MAP

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት   (Vatican Media)

የጳጳሱ ሳምንታዊ የጠቅላላ አስተምህሮ የቻይናን ማንዳሪን ቋንቋ ሊያካትት መሆኑ ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኅዳር 18/2017 ዓ.ም ባደረጉት ሳምንታዊ የጠቅላላ አስተምህሮ ማብቂያ ላይ እንደ ተናገሩት ከመጪው ኅዳር 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ በማንደሪን ቻይንኛ ቋንቋ ሰላምታ እና የማጠቃለያ ንግግር እንደምያካትቱ አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"በሚቀጥለው ሳምንት፣ በመጀመሪያው የስብከተ ገና ሳምንት መጀመሪያ፣ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማጠቃለያ ወደ ቻይንኛ ቋንቋ ይተረጎማል" ሲሉ ቅዱስነታቸው አስታውቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው የምያደርጉትን ሳምንታዊ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመከታተል በኅዳር 17/2017 ዓ.ም በስፍራው ለተገኙ ታዳሚዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ይህንን አስታውቀዋል።

ከመጪው ሳምንት ኅዳር 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ጳጳሱ ከምያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በኋላ የምያቀርቡት ሰላምታ እና ማጠቃለያ በማንደሪን ቻይንኛ፣ ከፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፖርቹጋልኛ፣ አረብኛ እና ፖላንድኛ ጋር ይነበባል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለቻይና ሕዝብ ያላቸው እንክብካቤ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማንዳሪንን ለማካተት መወሰናቸው ብዙውን ጊዜ ለቻይናውያን የገለጹትን ትኩረት እና እንክብካቤ ምልክት ያሳያል።

እ.ኤ.አ. በመስከረም 2018 ዓ.ም ባስተላለፉት መልእክት ቻይናን “በታላቅ ዕድሎች የበለፀገች ምድር” እና “የቻይና ህዝብ በችግር እና በልዩነት ውህደት የጠራ በዋጋ ሊተመን የማይችል የባህል እና የጥበብ ቅርስ መሃንዲስ እና ጠባቂዎች” በማለት ገልጿል። ከጥንት ጀምሮ የክርስትናን መልእክት የደረሳቸው በአጋጣሚ አይደለም።

ባለፈው ዓመት እ.አ.አ በመስከረም 3/2023 ዓ.ም ወደ መንጎሊያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት  በኡላንባታር ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለቻይናውያን ክቡር ሕዝብ ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርበዋል” በማለት የቻይና ካቶሊኮች “ጥሩ ክርስቲያኖች እና ጥሩ ዜጎች እንዲሆኑ” አሳስበዋል።

በተለያዩ ጊዜያት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቻይናን ለመጎብኘት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል. እ.ኤ.አ. በመስከረም 13/ 2024 ዓ.ም ከሲንጋፖር ወደ ሮም ሲመለሱ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቻይናን ሀገር “ለቤተ ክርስቲያን የተስፋ ቃል እና ተስፋ” በማለት ጠቅሰዋል።

ታሪካዊ ማስታወሻዎች

ዛሬ የቫቲካን ዜና ድረ-ገጽ በቻይንኛ ባህላዊ እና ቀላል መረጃ ያቀርባል እና የቫቲካን ሬዲዮ የቻይና ቋንቋ ፕሮግራም እ.አ.አ ከ1950 ዓ.ም. ጀምሮ ስርጭት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም ቻይንኛ በቅድስት መንበር ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ቫቲካን.ቫ ላይ ከሚገኙት ቋንቋዎች አንዱ ሆነ። በተጨማሪም የቫቲካን ፊደስ የዜና ወኪል ጋዜጣ በቀላል ቻይንኛ እ.አ.አ ከ1998 ጀምሮ መታተትም ጀምሯል።

28 Nov 2024, 12:11