MAP

የኒቂያ ጉባኤ 1,700ኛ ዓመት መታሰቢያ የኒቂያ ጉባኤ 1,700ኛ ዓመት መታሰቢያ 

“የኒቂያው ጉባኤ እምነትን በሚገባ ለመረዳት የሚያግዝ ብርሃን ነው” መባሉ ተገለጸ

ዓለም አቀፉ የሥነ መለኮት ኮሚሽን፥ የኒቂያ ጉባኤ 1,700ኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልከት፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እና አዳኝ” በሚል ርዕሥ ያወጣውን ሠነድ የሚያጠናል ጉባኤ በሮም ተካሂዷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“ኒቂያ የሚለው ቃል መሠረታዊ ትርጉሙ የክርስቲያኖችን አንድነት የሚገልጽ እና ከሁሉም የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ብጹዓን ጳጳሳት የሚሳተፉበት ነው” ሲሉ ብጹዕ ካርዲናል ቪልቶር ማኑኤል ፌርናንደዝ በጳጳሳዊ ምክር ቤት የእምነት አስተምህሮ ጽሕፈት ቤት ርዕሠ መስተዳድር እና የዓለም አቀፍ ሥነ-መለኮት ጥናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት አስታወቁ።

የጳጳሳዊ ምክር ቤቱ አስተባባሪ ብጹዕ ካርዲናል ቪልቶር ማኑኤል ፌርናንደዝ ይህን የተናገሩት፥ የኒቂያ ጉባኤ 1,700ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እና አዳኝ” በሚል ርዕሥ በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ ነው።

ጉባኤው የተዘጋጀው ሮም በሚገኝ ‘ኡርባኒያን’ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ግንቦት 12/2017 ዓ. ም. ሲሆን፥ ይህ ዕለት ከ1700 ዓመታት በፊት የኒቂያው ጉባኤ የተከፈተበት ዕለት እንደሆነ ይታወሳል።

“ኒቂያ የተመረጠበት ጂኦግራፊያዊ ምክንያት አለው” ያሉት ካርዲናል ፈርናንዴዝ፥ ለመድረ ቀላል፣ በጊዜው ኒቂያ ለውስጣዊ አንድነት የምትጋብዝ በመሆኗ እና በዚህም ደስታ እና ብርታት የሚገኝበት ነው” በማለት አስረድተዋል።

ዓለም አቀፉ የሥነ-መለኮት ኮሚሽን፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እና አዳኝ” በሚል ርዕሥ ያወጣው ሠነድ የበርካታ ዓመታት ሥራ ውጤት ሲሆን፥ የኒቂያ ጉባኤ መታሰቢያ ክብረ በዓል ለማክበር ብቻ ሳይሆን ምክር ቤቱ የተወለደበትን እና እስከ ዛሬ ድረስ ጠብቆ ያቆየውን እና የሚያቀርበውን የሐዋርያት ጸሎተ ሃይማኖት መግለጫን ለማጉላት እንደ ሆነ ታውቋል።

ጉባኤውን ከተካፈሉት ዓለም አቀፍ የሥነ-መለኮት ሊቃውንት እና መምራን መካከል፥ የዓለም አቀፍ ሥነ-መለኮት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሞንሲኞር ፒዬሮ ኮዳን ጨምሮ ከአውሮፓ እና ከላቲን አሜሪካ የተወጣጡ ታዋቂ የሥነ-መለኮት ሊቃውንት እና መምህራን ይገኙበታል።

በጳጳሳዊ ምክር ቤት የእምነት አስተምህሮ ጽሕፈት ቤት ርዕሠ መስተዳድር እና የዓለም አቀፍ ሥነ-መለኮት ጥናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት ብጹዕ ካርዲናል ቪልቶር ማኑኤል ፌርናንደዝ፥ ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ሠነዱ የሰጡትን አስተያየት ጠቅለል አድርገው ሲገልጹ፥ 1700ኛ ዓመት መታሰቢያን ለማክበር ወደ ኒቂያ ለመጓዝ ያነሳሳው የመጀመሪያው ምክንያት የኒቂያው ጉባኤ ጠንካራ የክርስቲያኖች የአንድነት ጊዜን የሚያመላክት በመሆኑ፣ በልዩ ልዩ የክርስትና እምነት ተቋማት መካከል ያለውን የአንድነት ምልክት የሚገልጽ የሐዋርያት ጸሎተ ሃይማኖት የጋራ ቅርስ የሚገኝበት መሆኑን አስታውሰዋል።

