የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ ቀጣይነት ያለው መሻሻል እያሳየ መሆኑ ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጤና ሁኔታ መሻሻል በመደበኛነት እንደቀጠለ እና መሻሻያዎችን እያሳየ መሆኑን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት አርብ ጠዋት ሚያዝያ 03/20117 አስታውቋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው እያገገሙ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የሁለትዮሽ የሳንባ ምች በሽታን ያስከተለ ፖሊሚክሮቢያል ኢንፌክሽን በሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ የፕሬስ ጽ/ቤት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን የጤና ሁኔታ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የጤና ሁኔታቸው መሻሻሎችን ማሳየቱን ቀጥሏል ሲል ገልጿል።
ቅዱስ አባታችን ባለፈው ወር እሑድ መጋቢት 14/207 ዓ.ም ከሮም ጂሜሊ ሆስፒታል “በተጠበቀ ሁኔታ” ከሆስፒታል መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሁኔታ መጠነኛ የትንፋሽ፣ የመንቀሳቀስ እና ከድምፅ ጋር የተያያዙ መሻሻሎችን አሳይቷል፣ እና የደም ምርመራዎች ጥሩ መሆናቸውን የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
ቅዱስ አባታችን ሕክምናቸውን፣ መንቀሳቀስ እና የመተንፈሻ አካላት ላይ የሚደርገው ሕክምናን ቀጥሏል፣ በተጨማሪም አነስተኛ ተጨማሪ ኦክሲጅን ያስፈልጋቸዋል። በቀን ውስጥ ተጨማሪ ኦክስጅን ሳይጠቀሙ ለረጅም ጊዜ ሊሄዱ ይችላሉ ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።
ከዚህም በላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሥራ እንቅስቃሴያቸውን እንደቀጠሉ እና በጥሩ መንፈስ ላይ መሆናቸውን የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሳምንት (የሕማማት ሣምንት) የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ ለመወያየት ገና በጣም ገና መሆኑን የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ ገልጾ ተጨማሪ መረጃ በክስተቶች ላይ ተመርኩዞ ሊሰጥ እንደሚችል አስረድቷል ።