MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕክምና ላይ የሚገኙበት የጂሜሊ ሆስፒታል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕክምና ላይ የሚገኙበት የጂሜሊ ሆስፒታል  (AFP or licensors)

የጳጳሱ የጤና ሁኔታ መጠነኛ መሻሻሎችን ማሳየቱን ቀጥሏል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጤና ሁኔታ መጠነኛ መሻሻሎችን ማሳየቱ የገለጸ ሲሆን አሁን ቅዱስነታቸው ለተወሰኑ ቀናት በሆስፒታል ውስጥ እንደሚቆዩ መግለጫው አክሎ ጠቁሟል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ትናንት ምሽት ማለትም መጋቢት 08/2017 ዓ.ም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል፣ አጋዥ የመተንፈሻ መሣርያ ቅዱስነታቸው መጠቀም አላስፈለጋቸውም፣ ይህ ማክሰኞ መጋቢት 08/2017 ዓ.ም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን የጤና ሁኔታ በተመለከተ የቅድስት መንበር የፕሬስ ቢሮ ለጋዜጠኞች ከሰጠው መግለጫ የተወሰደ ነው። የካቲት 07/2017 ዓ.ም ቅዱንስነታቸው በመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን እና በሁለትዮሽ የሳንባ ምች ተይዘው በነበረበት ወቅት በሮም ከተማ ወደ ሚገኘው ጂሜሊ ሆስፒታል ተወስደው የሕክምና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑ ይታወቃል።

መግለጫው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁኔታ ውስብስብ በሆነ የጤና ማዕቀፍ ውስጥ የተረጋጋ መሆኑን እና በሞተር እና በመተንፈሻ አካላት መሣርያ የሚደረግላቸው ድጋፍ በመቀነስ መጠነኛ መሻሻሎች መኖራቸውን አመልክቷል።

ትናንት ምሽት ቅዱስነታቸው አየር መተንፈሻ መሣርያ መጠቀም አላስፈለጋቸውም ነበር፣ ይህ አወንታዊ እድገት ቢሆንም፣ ቀስ በቀስ የመቀነስ ሂደት አካል ሆኖ በጥንቃቄ መታየት አለበት።

የቅዱስ አባታችን እለት በህክምና፣ በጸሎት እና ቀላል ስራ በመስራት አሳልፈው ነበር። አሁን ጠንካራ ምግብን የሚያጠቃልለው በሕክምና የታዘዘውን አመጋገብ መከተል ቀጥሏል።

19 Mar 2025, 10:52