የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ጳጳሳት ጉባኤዎች ህብረት ጉባኤ መካሄዱ ተገለጸ!
የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ጳጳሳት ጉባኤዎች ህብረት (SECAM) 20ኛው ምልአተ ጉባኤውን በሩዋንዳ ኪጋሊ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በማካሄድ ላይ ይገኛል። ለሶስት ቀናት የተካሄደው ይህ ጉባኤ እሑድ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁ ተገልጿል።
የሴካም ጠቅላይ ጸሃፊ ክቡር አባ ራፋኤል ሲምቦን በመክፈቻ ንግግራቸው ስብሰባው ታሪካዊ መሆኑን ገልፀው ከ200 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል ብለዋል። 20ኛው የሴካም ጉባኤ “ኢየሱስ ክርስቶስ የተስፋ፣ የእርቅ እና የሰላም ምንጭ” በሚል መሪ ቃል መካሄዱ የተገለጸ ሲሆን በጉባኤው በሁሉም የአገልግሎት ዘርፎች ያለፉትን ሶስት ዓመታት (እ.ኤ.አ ሐምሌ 2022 - ሐምሌ 2025) አጠቃላይ አፈጻጸም እና እንቅስቃሴን የሚያጠቃልል አንድ ወጥ የሆነ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ጠቅላይ ጸኃፊው አባ ሲምቦን ገልጸዋል።
በጉባኤው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በመወከል ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት ጳጳስ እና ክቡር አባ ከተማ አስፋው የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ ተገኝተዋል።
ምንጭ፡ የኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ
04 Aug 2025, 08:54