ካርዲናል ፈርናንዴዝ አክለውም፥ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛም ከዚህ የአንድነት ምልክት ጋር በጥብቅ የተቆራኙ መሆናቸውን እናውቃለን” ሲሉ ተናግረው፥ ከኒቂያው የመጀመሪያው ጉባኤ መታሰቢያ በዓል በተጨማሪ፥ ቤተ ክርስቲያን ለአንድነት ያላትን ቁርጠኝነት በማስመልከት “Ut unum sint” ወይም “አንድ ይሆኑ ዘንድ” በሚል ርዕሥ የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ ሠነድ 30ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል እየተከበረ መሆኑን አስታውሰዋል።

ይህን በተመለከተ ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ “ምንም እንኳን ከሁሉም ክርስቲያኖች ጋር አንድ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን እንመሥርት ማለት ባንችልም፥ ለአክብሮታቸው ሲባል በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ማኅበር ራሳችንን እንደገና ማግኘት እንችላለን” ማለታቸውን ካርዲናሉ አስታውሰዋል።

በራስ ግንዛቤ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተመሠረተች እና በውስጧም የመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን ናት የሚል እምነት አለ። ነገር ግን ይህ እምነት፥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ እውነተኛ ሰው እና እንደ የእግዚአብሔር ልጅ ከሚቀበሉት እና ከሚወዱት ሁሉ ጋር የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ማኅበረሰብ የሚለውን አመለካከት የሚጻረር አይደለም።

የዓለም አቀፍ ሥነ-መለኮት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሞንሲኞር ኮዳ በንግግራቸው፥ “የኒቂያ ጉባኤን ውስብስብ በሆነ አውድ ውስጥ፣ አለመግባባቶች እና ልዩነቶች ዓለምን በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተኑ ባሉበት ወቅት እና ብዙውን ጊዜ ወደማይመለስ ጎዳና የሚሄድ በሚመስል ሁኔታ ማስታወስ ለቤተ ክርስቲያን ፀጋ እና ጥሪ ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

“በዓለም አቀፉ የሥነ-መለኮት ኮሚሽን የተዘጋጀው ሠነድ በዚህ አቅጣጫ ትክክለኛ አስተዋፅዖን ያበረክታል” ያሉት ዋና ጸሐፊው፥ “ከልዩ ብቃቱ በመነሳት እና በኒቂያ-ቆስጠንጢኒያ ምልክት ላይ ያተኮሩ የማይታለፉ ሃብቶችን በማጉላት፣ የሰው ልጅ ዛሬ እያጋጠመው ካለው ነገር ጋር በተያያዘ ከብዙ አቅጣጫዎች ለብዙ ሥነ-መለኮታዊ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ ትክክለኛ አቅጣጫ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

በቅድስት መንበር የባሕል እና የትምህርት ጉዳዮች ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ባለፈው ታህሳስ 9፥ “ስለ ነገረ መለኮት የወደፊት ዕጣ ፈንታ” በሚል ርዕሥ ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ “ሥነ መለኮት እንደገና ለማሰብ ያግዛል” በማለት ለጉባኤው ተካፋዮች የገለጹትን ጠቅለል አድርጎ ማየት ይቻላል” ብለዋል።

በኡርባኒያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት ፕሮፌሰር ቪንቸንሶ ቦኖሞ ባቀረቡት አጭር የሰላምታ ንግግር የተጀመረው የማለዳው ጉባኤ በጥልቅ ጥናታዊ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የተወያየ፣ በኒቂያው ጉባኤ መሠረት የኒቆሜዲያው ዩሲቢየስ ለአሪዮስ በላካቸው የሲኖዶሳዊነት ጥያቄ መልዕክቶች ላይ ጥልቅ ጥናት የተካሄዱባቸው ልዩ ልዩ ጽሑፎች እና የኒቂያው ጉባኤ በመጀመሪያው ሥነ-መለኮታዊ ጥናት፥ “የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት መገለጥ” የሚሉት በጉባኤው ላይ ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሕፎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

ዓለም አቀፉ የሥነ መለኮት ኮሚሽን በቅርቡ ሠነዱን በድጋሚ ለመመልከት አጋጣሚን ያገኘ ሲሆን፥ በጥናቱ ወቅት የቀረበው ሠነድ ቀላል ሥነ-መለኮታዊ ጽሑፍ የያዘ ሳይሆን ነገር ግን በክርስቲያን ማኅበረሰብ ሕይወት ውስጥ የእምነትን ጥልቀት እና ምሥክርነት ማዋሄድ የሚችል ጠቃሚ እና ወቅታዊ ሆኖ መቅረቡ ተመልክቷል።

 

23 May 2025, 13:54