MAP

በሮም ከተማ የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል በሮም ከተማ የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለብሮንካይተስ ሕክምና ወደ ጂሜሊ ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የብሮንካይተስ ሕመም ስለተሰማቸው እና አጠቃላይ የሕክምና ምርመራ ለማድረግ በሮም ከተማ ወደ ሚገኘው ጂሜሊ በመባል ወደ ሚታወቀው ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ አጎስቲኖ ጂሜሊ ፖሊክሊኒክ ሆስፒታል እንደገቡ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት አርብ የካቲት 7/2017 ዓ.ም አስታውቋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ብዙ የሕክምና ምርመራዎችን ያደርጋሉ፣ በቀጣይነት የብሮንካይተስ ህመም ሕክምናን ማድረግ እንደ ሚጀምሩ የተገለጸ ሲሆን መግለጫው “ዛሬ ጠዋት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስፈላጊ ለሆኑ የሕክምና ምርመራዎችን እና ለደረሰባቸው ብሮንካይተስ ሕመም የሆስፒታል ሕክምናን ለመቀበል ወደ ሆስፒታል እንደሚገቡ አክሎ ገልጿል።

ቀደም ሲል የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ቅዱስነታቸው የጤና እክል እንደ ገጠማቸው መግለጫ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በብሮንካይተስ ሕመም እየተሰቃዩ መሆናቸውን፣ ታዳሚዎቻቸውን እና እንግዶቻቸውን በቅድስት ማርታ ቤት  በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሆነው ያስተናግዱ እንደ ነበር ማስታወቁ ይታወሳል።

 

14 Feb 2025, 16:31