ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቤተሰብ ውስጥ ትርጉም ያለው ጸሎት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅዳሜ ዕለት የካቲት 01/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ለሁለተኛው ዓለም አቀፍ የማኅበረ ቅዱሳን እና የተወዳጅ አምልኮዎች ኮንግረስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንደተናገሩት የፍቅር የልብ ትርታ ምት ሁሌም በሥራችሁ ውስጥ ይሁን ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን የጀመሩት እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 4-8 ቀን 2024 ዓ.ም በሴቪል ስፔን የተካሄደውን የኮንግረሱ ኮሚቴ በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት ምዕመናን በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ለጉባኤያቸው እግዚአብሔርን ለማመስገን መምጣታቸውን አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በንግግራቸው በስብሰባው ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ያቀረቡላቸውን ጥሪ እና ግብዣ በማስታወስ “ወደ እግዚአብሔርና ወደ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሐሳቦቻችንን ስናደርግ ምድራዊ ጉዟችንን የሚያጅብ” የምስጋና ጸሎት በማስታወስ “ያበደ፣ በፍቅር ያበደ እስኪመስል ድረስ ለሚፈሰው ፍቅር ምስክሮች ይሆኑ ዘንድ” ጠይቀዋል።
ልባዊ ጸሎት
“የፍቅር የልብ ትርታ ሁል ጊዜ በዚህ ሥራ ይሰማ” በማለት ቅዱስ አባታችን ገልፀውታል።
ከዚህ አንፃር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሰብአዊ ክብርን ለማሳደግ እና ሌሎችን ለመንከባከብ በሚያደርጉት ጥረት አበረታቷቸዋል።
በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኢየሱስ እንዲባርካቸው፣ ማርያም እንድትጠብቃቸው ከተማጸኑ በኋላ ለእርሳቸውም ጸሎት እንዲያደርጉ እንግዶቻቸውን ከጠየቁ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጠው ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።