ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ሌሊቱን በጂሜሊ ሆስፒታል በጥሩ ሁኔታ ማሳለፋቸው ተገልጿል።
በሰኞ ማለዳ የካቲት 24/2017 ዓ.ም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ጤንነት በተመለከተ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሌሊቱን ሙሉ በመልካም ሁኔታ ማሳለፋቸው ገልጿል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሌሊቱን ሙሉ ጥሩ እንቅልፍ ተኝተው እንደነበር የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ሰኞ ማለዳ አስታውቋል።
በቅርብ ጊዜው የተሻሻለው የእሁድ ምሽት መግለጫ የጳጳሱ ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን ያሳያል።
የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ሰጥቷል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቀደም ሲል ይጠቀሙበት የነበረውን በከፍተኛ ደረጃ የመተንፈሻ አካል አጋዢ መሣሪያ ከቅርብ ቀናት ጀምሮ መጠቀም መቀነሳቸውን እና አሁን መደበኛ የሆነ የኦክስጂን ፍሰት እየተሰጣቸው እንደሚገኝ አክሎ ገልጿል።
ከጳጳሱ የጤና ሁኔታ ውስብስብነት ጋር በሚስማማ መልኩ የሚደርገው ሕክምና እንደተጠበቀ ይቆያል። እሁድ እለት የካቲት 23/2017 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሆስፒታል ቆይታቸው ሲንከባከቧቸው ከነበሩት ሃኪሞች ጋር መስዋዕተ ቅዳሴ ተሳትፈዋል። የቀረውን ቀን በእረፍት እና በጸሎት አሳልፈዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በየካቲት 14/2020 ዓ.ም በአተነፋፈስ ችግር ምክንያት ወደ ጂሜሊ ሆስፒታል ተወስደው በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
03 Mar 2025, 11:44