የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ አስከሬን ዓርብ አመሻሽ ላይ በሎት ሥነ-ሥርዓት እንደሚታሸግ ተገለ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ቅዳሜ ሚያዝያ 18/2017 ዓ. ም. ጠዋት ከሚፈመው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ቀደም ብሎ ዓርብ ዕለት የሚከናወነውን የሎት ሥነ-ሥርዓት የሚመሩት የቅድስት ሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የንብረት እና የፋይናንስ ክፍል አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል ኬቨን ጆሴፍ ፋሬል እንደሚሆኑ ተገልጿል።
በሎት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በርካታ ብፁዕ ካርዲናሎች እና የቅድስት መንበር ሓላፊዎች እንደሚገኙ ሲጠበቅ ዕለቱ ካለፉት ቀናት ወዲህ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች ለሟቹ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክብርን በመስጠት ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ እየመጡ የሚያደርጉት ስንብት ማብቂያ ይሆናል።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስከሬን ያለፈው ረቡዕ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ለምእመናን ክፍት ከሆነበት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ 50,000 በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል። ባዚሊካው ሐሙስ እስከ ንጋቱ አሥራ አንድ ተኩል ድረስ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ ለአንድ ሰዓት ተኩል ተዘግቶ ከማለዳው አንድ ሰዓት ላይ እንደገና ተከፍቷል።
ዓርብ ሚያዝያ 17/2017 ዓ. ም. ከምሽቱ በሁለት ሰዓት ላይ በሚፈመው የአስከሬን ማሸግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ባቲስታ ሬ፣ ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን፣ ብጹዕ ካርዲናል ሮጄር ማሆኒ፣ ብጹዕ ካርዲናል ዶሜኒክ ማምበርቲ፣ ብጹዕ ካርዲናል ማውሮ ጋምቤቲ፣ ብጹዕ ካርዲናል ባልዳሳሬ ሬይና እና ብጹዕ ካርዲናል ኮንራድ ክራጄቭስኪ እንዲገኙ የሥርዓተ አምልኮ እና በዓላት አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ጠይቋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከሚገኙት ጳጳሳት መካከል ሊቀ ጳጳስ ኤድጋር ፔና ፓራ፣ ሊቀ ጳጳስ ኢልሰን ደ ኢየሱስ ሞንታናሪ፣ ሞንሲኞር ሊዮናርዶ ሳፒየንሳ፣ የቫቲካን አስተዳደር ክፍል ሠራተኞች፣ የቫቲካን ማረሚያ ቤት ተወካዮች፣ የሟቹ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሐፍት እና ሌሎችም በጳጳሳዊ ሥርዓተ ቅዳሴ አስተባባሪ ሊቀ ጳጳስ ዲዬጎ ራቬሊ የተጋበዙት ይገኙበታል።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ቅዳሜ ሚያዝያ 18/2017 ዓ. ም. ከጠዋቱ አራት ሰዓት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የሚፈም ሲሆን፥ ይህም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ጥንታዊ ትውፊ የተከተለ ዘጠኝ የሐዘን ቀናት መጀመሪያ ይሆናል።
እሑድ ሚያዝያ 19/2017 ዓ. ም. ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ላይ ከሚከበር የመለኮታዊ ምህረት እሑድ በስተቀር ከዓርብ ጀምሮ በእያንዳንዱ ቀን ከአሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይና ባዚሊካ ውስጥ የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት ይካሄዳል።