ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በጂሜሊ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኘው የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ መሳተፋቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
እሁድ መጋቢት 07/2017 ዓ.ም ጠዋት 200 የሚጠጉ ከዩኒሴፍ እና ከተለያዩ የጣሊያን ቡድኖች የተውጣጡ ህጻናት አበባ እና ፊኛ ተሸክመው እና ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “ተምሳሌታዊ እቅፍ” ይዘው በጂሜሊ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ተሰብስበው ነበር።
ጸሎት፣ እረፍት፣ ፊዚዮቴራፒ
እሑድ መጋቢት 07/2017 ዓ.ም ምሽት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "መገኘት" አዲስ ምልክት በጸሎት ጊዜ ደረሰ። ጸሎት የእለት ተእለት ተግባራቸው አንዱ አካል ነው፣ ከእረፍት እና ከህክምና ጋር፡ ሁለቱም ማለትም በመድኃኒት የሚከናወነው ሕክምና እና የፊዚዮቴራፒ ሕክምና የሚቀጥሉ ናቸው። የቅድስት መንበር የዜና ማተሚያ ክፍል እንደገለጸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለይ የፊዚዮቴራፒ ሕክምና ተጠቃሚ ሆነዋል። እሁድ ቀን እንግዶችን አልተቀበሉም ነበር፣ እናም አንዳንድ ስራዎችንም ማከናወን ቀጥለዋል።
ቀደም ባሉት ቀናት እንደተረጋገጠው የጳጳሱ የጤና ሁኔታ የተረጋጋ ቢሆንም አሁንም በጤና ሕክምና አውድ ውስጥ የሕክምና ባልደረቦች - በቅርብ ጊዜ ጽሑፎች ላይ እንደተዘገበው - "ውስብስብ" በማለት ይገለፃል። ከጳጳሱ የተረጋጋ የጤና ሁኔታ አንጻር ሲታይ የሕክምና ዝመናዎች ብዙ ጊዜ እየወጡ ነው። ከዚሁ ጋር የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን የጤና ሁኔታ በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ መስጠቱን ቀጥሏል። በአሁኑ ጊዜ 700 እውቅና ያላቸው ጋዜጠኞች አሉ፣ ቁጥሩ ጳጳሱ ሆስፒታል ከገ በኋላ ጨምሯል። እስከዚያው ድረስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከአንድ ወር በላይ መኖሪያቸው በሆነው ሆስፒታል የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ማከናወን ቀጥለዋል።