MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ጂሜሊሆስፒታል የምያደርጉትን ሕክምና እንደ ቀጠሉ ነው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ጂሜሊሆስፒታል የምያደርጉትን ሕክምና እንደ ቀጠሉ ነው 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሮም ጂሜሊ ሆስፒታል ምሽቱን በሰላም ማሳለፋቸው ተገለጸ!

እሮብ ማለዳ የካቲት 26/2017 ዓ.ም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን የጤና ሁኔታ አስመልክቶ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የደረሰባቸውን የሳንባ ምች ሕመም ተክትሎ በአሁኑ ወቅት በሮም ጂሜሊ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት እያገኙ እንደ ሆነ በድጋሜ ያስታወሰው መግለጫው ትላንት ማታ ቅዱስነታቸው በዕረፍት እንዳሳለፉ ገልጿል።

የዚህ ዜና አቅርቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትላንት ሌሊት ጥሩ አርፈዋል እና ዛሬ ማለዳ ከእንቅልፋቸው እንደተነሱ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት እሮብ ማለዳ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሁለትዮሽ ማለትም በብሮንካይትስ እና የሳንባ ምች ሕመም ምክንያት በሮም ጂሜሊ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። የልብ፣ የኩላሊት እና የደም አጠቃላይ ምርመራ ውጤት የጤና ሁኔታቸው​​የተረጋጋ መሆኑን ያሳያል ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ማክሰኞ ማምሻውን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት የቅዱስ አባታችን የጤንነት ሁኔታ ላይ በሰጠው የሕክምና መረጃ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የጤና ሁኔታ በእለቱ የተረጋጋ መሆኑን እና የመተንፈሻ አካላት ችግር ወይም ብሮንካይተስ አላጋጠማቸውም ብሏል።

ከዚህም በላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትኩሳት እንዳልተሰማቸው እና ነቅተው ህክምናቸውን በመከታተል እና ንቁ ሁነው እንደ ዋሉ መግለጫው አክሎ ገልጿል።

የፕሬስ ቢሮው አክሎም በእለቱ በጸሎት እና በእረፍት ጊዜ በማሳለፍ መካከል እያፈራረቁ እንዳሳለፉ የገለጸ ሲሆን ቅዱስ ቁርባን እንደ ተቀበሉም አክሎ መግለጫው ገልጿል።

 

05 Mar 2025, 11:34