MAP

የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ አስክሬን በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ውስጥ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ አስክሬን በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ውስጥ  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ አስከሬን የቀብር ሥነ-ሥርዓት እስከሚፈጸም ድረስ በቫቲካን እንደሚቆይ ተገለጸ!

የሟቹ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስከሬን ቅዳሜ ጥዋት ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እስከሚፈጸም ድረስ በቫቲካን እንደ ሚቆይ የተገለጸ ሲሆን ረቡዕ ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም አስክሬናቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ እንደ ሚወሰድም ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የቅድስት መንበር ኅትመት ክፍል ማክሰኞ ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም እንዳስታወቀው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 04፡00 (በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 05፡00 ሰዓት) በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንደሚፈጸም አስታውቋል።

የብፁዕን ካርዲናሎች የመማክርት ቡድን ዋና ጸኃፊ የሆኑት  ብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ባቲስታ ሬ ቅዳሴውን ከሊቀ ጳጳሳት፣ ብፁዕ ካርዲናሎች፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት እና ቀሳውስት ጋር አብረው ያሳርጋሉ ተብለው ይጠበቃል።

የመስዋዕተ ቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት የቅዱስ ቁርባን በዓል የመጨረሻ ምስጋና እና የስንብት ንግግር ይጠናቀቃል ፣ የኖቪና መጀመሪያን ወይም የዘጠኝ ቀናት ሐዘን እና ቅዳሴ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ነፍስ ዕረፍት በመቀጠል ይደረጋል።

የሟቹ ሊቃነ ጳጳሳት አስከሬን ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ከዚያም ወደ ቅድስት ማርያም ሜጀር ባዚሊካ ይወሰዳል።

ቀደም ሲል እንደ ተገለጸው ረቡዕ ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም የጳጳሱን አስከሬን የያዘው የሬሳ ሣጥን ምእመናን አክብሮታቸውን ከገለጹ ቡኋላ ከቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ይወሰዳል።

ብፁዕ ካርዲናል ኬቨን ፋሬል፣ የቅድስት ሮማን ቤተ ክርስቲያን ካሜርሌንጎ (ካሜርሌንጎ የአንድ ማህበረሰብ ንብረት እና ፋይናንስ ጠባቂ እና አስተዳዳሪ፣ በተለይም የሃይማኖታዊ ተቋማት ማለት ነው) ዋና ጸኃፊ ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 3 ሰዓት ላይ በጸሎት የሚጀመረውን የሁደት ሥርዓት ይመራሉ።

ሁደቱ ከቅድስት ማርታ አደባባይ እና በሮማውያን ፕሮቶማርቲስቶች አደባባይ በኩል እንደሚያልፍ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ አስታውቋል።

ከዚያ በኋላ ሰልፉ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወጥቶ በማዕከላዊ በር በኩል ወደ ቫቲካን ባሲሊካ ይገባል ።

የኑዛዜ መሠዊያ ተብሎ በሚጠራው መንበረ ታቦት ላይ፣ ካርዲናል ካሜርሌንጎ የቃሉን ሥርዓተ ቅዳሴ ይመራሉ፣ በዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ላይ የሮማን ጳጳስ አካላት ጉብኝቶች ይጀምራሉ።

 

22 Apr 2025, 11:23