MAP

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የእግዚአብሔር ፍቅር ደፋር ምስክሮች ሁኑ ማለታቸው ተገለጸ!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ የካቲት 02/2017 ዓ.ም የጦር ሰራዊት ኢዮቤልዩ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት ወደ እርሱ ማለትም ወደ እግዚአብሔር አዘውትረው በጸሎት መንፈስ መመለሳቸው ለአስፈላጊ ተግባራቸው የብርታት ምንጭ መሆኑን በማስታወስ ጥረታቸውን ለክርስቶስ አደራ ሰጥተዋል። “እንደ ክርስቶስ መገኘት በመካከላችሁ ናቸው” በማለት ለጦር ሰራዊቱ የሐዋርያዊ እንክብካቤ የሚያደርጉትን አጃቢ የሆኑትን ካህናት ተግባር አወድሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"የእግዚአብሔር የአባታችንን ፍቅር ምስክሮች ሁኑ..."

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ዕለት ለጦር ኃይሎች፣ ለፖሊስ እና ለደህንነት አባላት በኢዮቤልዩ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ሐይቅ ላይ ያደረገውን የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ስብከት በማሰላሰል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሦስት መንገዶች እንደሚከፋፈል አመላክተው፣ እነዚህም ተመለከተ፣ ተሳፈረ እና ተቀመጠ የሚሉት እንደ ሆኑ ገልጸዋል።

ሁሉም ነገር የጠፋ በሚመስልበት ጊዜ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ተስፋ ይጸናል

በመጀመሪያ ደረጃ፣ ጳጳሱ ኢየሱስ በብዙ ሰዎች መካከል እንኳ ሁለቱ ጀልባዎች ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲቃረቡ “አይቷል” በማለት ገልጿል፤ በእነዚያ ዓሣ አጥማጆች ፊት ላይ የታዩትን የተስፋ መቁረጥ ስሜት፣ ፍሬ አልባ ድካም በሌሊት ካደረጉ በኋላ ባዶ መረባቸውን እያጠቡ ነው። ኢየሱስ ዓይናቸውን ተመልክቶ እንዴት እንደሚራራላቸው ጠቁመዋል። እዚህ ላይ በኢየሱስ አሳቢነት እንደምንመለከተው የእግዚአብሔርን ቅርበት፣ ርኅራኄ እና ምሕረት ሁልጊዜ መርሳት የለብንም በማለት አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእዚህ ሰሞን በብሮንካይት በሽታ በመያዛቸው እና ትንሽ የትንፋሽ ችግር ስለገጠማቸው  ሊቀ ጳጳስ ዲያጎ ራቬሊ ስብከታቸውን እንዲያነቡ ጠይቀው ነበር፣ በዚህ መሰረት ስበከታቸውን በንባብ መልክ ያቀረቡት ሊቀ ጳጳስ ዲያጎ እንደ ነበሩ ተገልጿል።

በሁለተኛ ደረጃ፣ ተስፋ የቆረጡበትን ሁኔታ የተመለከቱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስብከታቸው ውስጥ፣ ወደ ስምዖን ሕይወት ለመግባት እና የከንቱነትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜቱ ለመካፈል፣ ከባሕር ዳርቻ ትንሽ መንገድ እንዲወጣ ካደርገው በኋላ በጀልባው ላይ ለመውጣት ኢየሱስ ስምዖንን እንዴት እንደጠየቀ አስታውሰዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኢየሱስ ከስምዖን ጋር ያደርገው ግንኙነት እጅግ ወሳኝ እንደ ነበረ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ይህ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

ኢየሱስ “ብዙ ጊዜ እንደምናደርገው ሁሉ ነገሮች እየተበላሹ ሲሄዱ ዝም ብሎ አይመለከትም፣ ከዚያም በቁጭት አያጉረመርምም። ይልቁንም ቅድሚያውን በመውሰድ ወደ ስምዖን ቀርቦ በዚያ አስቸጋሪ ጊዜ ከእርሱ ጋር ጊዜ አሳልፎ በዚያ ምሽት በችግር የተሞላ በሚመስል የሕይወት ጀልባ ለመሳፈር መረጠ” ብሏል።

