MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከእዚህ አለም ድካም በሞት መለየታቸው ተገለጸ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከእዚህ አለም ድካም በሞት መለየታቸው ተገለጸ! 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከእዚህ አለም ድካም በሞት መለየታቸው ተገለጸ!

ብፁዕ ካርዲናል ፋረል የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ከእዚህ አለም ድካም በሞት መለየታቸውን በተመለከተ ሐዘን በተሞላበት መልኩ እና ሁኔታ እንዲህ በማለት አስታውቀዋል።

“ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! የቅዱስ አባታችን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ሞት ስገልጽ በታላቅ ሐዘን ውስጥ ሆኜ ነው" ።

ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 13/2017 ዓ. ም. ጠዋት በሮም የሰዓት አቆጣጠ 7፡35 (በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር 2፡35) ላይ የሮም ጳጳስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ አብ ቤት ተመለሱ። ሕይወታቸውን በሙሉ ለጌታ እና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የተሰጡ ነበሩ።  

የወንጌል እሴቶችን በታማኝነት፣ በድፍረት እና በአለማቀፋዊ ፍቅር እንድንኖር አስተምረውናል፤ በተለይም በጣም ድሆችን እና በጣም የተገለሉ ሰዎችን በመደገፍ።

የጌታ ኢየሱስ እውነተኛ ደቀ መዝሙር በመሆን ላሳዩት ምሳሌ ታላቅ ምስጋና በመስጠት፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ነፍስ ለአንዱና ለቅድስት ሥላሴ ማለቂያ የሌለው መሐሪ ፍቅር በአደራ እንሰጣለን።

 

21 Apr 2025, 10:46