MAP

በሮም ከተማ የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል በሮም ከተማ የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምሽቱን በሰላም ማሳለፋቸው ተገለጸ!

የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች እሮብ ማለዳ የካቲት 19/2017 ዓ.ም እንዳስታወቀው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ጂመሊ ሆስፒታል ሌላ መልካም ምሽት እንዳሳለፉ እና በሆስፒታል የሚኖራቸው ቆይታ እንደሚቀጥል የገለጸ ሲሆን ህመማቸው አሳሳቢ ቢሆንም የተረጋጋ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን አስታውቋል፣ የብሮካይትስ እና የሳንባ ምች ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነም አስታውሷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ ለጋዜጠኞች ረቡዕ ረፋድ ላይ በሰጠው መግለጫ “ጳጳሱ መልካም  ሌሊት አሳልፈዋል እና እረፍት በማድረግ ላይ ይገኛሉ” ብሏል።

የማክሰኞ ምሽት እየተሻሻለ የመጣው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ  "ክሊኒካዊ ሁኔታ ወሳኝ ቢሆንም የተረጋጋ ነው። ምንም አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት ችግር አልታየባቸውም፣ እናም የሂሞዳይናሚክስ መለኪያዎች የተረጋጋ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ያሳያሉ" ብለዋል።

"በምሽት የሳንባ ምች በሽታዎችን በራዲዮሎጂ ለመከታተል የታቀደውን ሲቲ ስካን አድርገዋል። ትንበያው እንደተጠበቀ ሆኖ "በማለዳ ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ እለታዊ ሥራቸውን ቀጥለዋል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ዓርብ የካቲት 07/2017 ዓ.ም በሮም ውስጥ በሚገኘው አጎስቲኖ ጂመሊ ሆስፒታል የብሮንካይተስ በሽታ መከሰቱን ተከትሎ ስለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጤና ሁኔታ የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት የሚደርገውን መግለጫዎች ምእመናንን ማሳወቅ መቀጠሉ ይታወሳል።

በአሁኑ ጊዜ የብሮካይትስ እና የሳምባ ምች ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው ሳምንት የጤንነት ሁኔታም እንዲሁ መጠነኛ የኩላሊት ችግር ምልክቶች እያሳየ መሆኑን ጠቁሟል ይህም ቁጥጥር እየተደረገበት ነው።

 

 

26 Feb 2025, 15:38