MAP

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ከምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ወጣት ካህናት እና መነኮሳት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ከምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ወጣት ካህናት እና መነኮሳት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለኦርቶዶክስ ካህናት፡ የኒቂያው ጸሎተ ሃይማኖት ሁሉንም ክርስቲያኖች አንድ ያደርጋ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ወጣት ካህናት እና መነኮሳት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ክርስቲያኖች በአክብሮት እና በወንድማማችነት ፍቅር ላይ ያለንን የጋራ እምነት እንድንገልጽ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"የጋራ እምነታችን ማወጅ ከምንም ነገር በፊት እርስ በርስ መዋደድን ይጠይቃል" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን የተናገሩት ሐሙስ ዕለት ጥር 29/2025 ዓ.ም በሮም ባደረጉት የጥናት ጉብኝት ላይ ከተሳተፉት የኦርቶዶክስ ቀሳውስት ልዑካን ጋር ሲገናኙ ያንን ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

የክርስቲያን አንድነትን ለማራመድ ጠንክሮ የሚሰራው ጳጳሳዊ ጽኃፈት ቤት አማካይነት የተዘጋጀው አምስተኛው የጥናት ቡድን ጉብኝት ከአርመን፣ ከኮፕቲክ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ፣ ከማላንካራ እና ከሶሪያ የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትና መነኮሳትን አሰባስቦ ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ለቡድኑ ባቀረቡት ሰላምታ፣ አመታዊ ጉብኝቱን “የስጦታ መለዋወጥ” ብለው ጠርተውታል፣ ይህም ሥነ-መለኮታዊ ውይይት ከበጎ አድራጎት ውይይት ጋር አብሮ እንዲሄድ ይረዳል ብለዋል።

ዘንድሮ የመጀመርያው የክርስቲያኖች ጉባኤ የሆነው የኒቂያ ጉባኤ ከተካሄደ 1,700ኛ ዓመት የሞላው ሲሆን በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ የእምነት ምልክት የሆነውን የኒቂያን የሃይማኖት መግለጫ ወይም ጸሎተ ሃይማኖት የዘጋጀበት አመት መሆኑን ጠቁመዋል።

የክርስትና እምነት ‘ምልክት’

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የኒቂያን የሃይማኖት መግለጫ ወይም ጸሎተ ሃይማኖት በማመልከት "ምልክት" የሚለውን ቃል ትርጉም መርምረዋል።

በሥነ-መለኮት ደረጃ፣ የሃይማኖት መግለጫው “የክርስትና እምነት ዋና ዋና እውነቶችን ስብስብ ያስቀምጣል፣ እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው” ብሏል።

የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ወይም ጸሎተ ሃይማኖት፣ በቤተክርስቲያኗ የተፈጠረ የመጀመሪያው የሃማኖት መግለጫ ወይም ጸሎተ ሃይማኖት ምልክት ነው፣ ስለዚህም “አብነት ያለው እና ወደር የለሽ” ነበር ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት የሃይማኖት መግለጫው ወይም ጸሎተ ሃይማኖት እውነትንም ሆነ አማኞችን እንደ አንድ ክርስቲያን ሕዝብ አንድ ስለሚያደርግ፣ ለቤተ ክህነት ጠቀሜታ አለው" ያሉ ሲሆን "በጥንት ጊዜ፣ የግሪክ ቃል 'ሲምቦን' የሚለው ቃል በግማሽ የተከፈለውን ሰነድ የማንነት ምልክት ሆኖ እንዲቀርብ ይጠቁማል ብለው

ጳጳሱ አክለው እያንዳንዱ ክርስቲያን የምልክቱ አንድ ክፍል አለው፣ ይህም ሙሉ በሙሉ ሊገለጽ የሚችለው ከሌሎቹ ክፍሎች ጋር ሙሉ በሙሉ ሲዋሃድ ብቻ ነው፣ በኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ወይም ጸሎተ ሃይማኖት የመጀመሪያ የብዙ ቁጥር መልክ ያለው ነው፣ ይህም “እናምናለን” የሚለው ቃል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

“ይህን ምስል አንድ ደረጃ ከፍ አድርገን ስንይዝ፣ አሁንም የተከፋፈልን ክርስቲያኖች፣ የአንድን እምነት በመግለጽ አንድነታችንን ማደስ እንዳለብን ጥሪ አቀባለሁ ብለዋል።

የክርስቲያን አንድነት የወንድማማች ፍቅር ይፈልጋል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዋናነት ክርስቲያኖችን ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርጋቸው የምስጋና ጸሎት መሆኑን በማስታወስ የእምነት ምልክት መንፈሳዊ ጠቀሜታ ላይ አሰላሰሉ።

“ከአምላክ ጋር ያለን አንድነት አንድ ዓይነት እምነት በምንሰብክ ክርስቲያኖች መካከል አንድ መሆን የግድ ነው” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ክርስቲያኖች የኒቂያን የሃይማኖት መግለጫ ወይም ጸሎተ ሃይማኖት በማወጅ እምነታችንን በምንገልጽበት ጊዜ ከማንኛውም ባህል ካላቸው ክርስቲያኖች ጋር አንድነት እንዲሰማቸው አሳስበዋል።

የምስራቃዊው አብያተ ክርስቲያናት የስርዓተ አምልኮ የሃይማኖት መግለጫ ወይም ጸሎተ ሃይማኖት መግቢያ ሐረግ እንዳለው ጠቁመዋል፡- “እርስ በርሳችን እንዋደድ፣ በመንፈስም አንድነት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ማመንን እንናገር" እንደ ሚል ጠቁመዋል።

በማጠቃለያውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኦርቶዶክስ ካህናት እና መነኮሳት የጥናት ቡድን ጉብኝት ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ወደ ጸሎት ወደ ሙሉ አንድነት ስትጓዝ የኅብረት “ምልክት” እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

07 Feb 2025, 11:54