MAP

ንጉሥ ቻርለስ እና ንግሥት ካሚላ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ! ንጉሥ ቻርለስ እና ንግሥት ካሚላ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ!   (ANSA)

ንጉሥ ቻርለስ እና ንግሥት ካሚላ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን የቅድስት ማርታ ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከእንግሊዝ ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ እና ንግሥት ካሚላ ጋር በግል መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ሁለቱ ጥንዶች ጋብቻ የፈጸሙበትን አመታዊ መታሰቢያ ላይ በመሆናቸው ቅዱስነታቸው እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በተለይ ለቤተሰባቸው 20ኛ የጋብቻ በዓላቸውን በሚያከብርበት እና የንጉሡ አባት ፊሊፕ የኤድንበርግ የሞቱበትን አራት አመት በሚዘከርበት ቀን፣ ንጉስ ቻርልስ እና ንግስት ካሚላ ረቡዕ ሚያዝያ 01/2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ተገናኝተዋል።

ግንኙነቱ የተካሄደው በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መኖሪያ ቤት ውስጥ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከጂሜሊ ሆስፒታል ከወጡ በኋላ ከሁለት ሳምንታት በላይ ሆኖዋቸዋል፣ይህ ግንኙነት እርሳቸው ከሆስፒታል ከወጡ በኋላ ያደረጉት የመጀመሪያው ሆፊሴላዊ ግንኙነት ነው።  

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ረቡዕ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ፡- “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ከሰአት ከግርማዊነታቸው ንጉሥ ቻርልስ እና ንግሥት ካሚላ ጋር በግል ተገናኝተው ተወያይተዋል። በስብሰባው ሂደትም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሠርጋቸውን ዓመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ ሊቀ ጳጳሱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፣ በተጨማሪም ንጉሥ ቻለስ ከአንድ አመት በፊት በተረጋገጠው የካንሰር ህክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች ምክንያት በሆስፒታል ተኝተው ታክመው በመውጣታቸው ምክንያት የንጉሱን የጤና ሁኔታ የሚያመለክት ነበር" ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ንጉሡ እና ንግስቲቱ ረቡዕ ከሰአት በኋላ ከቅዱስነታቸው ጋር በተገናኙበት ወቅት መልካም ምኞታቸውን በአካል መግለጽ ችለዋል። ሐሙስ ማለዳ ላይ በንጉሣዊው ቤተሰብ የኤክስ ግጽ ላይ የተለጠፈ ልጥፍ ፣ “ንጉሱ እና ንግሥቲቱ 20ኛ የሠርጋቸውን አመት በዓል አስመልክቶ ጳጳሱ በሰጡት ደግነት የተናገሯቸውን እና መልካም ምኞታቸውን በአካል ለእርሳቸው ማካፈል በመቻላቸው ትልቅ ክብር ተሰምቷቸዋል” ብሏል።

የእንግሊዝ ነገሥታት በሮም ለሦስት ቀናት ባደረጉት ጉብኝት ከኢጣሊያ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ እና ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተገናኝተዋል። እንደሚታወቀው ንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊ የዩናይትድ ኪንግደም ሉዓላዊ ገዥ ብቻ ሳይሆኑ (የሌሎች 14 የኮመንዌልዝ ግዛቶች) እና የእንግሊዝ ቤተክርስትያን ጠቅላይ ገዥም ናቸው።

10 Apr 2025, 14:15