MAP

ባዶ የሆነው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እና ከአለም ሕዝብ ጋር ግንኙነት ያላቸው እረኛ

የቫቲካን ዜና የአርትኾት ክፍል አላፊ የሆኑት አቶ አንድሪያ ቶርኔሊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ በነበረበት እ.አ.አ መጋቢት 27/2020 ዓ.ም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ታሪካዊ 'ስታቲዮ ኦርቢስ' (በላቲን ቋንቋ "ስታቲዮ ኦርቢስ"  'የዓለም ጣቢያ' ማለት ሲሆን የጸሎት ዝግጅትን በተለይም ቅዳሴን የሚያመለክት ነው፣ ይህም የቤተክርስቲያን መሰባሰብ እና አንድነትን የሚያመለክት ሲሆን ይህም ብዙ ጊዜ በሊቀ ጳጳሱ ወይም በተወካዩ ይመራል) ጸሎት አምስተኛ ዓመት ላይ ያሰላስላሉ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ፊት ለፊት ላይ ብቻቸውን ጠቀምጠው ጸሎት ካደረጉ እነሆ አምስት ዓመታት አልፈዋል። በወቅቱ ምሽት ላይ ዝናብ እየዘነበ ነበር።

ምንም እንኳን በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እርሳቸውን የሚከታተሉት በቴሌቪዥኖቻቸው እስክሪን ላይ ሆነው ሲሆን አሁንም ሕዝቡ በወቅቱ በኮቪድ 19 ምክንያት በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ለረጅም ጊዜ በኳራንቲን ውስጥ ተቆልፈው ነበር፣ ብዙ ተጎጂዎችን እያጠቃ ባለው የማይታየውን ቫይረስ በመፍራት ፣ ዘመዶቻቸው ሊያዩዋቸው ፣ ሰላምታ ሊሏቸው ወይም የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ሳያደርጉ ወደ ሆስፒታሎች ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍሎች እየወሰዳቸው ቢሆንም በወቅቱ የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚያስደንቅ ሁኔታ ባዶ ነበር ።

በዚያ ምልክት፣ በዚያ ጸሎት እና በቅድስት ማርታ ጸሎት ቤት በየዕለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ በቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ ይቀረብ ነበረ። በፀደይ መጀመሪያ ላይ ለደረሰው አስከፊ የአየር ጠባይ በመጋለጣቸው ምክንያት የሚያለቅስ በሚመስለው የመስቀሉን እግር በመሳም በቅዱስ ቁርባን ቡራኬ ሁሉንም በአደባባዩ ባዶነት አቀፋቸው።

"ከሰዎች ጋር ተገናኝቼ ነበር። በማንኛውም ጊዜ ብቻዬን አልነበርኩም" ጳጳሱ በወቅቱ እንደ ተናገሩት። ብቻቸውን የነበሩ ሲሆን ነገር ግን ብቻዬን አልነበርኩም ሲሉ በመንፈስ ከብዙ ሰዎች ጋር እንደ ነበሩ ተናግረው ነበር። በወረርሽኙ እየጠፋ ለነበረው አለም በመጸልይ ላይ ነበሩ።  የጵጵስና ስልጣናቸውን የሚያመለክት ኃይለኛ የማይረሳ ምስል ነበር።

በዚያ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እግዚአብሔርን እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፡- “ይህን የፈተና ጊዜ የምንመርጥበት ጊዜ አድርገን እንድንይዘው እየጠራህን ነው። ጊዜው የምትፈርድበት ጊዜ ሳይሆን የእኛ የፍርድ ጊዜ ነው፤ ጉዳዩን የምንመርጥበትና የሚያልፈውን የማንመርጥበት ጊዜ ነው፣ አስፈላጊ የሆነውን ከማይሆነው የምንለይበት ጊዜ ነው። አንተን፣ ጌታን እና ሌሎችን በተመለከተ ሕይወታችንን ወደ ትክክለኛው መንገድ የምንመልስበት ጊዜ ነው። በሚቀጥሉት ወራቶች ውስጥ ይህ ቀውስ ባለንበት ቦት በጭራሽ አይተወንም። የተሻለ ሁነን እንወጣለን ወይም የከፋ ሁኔታ ውስጥ ሁነን እንወጣለን" በማለት ተናግረው ነበረ።

ከአምስት አመት በኋላ ዙሪያችንን ስንመለከት እኛ ከአሁን በኋላ በለይቶ ማቆያ ውስጥ አይደለንም እና አሁን ሁኔታው ​​ተቀይሯል፡ አደባባዩ የኢዮቤልዩ በዓልን በሚያከብሩ ሰዎች ተሞልቷል፣ የሮማው ጳጳስ ስለ እኛ እና ስለ ሰላም በቅድስት ማርታ ውስጥ ከሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሆነው ሰላም እንዲሰፍን የሚፀልዩት ከከባድ የሳምባ ምች እያገገሙ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ነው።

ሆኖም ግን ያ ግንኙነት አልተቋረጠም እናም በዚያን ቀን የተናገሯቸው ቃላት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠቃሚ ናቸው፡ ዛሬም ቢሆን በተለይም ዛሬ "የሚገባውን ከማይገባው ነገር ለመምረጥ ጊዜው አሁን ነው"!

27 Mar 2025, 15:10