ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለዲፕሎማቲክ አባላት ‘የተስፋ ዲፕሎማሲ’ ሐሳብ አቅርበዋል!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጥር 01/2017 ዓ.ም ሐሙስ ዕለት ለዲፕሎማቲክ ቡድን አባላት በተወካያቸው በኩል ባደረጉት አመታዊ ንግግር በእውነት፣ በይቅርታ፣ በነጻነት እና በፍትህ ላይ የተመሰረተ ‘የተስፋ ዲፕሎማሲ’ ራዕያቸውን አቅርበዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተወካያቸው እና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናትን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ፊሊፖ ሢያምፓኔሊ በኩል ባስተላለፉት መልእክት የኢዮቤልዩ ዓመት ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ጠቀሜታ በመግለጽ እያንዳንዳችን “በእርግጥ አስፈላጊ የሆነውን ነገር” እንደገና እንድናገኝ ይጠራናል ብለዋል።
እ.አ.አ. በ 2025 ዓ.ም ወደ ዘላለማዊቷ ከተማ የሚጓዙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናንን ለመቀበል የሮማ ከተማን ለማዘጋጀት ላደረጉት ጥረት ለጣሊያን ባለስልጣናት ምስጋናቸውን ገልፀዋል ።
አመቱ ሲጀምር ዓለማችን በብዙ ግጭቶች፣ በሽብር ድርጊቶች፣ በህብረተሰቡ አለመግባባቶች እና ሰዎችን በሚከፋፍሉ አዳዲስ እንቅፋቶች ስትታመስ እናገኛታለን ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሁሉም ሰዎች “የግጭት አመክንዮ”ን ወደ ጎን እንዲተው እና ይልቁንም “የመገናኘት አመክንዮ እንዲቀበሉ ጋብዟቸዋል፣ ስለዚህም መጪው ጊዜ ተስፋ በሌለው መንገድ ዳር ሆኖ እንዳያገኘን፣ ነገር ግን እንደ ተስፋ ተጓዦች፣ ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ፣ በቁርጠኝነት ወደፊት እንድንገፋ። የወደፊት ሰላም መገንባት የሚሳተፉ ሰዎች ሆኖ እንዲያገኘን" ሲሉ ተናግረዋል።
የተስፋ ዲፕሎማሲ በእውነት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተወካያቸው አማካይነት ያስተላለፉትን መልእክት በመቀጠል፣ “በአዲስ የሰላም ንፋስ” ጥቅጥቅ ያሉ የጦርነት ደመናዎችን ጠራርጎ የሚወስድበትን “የተስፋ ዲፕሎማሲ” ራዕይ አስቀምጠዋል።
ሁሉም ሰዎች ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው እንደተናገሩት ከሆነ የእውነት ጥማት ተሰጥቷቸዋል፣ እናም ከመከራችን የሚያድነን የሰው ልጅ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጠውን የምስራች ለመስማት ይጓጓል ብለዋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን፣ “በቴክኖሎጂው ፈጣን እድገት ባመጣው ሰፊ የባህል ለውጥ፣ ከንግድ ፍላጎቶች ጋር መጣጣሙ በፍጆታ ላይ የተመሰረተ ባህል እየፈጠረ በመምጣቱ የትኛውም የዓለማችን ጥግ ሳይነካ ይቀራል ማለት አይቻልም ብለዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በምላሹ፣ የተስፋ ዲፕሎማሲ “የእውነት ዲፕሎማሲ” መሆን አለበት፣ ይህም የሰው ልጅ በእውነታው ላይ የቆመ የጋራ ቋንቋ እንዲኖራቸው እውነታን፣ እውነትንና እውቀትን የሚያገናኝ መሆን አለበት።
ቋንቋ በተለይ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውስጥ ጠቃሚ ነው ሲሉ የቃላቶችን ትርጉም ለመቀየር ወይም የሰብአዊ መብት ስምምነቶችን ይዘት በአንድ ወገን እንደገና ለመተርጎም የሚደረገውን ጥረት በቁጭት ገልጸዋል።
በጥንቃቄ በታቀዱ አጀንዳዎች መሠረት የህዝቦችን ወግ፣ ታሪክ እና ሃይማኖታዊ ትስስር ለመንቀል የሚሞክር እውነተኛ የርዕዮተ ዓለም ቅኝ ግዛትን ይወክላል '" ብለዋል።
