ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ መስዋዕተ ቅዳሴ የተከታተሉ፣ ሕክምናቸውንም እየቀጠሉ እንደምገኙ ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅ አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከሕመማቸው ማገገም ቀጥለው ሕክምናቸውን፣ እንቅስቃሴያቸውን እና የመተንፈሻ አካላት ጋር የተገናኘ የፊዚዮቴራፒ ሕክምና በተለይም ለድምፅ ማገገሚያ የሚሆን ሕክምና እያደረጉ ሲሆን የግል ጸሎት በማድረግ እና በመኖሪያው ቤታቸው ውስጥ በሚገኘው የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ እየተከታተሉ እንደ ሆንም ተገልጿል።
ጳጳሱ እሑድ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም ዓ.ም ከሆስፒታል መውጣታቸው ይታወሳል፣ ቅዱስነታቸው በሁለትዮሽ የሳንባ ምች ሕመም ምክንያት በሮም ጂሚሊ ሆስፒታል ለ38 ቀናት በሆስፒታል ውስጥ ከቆዩ በኋላ አሁን በማገገም ላይ እንደሚገኙ በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት እውቅና ለተሰጣቸው ጋዜጠኞች ከሰጣቸው መገለጫ ለመረዳት ተችሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም በሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ሆነው 3,000 ለሚጠጉ ሰዎች ሰላምታ እና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ በሮማው ማሪያ ማጆሬ ተብሎ በሚጠራው የቅድስት ማርያም ባዚሊካ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ቆይታ ካደረጉ በኋላ በቫቲካን በሚገኘው ቅድስት ማርታ መኖሪያ ቤታቸው መመለሳቸው ይታወሳል።
የጳጳሱ የማገገምና የእረፍት ጊዜ በመኖሪያ ቤታቸው “ሁለት ወር ያህል መሆን አለበት” ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡት ዶክተር ሰርጂዮ አልፊየሪ፣ የጳጳሱን በጂሜሊ ሆስፒታል መግባታቸውን የሚቆጣጠሩት ዶክተር እና የግል ሀኪማቸው ዶክተር ሉዊጂ ካርቦን ቅዳሜ ምሽት መጋቢት 13/2017 ዓ.ም በጂሜሊ ሆስፒታል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቃቸውም ይታወሳል።
እረፍት፣ አካላዊ ሕክምና እና የኦክስጂን ሕክምና (ቴራፒ)
ማክሰኞ መጋቢት 16/2017 ዓ.ም የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ እንዳስታወቀው “ጳጳሱ ቅዳሜ ዕለት በዶክተሮች እንደተገለፀው የሕክምና ድጋፍ እቅዱን እየተከተሉ ነው" ሲል አስታውቋል።
በወቅቱ ዶክተር አልፊዬሪ እና ዶክተር ካርቦን እንደገለጹት ቅዱስ አባታችን በየቀኑ በጂሜሊ እንዳደረጉት ሁሉ የሙሉ ጊዜ የመንቀሳቀስ እና የመተንፈሻ አካላት የፊዚዮቴራፒ ሕክምና ሲደረግላቸው "ለረዥም ጊዜ በአፍ የሚሰጥ" የመድሃኒት ሕክምናን መቀጠል አለባቸው ብለው መናገራቸው ይታወሳል።
ሐኪሞቹ በግለሰብም ሆነ በቡድን ቅዱስነታቸው ከስብሰባ እንዲርቁ እና የ24 ሰዓት የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ የኦክስጂን ቴራፒን ጨምሮ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች እንዲያገኙ እና ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ ሁኔታዎች እንዲፈቱ ለቅዱስነታቸው ምክረ ሐሳብ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። ይህ እንክብካቤ በቫቲካን የጤና እና ንፅህና ዳይሬክቶሬት እየተሰጠ ሲሆን የህክምና ቡድን ሁል ጊዜ ከጳጳሱ ጋር ይገኛል።
ቅዱስ አባታችን በሆስፒታል ውስጥ በነበሩበት ወቅት በኦክሲጅን ሕክምና መቀበላቸውን ቀጥለዋል-በሌሊት ከፍተኛ መጠን ያለው ኦክሲጅን በአፍንጫ በቱቦ ይሰጣቸዋል፤ በቀን ውስጥ የኦክስጂን ሕክምናን ቀስ በቀስ ይቀንሳሉ።
የመስዋተ ቅዳሴ እና የስራ እንቅስቃሴዎች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሆስፒታል ውስጥ እንዳደረጉት ፣ በአሥረኛው ፎቅ ላይ በሚገኘው የጸሎት ቤት ውስጥ ቅዳሴን ሲሳተፉ እንደቆዩ ሁሉ፣ አሁንም በቅድስት ማርታ መኖሪያ ቤታቸው በሚገኘው የጸሎት ቤት ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ መከታተል ቀጥለዋል።