ሦስተኛ፣ ቅዱስ አባታችን አስተንትኖ ይሆን ዘንድ ያቀረቡት ሐሳብ ኢየሱስ በጀልባ ላይ ተሳፍሮ ከነበረ በኋላ ተቀምጦ ያስተምር እንደነበር ጠቁመዋል።

ኢየሱስ “እነዚያን የዓሣ አጥማጆች ዓይንና ልብ እያየ፣ ፍሬ አልባ ድካም የሚኖሩበትን ሌሊት ብስጭት እያየ፣ ምሥራቹን ለመስበክ፣ በጨለማው ውስጥ ለነበረው የብስጭት ሌሊት ብርሃን ለመስጠት፣ በሕይወት ትግል ውስጥም እንኳ የእግዚአብሔርን ውበት ለመናገር በጀልባ ተሳፍሯል፣ እናም ሁሉም የጠፉ በሚመስሉበት ጊዜም እንኳ ተስፋ እንደሚጸና ያረጋግጣል” ብሏል።

ተአምር ይከሰታል

"ጌታ በሕይወታችን ጀልባ ውስጥ ሲገባ ዘወትር የሚሸኘን እና የሚደግፈንን የእግዚአብሔርን ፍቅር የምሥራች ሲያበስርልን፣ እንግዲያውስ ሕይወት በአዲስ መልክ ይጀምራል፣ ተስፋ ዳግም ይወለዳል፣ ጉጉታችንን ያድሳል፣ እናም መረቦቻችንን እንደገና ወደ ባሕር መጣል እንችላለን" ብለዋል።

ይህ የተስፋ መልእክት ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፖሊስ እና የጸጥታ አካላት ኢዮቤልዩ ሲያከብሩ አብሮ እንደሚጓዝ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውቀዋል።

በዚህ መንፈስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሥፍራው ለተገኙት ሁሉም ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ ማኅበራት እና አካዳሚዎች፣ ወታደራዊ ሰራዊት እና ለእነርሱ ሐዋርያዊ እንክብካቤ የምያደርጉ ካህናት ሰላምታ ሲሰጡ ስላደረጉት አገልግሎት አመስግነዋል።

መለያችሁ ጉብዝናችሁ ነው

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሁላችሁም በርካታ የማኅበራዊ እና የፖለቲካ ሕይወቶችን የሚያካትት የላቀ ተልእኮ ተሰጥቶአችኋል፤ አገሮቻችንን የመጠበቅ፣ ደህንነትን የማስጠበቅ፣ ሕጋዊነትና ፍትህን የማስከበር አደራ ተሰጥቷችኋል ያሉ ሲሆን "ምክንያቱም መለያ ልብሳችሁ (ዩኒፎርም)፣ የተቀረፃችሁበትን ስነ-ስርዓት (ዲሲፕሊን) ያሳያል፣ ድፍረታችሁ መለያችሁ ነው፣ የገባችሁት መሃላ - ይህ ሁሉ ነገር ክፉውን ለመዘገብ ክፉን ማየት ብቻ ሳይሆን አውሎ ነፋሱ በተናወጠችው ጀልባ ተሳፍረው እንዳትወድቅ ለማድረግ መስራት አስፈላጊ መሆኑን የሚያስታውሱ ናቸው" ብለዋል።

በመጨረሻም ሊቀ ጳጳሱ፣ “በከተማችንና በየአካባቢያችን መገኘታችሁ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር መሥራታችሁ፣ እናንተም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን መጠበቃችሁ ለሁላችን ትምህርት ይሆናልና” በማለት “በሁሉም ነገር ላይ መልካምነት ማንጸባረቅ ይገባል” በማለት ገልጸዋል።  

