MAP

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የመኖሪያ ቤት የሚገኝበት በቫቲካን የሚገኘው የቅድስት ማርታ ሕንጻ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የመኖሪያ ቤት የሚገኝበት በቫቲካን የሚገኘው የቅድስት ማርታ ሕንጻ  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

የር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑ ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከደረሰባቸው የሁለት ወገን የሳንባ ምች ህመማቸው እያገገሙ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የጤንነታቸው ሁኔታቸው ቀስ በቀስ መሻሻል ማሳየት መቀጠሉን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ አስታውቋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከሁለትዮሽ የሳንባ ምች በሽታ ማገገማቸውን በተመለከተ የቅድስት መንበር የፕሬስ ቢሮ ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ አርብ ዕለት መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ብሩኒ የጳጳሱ ጤንነት የተረጋጋ ነው፣ በመተንፈሻ አካላታቸው ላይ የጤና መሻሻል እየታየ እና እንዲሁም በንግግራቸው ላይ መጠነኛ መሻሻሎችን አሳይቷል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ቅዱሱ አባታችን በቀን ውስጥ በአፍንጫው በሚገባ ቱቦ የሚቀበሉት ከፍተኛ መጠን ያለው ኦክሲጅን ቀስ በቀስ እየቀነሰ መቷል፣ በሌሊት መጠነኛ መቀነስን ማሳየቱም ይቀጥላል ብለዋል።

እሮብ ላይ በተደረጉ የደም ምርመራዎች መሰረት የጳጳሱ የደም ህክምና መለኪያዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ያሳያል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕክምና ፣ በጸሎት ፣ በእረፍት እና በአንዳንድ የሥራ እንቅስቃሴዎች መካከል በማፈራረቅ ቀናቸውን ማሳለፍ ቀጥለዋል ፣ ሁሉም የሮማን ኩሪያ ጽ/ቤቶች እንቅስቃሴዎችን ለማዘመን የሚረዱ ሰነዶችን ልከዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በየቀኑ በቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ በሚገኘው የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ መከታተላቸውን ቀጥለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማያንማር ስለደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተነገራቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለብዙ ተጎጂዎች እየጸለዩ ነው ሲሉ አቶ ቡሩኒ አክለው ገልጸዋል።

28 Mar 2025, 16:08