ከዚህም በላይ ቀደም ሲል በተጠቀሰው የአቅም ውስንነትን ከግምት ባስገባ መልኩ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይቀጥላሉ። እንዲሁም የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት የቀትር መገለጫ ይፋ እንዳደረገው ሊቀ ጳጳስ ኢግናዚዮ ሴፋሊያ የቤላሩስ የቫቲካን ሐዋርያዊ እንደራሴ እንዲሆኑ እና የእኔታ አባ ፍራንችስኮ ኢባ በሮማ ሮታ ፍርድ ቤት የጋብቻ ተከላካይ ጠበቃ (የተክሊል ጋብቻ ጠበቃ፣ ጋብቻን የተመለከተ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን ሲሆን ግዴታው የተክሊል ጋብቻ ቃል ኪዳን ማስጠበቅ፣ መከላከል በትዳር ውስጥ የተፈጸሙ ጉዳዮችን ለመስማት በተደነገገው ሂደት ውስጥ ቀደም ሲል የተፈረመ ጋብቻ ትክክለኛነት ወይም ጋብቻ እንዳልበረ ማድረግን ያካትታል) ይህንን ጉዳይ የሚከታተሉ ጠበቆች የበላይ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።
በመጪዎቹ ቀናት የሊቀ ጳጳሱን የጊዜ ሰሌዳ፣ ወይም ወደፊት ስለሚደረጉ ክንውኖች እንደ የተለያዩ ኢዮቤልዩ አከባበር ወይም የቅዱስ ሳምንት ሥርዓቶችን በተመለከተ ምንም ዓይነት ትክክለኛ ዝርዝሮች አልተሰጡም። ዶክተሮቹ አጽንኦት ሰጥተው እንደገለፁት ቅዱስነታቸው ሙሉ በሙሉ ማገገም እንዳለባቸው እና በቅርበት ክትትል ሊደረግላቸው እንደሚገባ አበክረው የገለጹ ሲሆን “የሚጠበቁትን የጤና ማሻሻያዎች” በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት “አንዳንድ ውሳኔዎች እየታሰቡ ናቸው እናም በሚቀጥሉት ሳምንታት በሚደረጉ ማሻሻያዎች ላይ ተመስርተው የሚደረጉ ናቸው” ብሏል።
በጽሑፍ የተዘጋጀ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት ያዘጋጁት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቅዱስነታቸው እስከምያገግሙ ድረስ በጽሑፍ መልክ መቅረቡ ይቀጥላል።
አሁንም በእየጊዜው የሚታዩት ክስተቶች በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም ዘወትር እሁድ የሚደርገው የመልእከ እግዚአብሔር ጸሎት እና የእለቱ የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በቅድስት መንበር የኅትመት ክፍል ይለቀቃል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ ጎብኝዎችን እንደማይቀበሉ እና የቅርብ ተባባሪዎቻቸውን ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ እንዳዩ አስታውቋል። ከርዕሰ መስተዳድሮች እና ከመስተዳድሮች ሊደረጉ የታቀዱ ጉብኝቶችን በተመለከተ ምንም አይነት እቅድ አልተገለጸም።
የዶክተር ሰርጂዮ አልፌሪ አስተያየት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቤታቸው በመገኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። ዶክተር አልፌሪ እና ዶክተር ካርቦኔ ሁለቱም ጳጳሱ ጤንነታቸው ከተሻሻለ በኋላ ያገኟቸውን መልካም እርካታዎች ቀደም ብለው ጠቅሰዋል። በጂሜሊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተረጋገጠው የሕመሙ በጣም አደገኛ ደረጃ አልፏል፣ እና በጣም ከባድ የሆኑ ኢንፌክሽኖች ተወግደዋል።
በዚያ ጉባኤ ላይ፣ ዶ/ር አልፊየሪ ጳጳሱ ሕይወታቸው አደጋ ላይ የወደቀባቸው ሁለት ወሳኝ ጊዜያት እንዳጋጠማቸው ገልጿል።
ከጣሊያን ዕለታዊ ጋዜጣ ኮሪየር ዴላ ሴራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ዶ/ር አልፊየሪ በየካቲት 21/2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቅዱስነታቸው ሁኔታ በብሮንካስፓስም ችግር ምክንያት መባባሱን አስታውሰዋል።
“ለመጀመሪያ ጊዜ በዙሪያው ባሉት አንዳንድ ሰዎች ዓይን እንባ ሲፈስ አይቻለሁ—በዚህ ሆስፒታል ውስጥ እንደገባኝ ከሆነ የተረዳሁት እንደ አባት በእውነት የሚወዷቸው ተረዳው። ሁኔታውይበልጥ እየተባባሰ እንደሄደ እና ሕይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።
ሌሎች የአካል ክፍሎችን የመጉዳት ዕድሉ ከፍተኛ ቢሆንም ቆም ብለን እንዲሁ እንዲሄዱ ወይም ሁሉንም መድኃኒቶችና ሕክምናዎች ወደፊት መግፋት እንዳለብን መወሰን ነበረብን። በመጨረሻም መዋጋትን መርጠናል ሲሉ ሐኪሙ ገልጿል፤ የመጨረሻው ውሳኔ የተላለፈው በጳጳሱ ራሱ እንደሆነ ገልጿል።
እውነቱን ለመናገር የጳጳሱ ጥያቄ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ስለ ጤንነታቸው ሙሉ በሙሉ እንዲነገራቸው አጥብቀው ተናግረዋል ። "እውነቱን እንድንነግራቸው ጠየቁን እና ስለ ሁኔታው እውነቱ እንዲነገራቸው ፈልገው ነበር" ብለዋል ዶክተር አልፊየሪ።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱን ሁኔታ በተመለከተ የተጻፈውን ወቅታዊ መረጃ በተመለከተ፣ ዶክተር አልፊየሪ ወቅታዊ የሕክምና ውጤቶች ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጸኃፊ እንደደረሷዋቸው ገልፀው እሺታ ከማግኘታቸው በፊት ተጨማሪ ዝርዝሮችን ጨምረዋል።