ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሕዝቡ ለእርሳቸው ስላሳየው ቅርበት አድናቆታቸውን መግለጻቸው ተገለጸ!
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጂሜሊ ሆስፒታል ውስጥ ሁነው ከሕመማቸው በማገገም ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት፣ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ ቅዱስነታቸው ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ የሚያደርጉትን አስተንትኖ ይፋ አድርጓል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው ሕዝቡን ለጸሎታቸው እና ለህክምና አገልግሎት ምስጋናቸውን ገልጸው ቀጣይነት ያለው ጸሎት እንዲደረግላቸው ቅዱስነታቸው ጠይቀዋል። በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ንባብ ላይ በማሰላሰል፣ ሌሎችን በበጎ አድራጎት ተግባር የመጎብኘት እና ሁልጊዜም በመልካም የመናገርን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥው ገልጸዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሆስፒታል ህክምናቸውን ሲቀጥሉ ባዘጋጁት እና በቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ባሳተሙት የመልአከ ሰላም መልእክት፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምእመናንን የ"ጤና እክል በገጠማቸው" ጊዜ ስላሳዩት ቅርበት አመስግነው ለእርሳቸው እንደሚጸልዩ ሁሉ ለዓለምም ሰላም መጸለይን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
“ከዚህ፣ ጦርነት የበለጠ ግራ የምያጋባ ይመስላል” በማለት በተለይ “ለተሰቃዩት ዩክሬን፣ ፍልስጤም፣ እስራኤል፣ ሊባኖስ፣ ምያንማር፣ ሱዳን እና ኪቩ” ጸሎቶች እንዲደረጉ ጠይቀዋል።
ለጸሎቶች እና ለቅርበታቸው የቀረበ መስጋና
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለዶክተሮች እና የጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች "ስለሚንከባከቡኝ ትኩረት ስለሰጡኝ" በማለት ምስጋናቸውን ገልፀው በሕመማቸው ውስጥ ስላለው የተደበቀ ጸጋ አንፀባርቀዋል ። "በጌታ ለመታመን የበለጠ የምንማረው በእነዚህ ጊዜያት ነው፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ የበርካታ የታመሙ እና የሚሰቃዩ ሰዎችን ሁኔታ በአካል እና በመንፈስ ለመካፈል እድል ስለሰጠኝ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ" ብሏል።
በመጨረሻም፣ በመላው አለም ከሚገኙ ምእመናን ልብ ለሚነሱት ጸሎቶች ያላቸውን ጥልቅ አድናቆት ገልጿል። "ሁሌም የእናንተ ፍቅር እና ቅርበት ይሰማኛል፣ እናም በዚህ ልዩ ጊዜ፣ ‘ሸክም የሆንኩኝ’ እና በሁሉም የእግዚአብሔር ሰዎች የተደገፉክኝ ያህል ይሰማኛል። ሁላችሁንም አመሰግናለሁ!” ብለዋል ቅዱስነታቸው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእለቱ ወንጌል ላይ ወደማሰላሰል ከመግባታቸው በፊት ለምእመናን እርሳቸውም ጸሎታቸውን እንደምያደርጉ አረጋግጠዋል። "እኔም ለአንተ እጸልያለሁ፣ እና ከሁሉም በላይ ስለ ሰላም እጸልያለሁ" ብለዋል።
ከዚያም ከአምስቱ የስሜት ሕዋሶቻችን ሁለቱን ማለትም እይታ እና ጣዕም የሚያጎላውን በዚህ የእሁድ ወንጌል ላይ እንዲያሰላስሉ ምዕመናንን ገብዘዋል።
ዓይኖቻችንን ማሰልጠን
እይታን በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኢየሱስ "ዓለምን በመልካም እንድንመለከት ዓይኖቻችንን እንድናሰልጥንና ባልንጀራችንን በበጎ አድርጎት ተግባር እንድንደግፍ" እንደጠየቀን ገልጿል። ከውግዘት ይልቅ መተሳሰብ ብቻ የወንድማማችነት እርማት እውነተኛ በጎነት እንዲሆን የሚፈቅድ መሆኑን አጽንኦት ሰጥው ገልጸዋል። ምክንያቱም ወንድማማችነት ማለት አንዱ አንዱን ማረም እንጂ ማውገዝ አይደለም! በማለት አክለው ገልጸዋል።
በጥንቃቄ መናገር
ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "ጣዕም" ወደ ሚለው ቃል ሐሳባቸውን ዘወር አድርገው እንደ ተናገሩት እያንዳንዱ ዛፍ በፍሬው እንደሚታወቅ የሚገልጸውን የኢየሱስን ትምህርት አስታውሰዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ከሰው የሚመጡ ፍሬዎች፣ ለምሳሌ በከንፈሮቹ ላይ የሚበስሉ ቃላቶቹ ናቸው" ያሉ ሲሆን በመቀጠልም “በከንፈሮቻችን ላይ የሚበስሉትን ፍሬዎችን” - ጨካኝ ፣ ሀሰተኛ እና ጸያፍ ቃላትን - ከ “ጥሩ ፍሬዎች” - ፍትሃዊ እና ታማኝ ቃላት ጋር ለውይይታችን ጣዕም የሚሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም በእነዚህ ሁለት ገጽታዎች ላይ በማሰላሰል ጳጳሱ ምእመናን የራሳቸውን ሕይወት እንዲመረምሩ ጋብዟቸዋል፥ "ወንድሞቼ እና እህቶቼ የሆኑትን ሌሎች ሰዎችን እንዴት እመለከታለሁ? እናም ስለሌሎች ሰዎች ምን ይሰማኛል? ቃሎቼ ጥሩ ጣዕም አላቸው ወይንስ በምሬት እና በከንቱነት የተሞሉ ናቸው?" የሚሉትን ጥያቄዎች እያንዳንዳችን እንድንጠይቅ ከጋበዙን በኋላ ቅዱስነታቸው አስተንትኖዋቸውን አጠናቀዋል።