MAP

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ድምጽ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ድምጽ   (ANSA)

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ድምጽ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ. በመጋቢት 13/2013 ዓ.ም. 266ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተመረጡበት 12ኛ ዓመት ዛሬ ታስቦ እንደሚውል ይታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በታኅሳስ 17/1936 ዓ.ም የአርጀንቲና ዋና ከተማ በሆነችው በቦይነስ አይረስ መወለዳቸው የምታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የ88 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ 12 ዓመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዓመታት በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ሚስዮናዊ የሆነ ተግባሯን አጠናክራ እንድትቀጥል እና ለሁሉም የሰው ልጆች በቅዱስ ወንጌል የሚገኘውን ደስታ እንድታበስር፣ በማንኛውም ቅዱስ ወንጌልን የማብሰር ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በቀጥታ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ በመፍቀድ ማከናውን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው አበክረው መናገራቸው እና አሁንም ቤተ ክርስቲያን በእዚሁ መንገድ እንድትቀጥል ማሳሰባቸውን በፍጹም አላቋረጡም።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተመረጡበት 12ኛ አመት በመጋቢት 04/2017 ዓ.ም ታስቦ በሚውልበት በአሁኑ ወቅት ቅዱስነታቸው ይህንን እለት በሆስፒታል ውስጥ ሆነው ለማሳለፍ ተገደዋል። ይህንን መታሰቢያ በተመለከተ የቫቲካን ዜና የአርትኾት ክፍል ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ አድርያ ቶርኔሊ የሚከተለውን መልእክት አቅርበዋል።

ዘንድሮ፣ ለአንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው በጂሜሊ ሆስፒታል አስረኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሆስፒታል ክፍላቸው ውስጥ ለቆዩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እዚያው ሆነው ጳጳስ የሆኑበትን 12ኛውን አመት ያከብራሉ።  የቅርብ ጊዜዎቹ የሕክምና ውጤቶች የምያወጧቸው ዜናዎች አበረታች ናቸው፣ የእርሳቸው የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ በቅርቡ ወደ ቫቲካን ሊመለሱ እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን። አሁንም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ ወቅት እያጋጠሟቸው ያሉት ነገሮች ይህን የጵጵስና ሹመት የጀመሩበትን አመታዊ በዓል እጅግ ያልተለመደ ያደርገዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ እ.አ.አ የ2025 ዓ.ም ኢዮቤልዩ አመት ባርከው ያሰጀመሩ ሲሆን፣ በዚያውም የቅዱሱ በር አከፋፈት መንፈስዊ ሥነ-ስርዓት ማከናወናቸውም ይታወሳል። የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ በበሽተኞች መካከል ታመው በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት እርሳቸው ራሳቸው በመከራ እየተሰቃዩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ስለ ሰላም ሲጸልዩ በብዙ የዓለም ማሕበረሰቦች ጸሎት ታጅበው ነው። በእነዚህ አሥራ ሁለት ዓመታት ውስጥ “እባካችሁ ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ከሚለው ተማጽኖዋቸው ባሻገር እራሳቸው የመሯቸውን እና ያከናወኗቸውን ስብሰባዎች፣ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮን ወይም የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት የማያውቁ ሰዎች እንኳን ዛሬ ለእራሳቸው በጥልቅ የሚጨነቁ መዕመናን እና ኢማንያን ሳይቀሩ እርሳቸውን ያስታውሷቸዋል።

አሁን የቤተክርስቲያንን ተፈጥሮ እና የሮማ ኤጲስ ቆጶስ ተልእኮ የምናስብበት ጊዜ ነው፣ ይህም ከአንድ መድብለ ኢንተርናሽናል ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ በእጅጉ የተለየ ነው። ከአሥራ ሁለት ዓመታት በፊት፣ በወቅቱ የነበሩት ካርዲናል ቤርጎሊዮ ለጠቅላላ ጉባኤዎች ንግግር አድርገዋል፣ የሄንሪ ዴ ሉባክን አስተያየት በመጥቀስ፣ ቤተ ክርስቲያን ልትደርስበት የምትችለው “ከፉ ክፋት” “መንፈሳዊ ዓለማዊነት” ነው፡- “የራሷ ብርሃን እንዳላት የምታምን ቤተ ክርስቲያን አደጋ፣ በራሷ ጥንካሬ፣ የራሷ ስልቶች፣ የራሷ ቅልጥፍና፣ እና “ከእንግዲህ ውጤታማ ለመሆን አትችልም” የሚሉ አስተሳሰቦች መሆናቸውን ገልጸው ነበር። የሌላውን ብርሃን በማንፀባረቅ ፣ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ባለው ጸጋ ብቻ መኖር እና መተግበር አልቀረም።

እነዚህን ቃላት በድጋሚ በማስታወስ፣ ዛሬ፣ በጂሜሊ ሆስፒታል አስረኛ ፎቅ መስኮቶች በፍቅር እና በተስፋ እንመለከታለን። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን አሁንም  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመቁጠሪያ ጸሎት ወቅት በቅርብ ቀናት ውስጥ ለተቀላቀለው ለዚህ ደካማ ድምጽ እናመሰግናለን - ስለሰላም የሚማጻኑ እና ጦርነትን ሳይሆን ውይይትን ይደግፋሉ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልካም አመታዊ በዓል፣ ይሁንሎት! አሁንም ድምጾን መስማት በጣም እንፈልጋለን!

 

 

12 Mar 2025, 16:51