ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከኮሙኒኬሽን እና ከደህንነት ኃይሎች ጋር ኢዩቤሊዩ እንደምያከብሩ ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በኢዮቤልዩ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በኮሙንኬሽን ዘርፍ ለሚሰሩ፣ ለጦር ኃይሎች፣ ለፖሊስ እና ለደህንነት ሠራተኞች የሚከናወነውን መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ በቫቲካን ረቡዕ ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም የተለቀቀው የሥርዓተ አምልኮ የጊዜ ሰሌዳ አስታውቋል።
ለዓለማችን የኮሙንኬሽን ወይም የመገናኛ ባለሙያዎች ኢዮቤልዩ እ.አ.አ ከጥር 24-26 ይካሄዳል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሦስተኛው መደበኛ እለተ ሰንበት የእግዚአብሔር ቃል እንደ ምያስሙ ከወዲሁ ይጠበቃል።
ከሁለት ሳምንታት በኋላ በአምስተኛው የመደበኛው እለተ ሰንበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጦር ኃይሎች፣ የፖሊስ እና የደኅንነት ሠራተኞች ኢዮቤልዩ ዝግጅት ማጠቃለያ ቅዳሴን ያከብራሉ። ሁለቱም የኢዮቤልዩ ቅዳሴዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ውስጥ ይከናወናሉ።
ለሊቃነ ጳጳሳቱ ለሚቀጥሉት ሳምንታት የወጣው የድርጊት መርሃግብር የጊዜ ሰሌዳ እ.አ.አ በጥር 25/2025 ዓ.ም ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ለውጥ ያመጣበት ቀን የሚታሰብበት በዓል በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ በቅዱስነታቸው መሪነት መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚከናወን እና በጣም አስፈላጊ ለሆኑ በዓላት የአምልኮ ሥርዓቶችን ያካትታል፣ ለክርስቲያናዊ አንድነት የሚደርገው የጸሎት ሳምንት ማጠቃለያ በእዚያው በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ እንደሚከናወን ይጠበቃል።
እ.አ.አ. የካቲት 1፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቀደስ የቀረበበት እለት የሚታሰብበት አመታዊ በዓል የዋዜማ ጸሎት አከባበር በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መሪነት ይከናወናል።
የክብረ በዓሎች የቀን መቁጠሪያ
እ.አ.አ ጥር 25/2025
የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ የምያመልክት አመታዊ በዓል ይከበራል፣
ይህ በዓል በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ የሚከበር ሲሆን በሮም ሰዓት አቆጣጠር አመሻሹ ላይ 5፡30 የዋዜማ ጸሎት ከተካሄደ በኋላ 58ኛው ለክርስቲያኖች ሕብረት የሚደርገው የጸሎት ፕሮግራም ይከናወናል።