ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በስትሮክ እና ሊቀለበስ በማይችል የልብና የደም ዝውውር እክል ምክንያት ማረፋቸው ተገለጸ!
የቫቲካን ግዛት የጤና እና ንጽህና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር አንድሪያ አርካንጄሊ "በኤሌክትሮካርዲዮግራፊክ ቲታቶግራፊ" (ኤሌክትሮካርዲዮግራም (ECG ወይም EKG) በልብ ውስጥ የኤሌክትሪክ ምልክቶችን ለመመዝገብ የሚደረግ ሙከራ ነው። ልብ እንዴት እንደሚመታ ያሳያል። ኤሌክትሮዶች የሚባሉ ተለጣፊዎች በደረት ላይ እና አንዳንድ ጊዜ በእጆች ወይም በእግሮች ላይ ይቀመጣሉ። ሽቦዎች ንጣፎችን ከኮምፒዩተር ጋር ያገናኛሉ፣ ይህም ውጤቶችን ያትማል ወይም ያሳያል) የተረጋገጠውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አሟሟት ይፋዊ የህክምና ዘገባ አውጥተዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሞት ምክንያት እንደ ስትሮክ ፣ከዚህም በኋላ ኮማ እና የማይቀለበስ የልብና የደም ዝውውር ውድቀት ተለይቶ ታይቷል።
የቫቲካን ግዛት የጤና እና ንጽህና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አንድሪያ አርካንጄሊ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ሞት የምያረጋግጥ ይፋዊ የምስክር ወረቀት የሰጡ ሲሆን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ሰኞ ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም ማምሻውን ዘገባውን አቅርቧል።
እንደ የሕክምና ዘገባው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በብዙ ተህዋሲያን የሁለትዮሽ የሳንባ ምች፣ በርካታ ብሮንካይተስ፣ የደም ግፊት እና ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ሳቢያ የሚከሰቱ አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት ችግር ቀደም ብለው ነበራቸው።
የእርሳቸው ሞት በኤሌክትሮካርዲዮጋርፊክ ታናቶግራፊ መሣሪያ ተረጋግጧል። ዶክተር አርካንጄሊ “የሞት መንስኤዎች እስከማውቀውና እኔ በወሰድኩት ውሳኔ ከላይ እንደተገለጸው” ነው በማለት ጽፈዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 266ኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ለባለፉት 12 አመታት አለም አቀፋዊቷን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በብቃት እና በታላቅ መንፈሳዊነት እንደ መሯትም ይታወቃል።
22 Apr 2025, 10:29