መስጫ ብቻ ይሆናል። በቀጣዮቹ ቀናት በጠዋቱ እና ከሰዓት በኋላ ሁለት ምርጫዎች ይካሄዳሉ።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቶች በ "Universi Dominici Gregis" ውስጥ ተዘርዝረዋል፣ መራጮች ጤነኛ ላልሆኑ እና በላቲን ቋንቋ "Domus Sanctae Marthae" (የቅድስት ማርታ ቤት) ከክፍላቸው ድምጽ መስጠት ለሚፈልጉ መራጮች ድንጋጌዎችን ጨምሮ ይገልጻል። ድምጾቹ ከተቆጠሩ በኋላ ሁሉም የድምፅ መስጫዎች ይቃጠላሉ።

የሚፈለገው አብላጫ ካልደረሰ ምን ይሆናል?

መራጮቹ ከሶስት ቀናት ያልተቋረጠ ድምጽ በኋላ በእጩ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ ለጸሎት እስከ አንድ ቀን እረፍት ይፈቀድላቸዋል፣ በመራጮች መካከል ነፃ ውይይት እና በካርዲናል ፕሮቶ-ዲያቆን (ካርዲናል ዶሚኒክ ማምበርቲ) አጭር መንፈሳዊ ምክር እንዲሰጣቸው ተፈቅዶላቸዋል።

ከዚያም ድምጽ መስጠት ይቀጥላል እና ከሰባት ተጨማሪ ድምጽ በኋላ ምርጫ ካልተደረገ ሌላ እረፍት ይደረጋል።

ይህ ሂደት ከሌሎች ሰባት ያልተሳኩ የምርጫዎች በኋላ ይደገማል። በዚህ ጊዜ ካሜሬሌንጎ እንዴት መቀጠል እንዳለበት ከካርዲናሎች ጋር ይመክራል።

የዩኒቨርሲ ዶሚኒሲ ግሪጂስ አንቀፅ 75 የተሻሻለው በሞቱ ፕሮፕሪዮ (በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም (አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ በመሆኑ፣ በእዚህ በተሰጠው መንፈሳዊ ስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የሚጽፋቸው ሰነዶች፣ የሚያደርጋቸው ሹመቶች፣ ውሳኔዎች የተመለከቱ ጉዳዮችን ያመለክታል) በጳጳስ በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም የተሻሻለ ሲሆን ይህም የአዲሱን ጳጳስ ምርጫ ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ ከመራጮች ሁለት ሦስተኛው የሚፈልገውን ባህላዊ ደንብ ወደነበረበት እንዲመለስ ማድረጉ ጠቃሚ ነው። ይህ ደንብ እ.አ.አ በየካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በወጣው በላቲን ቋንቋ "ሞቱ ፕሮፕሪዮ" (ሞቱ ፕሮፕሪዮ በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም (አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ በመሆኑ፣ በእዚህ በተሰጠው መንፈሳዊ ስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የሚጽፋቸው ሰነዶች፣ የሚያደርጋቸው ሹመቶች፣ ውሳኔዎች የተመለከቱ ጉዳዮችን ያመለክታል)  ላይ የተረጋገጠ ሲሆን ይህም ድምጾቹ በተገኙበት እና በድምጽ መስጫ መራጮች ላይ ተመስርቶ መቆጠር አለበት።

አዲስ ጳጳስ ከተመረጡ በኋላ ወዲያውኑ ምን ይሆናል?

ምርጫው ከተካሄደ በኋላ፣ የመጨረሻው የብፁዕን የካርዲናሎች ኮሌጅ ፀሐፊን እና የጳጳሳዊ ሥርዓተ አምልኮ እና የበዓላት አከባበር መምህርን ወደ ሲስቲን የጸሎት ቤት ይጠራሉ።

የኮሌጁ ዲን፣ ሁሉንም መራጮች በመወከል፣ የተመረጠውን እጩ ፈቃድ በሚከተለው ቃል ይጠይቃሉ፡- “እንደ ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመረጡበትን የእርስዎን ቀኖናዊ ምርጫ ይቀበላሉ?”

ፈቃድ ካገኘ በኋላ፣ “በምን ስም መጠራት ይፈልጋሉ?” ሲሉ ይጠይቃሉ።

ሁለት የክብር ሹሞች ምስክሮች ያሉት የሰነድ አረጋጋጭ ተግባራት የሚከናወኑት በጳጳሳዊ የሥርዓተ አምልኮ እና የበዓላት አከባበር መምህር ሰነድን አዘጋጅቶ የተመረጡትን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስም በመዝገብ ላይ ያስፍራሉ።

ከዚህ ቅጽበት ጀምሮ፣ የተመረጠው እጩ በአለም አቀፉ ቤተክርስቲያን ላይ ሙሉ እና ከፍተኛ ስልጣንን ያገኛል። ምስጢራዊው ምርጫ በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ያበቃል።

ከዚያም ካርዲናል መራጮች ክብርን ይሰጣሉ እና አዲስ ለተመረጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመታዘዝ ቃል ይገባሉ እና ምስጋናም ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ።

የምርጫው አስተባባሪ ካርዲናል በመቀጠል ምርጫውን እና የአዲሱን ጳጳስ ስም ለምዕመናን በታዋቂው መስመር በላቲን ቋንቋ Annuntio vobis gaudium magnum; Habemus Papam” (ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ፣ አዲስ ጳጳስ አግኝተናል) በማለት ያስታውቃሉ።

ወዲያውም አዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ሰገንት ላይ ሆነው ሐዋሪያዊ ቡራኬ "ዑርቢ እና ኦርቢን" (ለከተማው 'ሮም' እና ለአለም) የተሰኘውን ቡራኬ ይሰጣሉ (UDG ገጽ 87-91)።

በመጨረሻው ደረጃ የሚያስፈልገው የጳጳስ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ከተከበረ በኋላ እና ተስማሚ በሆነ ጊዜ ውስጥ አዲሱ ጳጳስ በተደነገገው ሥርዓት መሠረት የቅዱስ ዮሐንስ ላተራን ፓትርያርክ ሊቀ ጳጳስ በመደበኛነት መረከብ ነው።

 

24 Apr 2025, 10:31