MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሮም በሚገኘው ጀሜሊ ሆስፒታል ድርብ የሳንባ ምች ሕክምና እየተደረገላቸው ነው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሮም በሚገኘው ጀሜሊ ሆስፒታል ድርብ የሳንባ ምች ሕክምና እየተደረገላቸው ነው  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በጀሜሊ ሆስፒታል ዘጠነኛ ሌሊታቸውን በሰላም ማሳለፋቸው ተነገረ

የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም. እሁድ ማለዳ የቅድስት መንበር የጋዜጣዊ መግለጫ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ድርብ የሳምባ ምች ህክምና እያደረጉበት ባለው ሮም በሚገኘው ጀሜሊ ሆስፒታል ዘጠነኛ ሌሊታቸውን በሰላም ማሳለፋቸውን ገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ጽህፈት ቤቱ እሁድ ጠዋት ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሌሊቱን በሆስፒታል ውስጥ በሰላም ማሳለፋቸውን በመግለጽ፥ ቅዱስ አባታችን ሮም በሚገኘው ጀሜሊ ሆስፒታል በአሁኑ ወቅት ድርብ የሳንባ ምች ህክምናን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ለጋዜጠኞቹ ይፋ አድርጓል።

ከዚህም በተጨማሪ ጋዜጣዊ መግለጫው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፍተኛ ፍሰት ያለው ኦክሲጅንን ለመቆጣጠር በአፍንጫ የሚገቡ ቱቦዎች እንደተገጠሙላቸው እና ሌሎች ክሊኒካዊ ሙከራዎች በመካሄድ ላይ እንደሆኑ የገለጸ ሲሆን፥ በዚህ ምሽት የሚወጣው የህክምና መረጃ ውጤት የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን ብሏል።
 

23 Feb 2025, 13:50