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ሕይወታቸውን በሙሉ የሚያቅፍ ሥራቸውን ሲያከናውኑ፣ ለእነርሱ ሐዋርያዊ እንክብካቤ የምያደርጉ ካህናት ጋር በመሆን፣ “በመካከላችሁ አስፈላጊ የሆነ የካህን መገኘት” ተቃሚ መሆኑን አስታውሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሥራቸው - አንዳንድ ጊዜ በሚያሳዝን ሁኔታ በታሪክ እንደተፈጸመው - ጠማማ የጦርነት ድርጊቶችን መባረክ አይደለም” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ይልቁንም፣ “ከእናንተ ጎን ሊሄድ የሚወድ የክርስቶስ መገኘት በመካከላችሁ አስፈላጊ ነው፣ የምያዳምጥ እና የሚራራ ጆሮ እንዲኖራችሁ ሊያቀርቡላችሁ፣ በአዲስ መልክ ወደ ፊት እንድትሄዱ ለማበረታታት እና በእለት ተእለት አገልግሎታችሁ እንዲደግፋችሁ” ሐዋርያዊ እንክብካቤ የምያደርጉ ካህናት በመካከላችሁ መገኘታቸው አስፈላጊ ነው ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አክለው እንደ ገለጹት የሞራልና የመንፈሳዊ ድጋፍ ምንጭ እንደመሆናቸው መጠን፣ “በእያንዳንዱ እርምጃ አብራችሁ ተልእኮአችሁን ከወንጌል አንጻርና ለጋራ ጥቅም ማስከበር ይርዳችሁ” በማለት የሐዋርያዊ እንክብካቤ የሚሰጡ ካህናትን ጥቅም ተናግረዋል።

ምስጋና፣ ንቃት እና ትልቅ የግል ስጋት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለምታደርጉት ነገር አመስጋኞች ነን፣ አንዳንድ ጊዜ በአገልግሎታችሁ ምክንያት ሕይወታችሁ በግል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል" በማለት ለምያከናውኑት አገልግሎት “እናመሰግናለን ምክንያቱም በማዕበል በተናወጠው ጀልባዎቻችን ላይ በመሳፈር ከለላ ስለምትሰጡን እና በአቅጣጫችን ላይ መጓዝ እንድንቀጥል ስለምታደርጉን በድጋሚ እናመሰግናለን" ብለዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የአገልግሎታችሁን አላማ እና ሁሉንም ተግባሮቻችሁን ፈጽሞ እንዳይዘነጉ፣ ይህም ህይወትን ማራመድ፣ ህይወትን ማዳን፣ የህይወት የማያቋርጥ ተከላካይ መሆን ነው ተግባራችሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

"የጦርነት መንፈስን ለማዳበር ለሚደረገው ፈተና ለመቋቋም ንቁ ሁኑ። በስልጣን ቅዠትና በጦር መሳሪያ ጩኸት እንዳትወሰድ ተጠንቀቁ" ያሉ ሲሆን አክለውም "ጥላቻን በሚያሰርጽ ፕሮፓጋንዳ እንዳትመረዙ፣ ዓለም ወዳጅ እንዲሆን እንጂ እንዲዋጉ ጠላት እንዳይሆኑ ነቅታችሁ ጠብቁ" ብለዋል።

ይልቁንም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት ከሆነ “ሁላችንም ወንድማማቾች እና እህተማማቾች እንድንሆን ለሚፈልገው የእግዚአብሔር አባታችን ፍቅር ደፋር ምስክሮች እንሁን” በማለት ያበረታቱ ሲሆን  “እንግዲህ አብረን የሰላም፣ የፍትህ እና የወንድማማችነት የአዲስ ዘመን የእደ ጥበብ ባለሞያዎች ለመሆን እንነሳ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።  

10 Feb 2025, 13:09