የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ ባለበት እንደ ሆነ ተገለጸ!
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያመለክተው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሌሊቱን ሙሉ ጥሩ እረፍት ማድረጋቸውን የገለጸ ሲሆን ቅዱስ አባታችን በሮም ጂሜሊ ሆስፒታል የብሮንካይተስ እና የሳንባ ምች በሽታ ሕመም ስለደረሰባቸው በሕክምና ላይ መሆናቸው ይታወቃል፣ ከባለፈው ሳምንት የተሻሻለው የጤና ሁኔታቸው እንዲሁ በቁጥጥር ሥር ሊውል የሚችል መጠነኛ የኩላሊት ሕመም ምልክቶች እያሳየ መሆኑን ጠቁሟል።
የሰኞ ምሽት መግለጫ የጳጳሱ ሁኔታ ከባድ ቢሆንም ትንሽ መሻሻል አሳይቷል በማለት የገለጸ ሲሆን “[ሰኞ] አስም የሚመስል የመተንፈስ ችግር አልተከሰተም፣ እናም አንዳንድ የላብራቶሪ ምርመራዎች መሻሻል አሳይተዋል። መለስተኛ የኩላሊት ሕመም ችግር ላይ የተደረገው ክትትል ምንም የሚያሳስብ ነገር የለውም። ምንም እንኳን በመተንፈሻ መሳርያ ድጋፍ ይደረግ የነበረው ፈጣን የሆነ የኦክሲጅን ድጋፍ በትንሹ ቢቀንስም በኦክስጂን ድጋፍ የሚደርገው ሕክምና ይቀጥላል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።
መግለጫው ዶክተሮች “ከክሊኒካዊው ምስል ውስብስብነት አንፃር ጥንቃቄ የተሞላበት” ትንበያ እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግሯል ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰኞ ማለዳ ቅዱስ ቁርባን መቀበላቸውንና ከሰአት በኋላም ሥራቸውን እንደቀጠሉ የፕሬስ ቢሮው ገልጿል።
እንደተለመደው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጋዛ የሚገኘውን የቅዱስ ቤተሰብ ደብር ቆመስ ደውለው በዚያ ላሉ ሰዎች ያላቸውን የአባታዊ ቅርርብ ገልጸው ነበር፣ የቁምስናው ህዝብ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቪዲዮ መልእክት እንደላኩ የሚገልጹ ዘገባዎች የወጡ ሲሆን፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም በስልክ ባደረጉት ጥሪ አመስግነዋል።