MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢጣሊያ ሳንሬሞ ፌስቲቫል በቪዲያ መልእክት ስያስተላልፉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢጣሊያ ሳንሬሞ ፌስቲቫል በቪዲያ መልእክት ስያስተላልፉ   (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ ሙዚቃ የህዝቦችን አብሮ የመኖር ፍላጎት ያጠናክራል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢጣሊያ ሳንሬሞ ፌስቲቫል ለተገኙ ታዳሚዎች በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ትኩረት ያደረጉት “ሕጻናትን በሚያወድሙ ጦርነቶች” በተሞላው ዓለም ሰላም ለመፍጠር ሙዚቃን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትኩረት በመስጠት በዓለም ሰላም ለመፍጠር ሙዚቃ ያለውን ጠቃሚ ሚና ሲናገሩ ሳንሬሞ በየዓመቱ በሚካሄደው የኢጣሊያ የሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ሙዚቃ ሁሉንም የምያነጋግር ቋንቋ ነው ብለዋል።

ሙዚቃ ሁሉንም የሚናገር ቋንቋ ነው።

በአሪስቶን ቲያትር የበዓሉ አስተናጋጅ እና የስነ-ጥበባት ዳይሬክተር ካርሎ ኮንቲ "አስገራሚ" እንግዳ ለ 75 ኛው የሳንሬሞ ፌስቲቫል መርሃ ግብር ያልተጠቀሰ መልእክት እንደሚያካፍሉ አስታውቀው የነበረ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በቪዲዮ የተቀዳ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ጋር በመቀላቀል ሙዚቃ “የሰላም መሣሪያ” እንዴት እንደሆነ አብራርተዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ሙዚቃ፣ ሁሉም ሕዝቦች በተለያየ መንገድ የሚናገሩት፣ የሁሉንም ሰው ልብ የሚነካ ቋንቋ ነው። ሙዚቃ ህዝቦች አብረው እንዲኖሩ ይረዳል ብለዋል።

ከጳጳሱ መልእክት በኋላ፣ ለዚህ​​ምሳሌ የሚሆን ትርኢት ተካሄዷል—እስራኤላዊው ዘፋኝ ኖኦ እና ፍልስጤማዊቷ ዘፋኝ ሚራ አዋድ በዕብራይስጥ፣ በአረብኛ እና በእንግሊዘኛ በጆን ሌኖን “አይማጂን” የተሰኘ ዜማ አሳይተዋል።

ልጆችን በማዕከሉ ውስጥ ማቆየት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዓለም ዙሪያ እየተካሄደ ያለውን ዓመፅ ትኩረት ሰጥተው ሲናገሩ፣ “መዝፈን የማይችሉ ብዙ ልጆች” እንዳሉ በመግለጽ፣ ዜማ መያዝ ባለመቻላቸው ሳይሆን “በዓለም ላይ ካሉት በርካታ ኢፍትሐዊ ድርጊቶች፣ ከብዙ ጦርነቶችና ከግጭት ሁኔታዎች የተነሳ እያለቀሱና እየተሰቃዩ ስለሆነ ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ጦርነቶች ሕፃናትን ያጠፋሉ” ሲሉ ገልጸው በጣም የሚመኙት “እርስ በርስ የሚጠላሉ ሰዎች ሲጨባበጡ፣ ሲተቃቀፉና በሕይወት፣ በሙዚቃና በዘፈን ሰላም ሲፈጥሩ ማየት ነው” ሲሉ ገልጿል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት የሳንሬሞ ፌስቲቫል ለዚህ ምሳሌ ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ዓመት በሮም ኦሎምፒክ ስታዲየም ለዓለም ሕፃናት ቀን በተዘጋጀው የሳንሬሞ ፌስቲቫል ዝግጅት ላይ መድረኩን መካፈላቸውን አስታውሰው፣ ለዓለም ሕፃናት እንክብካቤም መልእክት አስተላልፈዋል። ክስተቱን “በልባቸው ያቆዩት” “ቆንጆ ጊዜ” ነበር ሲሉ ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቪዲዮ መልእክታቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት ለሁሉም ሰው ሰላምታ በመስጠት እና ሙዚቃ “ልብን ለመስማማት ፣ለአንድነት ደስታ ፣በጋራ ቋንቋ እና ለመግባባት በር ይከፍታል ፣ ለበለጠ ፍትሃዊ እና ወንድማማችነት ዓለም እንድንገባ ያደርገናል” ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

13 Feb 2025, 15:23