ይቅርታ ከጥላቻ ለመራቅ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ለተጎጂዎች እንክብካቤ በሚሰጡ መንገዶች በጥላቻ እና በአመጽ የተበላሹ ግንኙነቶችን የሚያስተካክል "የይቅርታ ዲፕሎማሲ" እንዲተገበ ጥሪ አቅርበዋል።
ግጭቶች በንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረሱትን ከፍተኛ ጉዳት በማስታወስ በዩክሬን እና በጋዛ ያለውን ጦርነት እንዲያቆም የአለም ማህበረሰብ ተማጽኗል።
አክለውም “በተጨማሪም ጦርነት የሚቀሰቀሰው ይበልጥ የተራቀቁ እና አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች መበራከታቸው ነው” ሲሉ “ጦርነት ሁሌም ውድቀት ነው” ሲሉ ተናግሯል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማያንማር፣ በሱዳን፣ በሳህል፣ በአፍሪካ ቀንድ፣ በሞዛምቢክ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶችን አስታውሰዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄደውን የፀረ-ሴማዊነት መግለጫዎች እና በክርስቲያን ማህበረሰቦች ላይ የሚደርሰውን ስደት አውግዟል።
"የግለሰቦችን ሕሊና ማክበር፣ እምነትን እና የአንድን ማህበረሰብ አባልነት በአደባባይ መግለጽ የሚቻልበት የእምነት ነፃነት ዋስትና ከሌለ እውነተኛ ሰላም ሊኖር አይችልም" ብሏል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለወደፊት ለሶሪያ ተስፋ ያላቸውን እምነት በመግለጽ ሁሉም ሶርያውያን ክርስቲያኖችን ጨምሮ መላውን ሕዝብ የጋራ ጥቅም ማሳደግ አለባቸው ብለዋል።
ነፃነት እና ፍትህ ለሰላም መሰረት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የሰዎችን ዝውውር፣ የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት እና ሌሎች የዘመናዊ ባርነት ዓይነቶችን ለማስወገድ የሚጥር “የነፃነት ዲፕሎማሲ” እንዲሰፍን ጠይቀዋል።
ሁሉም ሀገራት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ለሆኑ እና የተሻለ ህይወት ፍለጋ ለሚነሱ ስደተኞች እንክብካቤ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፤ የዜጎችን መፈናቀል መንስኤዎች ለመፍታትም ርብርብ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
የተስፋ ዲፕሎማሲ በተጨማሪም "የፍትህ ዲፕሎማሲ" ነው ብለዋል፣ ያለ ፍትህ ሰላም ሊኖር አይችልም፣ ይህም የኢዮቤልዩ አመት ዕዳን ስረዛ እንዲደረግለት፣ ማህበረሰቡም ሆነ አገራት ከጭንቀት እፎይ የሚሉበትን ሁኔታ መፍጠር ተገቢ ነው ብለዋል።
"ፍትህ ወደነበረበት መመለስ ከሚችሉ መሳሪያዎች መካከል ዛሬ ምንም ምክንያት ስላላገኘ የሞት ቅጣት በእያንዳንዱ ሀገር እንዲወገድ ጥሪዬን በድጋሚ አቀርባለሁ" ብሏል።
ለጋራ ቤት የስነ-ምህዳር ዕዳዎችን መክፈል
በማጠቃለያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጋራ ቤታችን ላይ ያለው የሰው ልጅ ዕዳ በማስታወስ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል አገሮች የገንዘብ ምንጮችን ለመለዋወጥ በሚደረገው ጥረት ሊንከባከቡ ይገባል ብለዋል።
"ከዚህ የስነምህዳር እዳ አንፃር የድሆች ሀገራትን የውጭ ዕዳ ወደ ውጤታማ፣ ፈጠራ እና ኃላፊነት የተሞላበት ፖሊሲ እና የሰው ልጅን ሁለንተናዊ እድገት ለማሳደግ ውጤታማ መንገዶችን መፈለግ አስፈላጊ ነው" ብለዋል ።
የኢዮቤልዩ ዓመት ሲጀመር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅድስት መንበር ዕውቅና ለተሰጣቸው ዲፕሎማቶች፣ በሁሉም ሰዎች ልብ ውስጥ ተስፋ እንዲያብብ፣ የሰላም ምኞታችን እውን ይሆን ዘንድ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።