ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- 'ክርስቲያናዊ የወንድማማችነት ውይይት ለዛሬው ዓለም ምሳሌ ሊሆን ይችላል' አሉ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የጥንት ትውፊትን ተከትሎ የዛሬው የቁስጥንጥንያው ቅዱስ እንድርያስ የሐዋርያውየቅዱስ እንድርያስ በዓል ምክንያት በማድረግ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ኢስታንቡል ልከው ሰላምታና “ወንድማዊ ፍቅራቸውን” ለቁስጥንጥኒያ ቅዱስ ፓትርያርክ ለሆኑት ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ የሰላምታ መልእክታቸውን መላካቸው ተገልጿል።
ጉብኝቱ በቅድስት መንበር እና በመንበረ ፓትርያርክ መካከል በየአመቱ የሚካሄደው የልዑካን ቡድን ልውውጥ አካል የሆነ ሲሆን እ.አ.አ በሰኔ 29 ቀን በሮም ፣ የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በዓል ሲከበርና እንዲሁም በተጨማሪ እ.አ.አ በህዳር 30 ቀን በኢስታንቡል ፣ ቱርኪ የቅዱስ እንድሪያ በዓል ሲከበር የሚደረግ ልውውጥ ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልእክታቸው፣ በካቶሊኮችና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መካከል ያለው አንድነት ወደ ሕብረት ለማምጣት ቀዳሚ መንገድ መሆኑን ጠቅሰው መደማመጥን አጉልተው ገልጸው፣ በቅርቡ የሚከበረው 1,700ኛው የመጀመሪያው የኒቂያ የክርስቲያናዊ ሕበርት ጉባኤ የምስረታ በዓል የነበራቸውን ወንድማማችነት ግንኙነት ለማጠናከር ዕድል እንደሚሰጥ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የ 60 ዓመታት ፍሬያማ ውይይት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክቱን የጀመሩት እ.አ.አ በ1964 ዓ.ም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በይፋ ወደ ኢኩሜኒካል ወይም ክርስቲያናዊ ሕበረት እንቅስቃሴ መግባቷን የሚያሳየውን በላቲን ቋንቋ 'Unitatis Redintegratio' (የአንድነት ዳግም ውህደት) አዋጅ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የካቶሊክ - የኦርቶዶክስ ውይይት ከፍተኛ እድገት በማሳየት ላይ እንደ ሚገኝ ይታወቃል።
በዚህ ውይይት ውስጥ ከተገኙት የመጀመሪያ ፍሬዎች መካከል አንዱ በዛሬው ጊዜ የሚያገኙት “በተለይ የታደሰ ወንድማማችነት” እንደሆነ ተናግሯል።
የሙሉ ውህደት ጠቅላላ ግብ
“ከሺህ ዓመት በፊት ጀምሮ የነበረው ልዩነት በጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ሊፈታ ስለማይችል፣ በኮንሲሊያር ሰነድ የታሰበው ሙሉ ውህደት ገና እንዳልተሳካ ቢገነዘቡም፣ ጳጳሱ ክርስቲያኖች “ይህን የመጨረሻ ግብ አድርገው እንዳያዩት” አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። "ይህ አንድነት በታሪክ ሂደት ውስጥ እና ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ሊገኝ ይችላል" ብለው በማሰብ ተስፋ እንዳይቆርጡ ጠይቀዋል።
"ካቶሊኮች እና ኦርቶዶክሶች መጸለይ ማቆም የለባቸውም፣ ለሕብረት አብረን መሥራት ይኖርብናል፣ በአንድነት ለመለኮታዊ ስጦታ" መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።
ስለ ኢኩሜኒካል ውይይት ሲኖዶሳዊ አቀራረብ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን “የማያዳግም ቁርጠኝነትን በውይይት ጎዳና ላይ መመሥረት” በቅርቡ በተካሄደው ሲኖዶስ ላይ ከተለያዩ ቦታዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች “ሳይፈረድባቸውና ሳይወቅሱ እርስ በርሳቸው መደማመጥ” ላይ ያተኮረ ተግባር መፈጸማቸውን መረጋገጡን አስታውሰዋል።
ይህ አካሄድ “ካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች ወደ አንድነት የሚያደርጉትን ጉዞ የሚቀጥሉበት መንገድ መሆን አለበት” ብሏል።
ክርስቲያናዊ ውይይት ዛሬ ለተከፋፈለው ዓለም አብነት ነው።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልእክታቸው ማጠቃለያ ላይ እ.አ.አ በ2025 የሚከበረው የ1700ኛ ዓመት የኒቂያ የመጀመሪያ ጉባኤ ዝክረ አመት “አሁን ያለውን ትስስር የሚያጠናክር እና ዛሬ ባለው ዓለም ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የታደሰ ምስክርነት እንዲሰጡ የሚያበረታታ ነው” ብለዋል።
በክርስቲያኖች የተሰጠው “የወንድማማችነት መንፈስና ምሥክርነት” “በጦርነትና በዓመፅ ለተመሰቃቀለው ዓለም አርአያ” እንደሚሆን ተናግሯል። በዚህ መንፈስም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዩክሬን፣ በፍልስጤም፣ በእስራኤል ሰላም እንዲሰፍን ያላቸውን ተስፋ በማጽናት ደምድመዋል።