ሰው ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ምላሽ “አምናለሁ" የሚለው ነው
ሰው ራሱን ለሚገልጥለት ለእግዚአብሔር እንዴት ምላሽ ይሰጣል?
ለእግዚአብሔር ምላሽ የምንሰጠው በመለኮታዊ ጸጋ በመታገዝና በእምነት በመታዘዝ ማለትም ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠትና ራሱ እውነት በሆነው በእርሱ የተረጋገጠውን እውነት በመቀበል ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእምነት የመታዘዝ ዋና ምስክሮች እነማን ናቸው?
ለዚህ በጣም ብዙ ምስክሮች አሉ፤ ከእነዚህም አንዱ አብርሃም ሲሆን፣ እርሱም በተፈተነ ጊዜ “በእግዚአብሔር አመነ” (ሮሜ.4፡3) ለእርሱም ጥሪ ዘወትር የታዘዘ ሆነ፡፡ ስለዚህም “ለሚያምኑት ሁሉ አባት” ተባለ (ሮሜ. 4፡11-18) ሌላዋ ሕይወትዋን በሙሉ በእምነት የመታዘዝ ፍጹም ምሳሌ የሆነችውና “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” (ሉቃ 1፡38) ያለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡
በተጨባጭ ለአንድ ሰው በእግዚአብሔር ማመን ማለት ምን ትርጉም አለው?
በእግዚአብሔር ማመን ማለት ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር መጣበቅ፣ ራስን ለእርሱ አሳልፎ መስጠትና
እውነት የሆነው እግዚአበሔር የገለጣቸውን እውነቶች በሙሉ መቀበል ማለት ነው፡፡ ሦስት አካል በሆነው በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ማመን ማለት ነው፡፡
የእምነት ባህርያት ምንድን ናቸው?
እምነት ለደኀንነት አስፈላጊ የሆነ የላቀ ጸጋ ነው፡፡ በትሕትና የሚጠይቅ ሁሉ የሚያገኘው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ የእምነት ሥራ የሰው ሥራ ነው፤ ማለትም በፈቃዱ የተነሣሣና በእግዚአብሔር የተቀሰቀሰ፣ መለኮታዊ እውነትን በደስታ የሚቀበል ሰው የአእምሮ ሥራ ነው፡፡ እምነት በእግዚአብሔር ቅል ላይ የተመሠረተ ስለሆነ እርግጠኛ ነው፡፡
የሚሠራውም “በፍቅር አማካይነት” (ገላ.5፡6) ነው፡፡ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል በመስማትና በጸሎት አማካይነት ያለማቋረጥ ያድጋል፡፡ አሁንም ቢሆን የሰማያዊ ደስታ ቅድመ ልምድ ነው፡፡
በእምነትና በሳይንስ መካከል ቅራኔ የሌለው ለምንድነው?
እምነት ከአእምሮ በላይ ቢሆንም በእምነትና በሳይንስ መካከል ቅራኔ ሊኖር አይችልም፣ ምክንያቱም የሁለቱም ምንጭ እግዚአብሔር ነውና፡፡ የአእምሮና የእምነት ብርሃን የሚሰጠን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ “ለማወቅ አምናለሁ፤ በተሻለ ሁኔታ ለማመንም አውቅለሁ” (ቅዱስ አጎስጢኖስ)።
እናNJለን
እምነት ግላዊና ቤተክርስቲያናዊ ሥራ የሆነው ለምንድነው?
እምነት ሰው ራሱን ለሚገልጠው ለእግዚአብሔር በፈቃደኝነት የሚሰጠው ምላሽ እስከሆነ ድረስ ግላዊ ሥራ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር እምነት “እናNJለን” በሚለው ቃል የሚገለጸው የቤተክርስቲያንም ሥራ ነው፡፡ በመሠረቱ የምታምነው ቤተክርስቲያን ናት፣ በመሆኑም በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የእያንዳንዱን ክርስቲያን እምነት ታስቀድማለች፣ ታስገኛለች ትመግባለች፡፡ ከዚህም የተነሣ ቤተክርስቲያን እናትና አስተማሪ ናት፡፡ “ቤተክርስቲያንን እንደ እናት ያልተቀበለ ሰው እግዚአብሔርን እንደ አባት ሊቀበል አይችልም" (ቅዱስ ቆጵሪያኖስ)
የእምነት ቀመሮች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድነው?
የእምነት ቀመሮች አስፈላጊ የሆኑበት ምክንያት አንድ ሰው የእመት እውነቶችን በጋራ ቋንቋ ከሌሎች ጋር በህብረት ለመግለጽ፣ ለመቅሰም፣ ለማክበርና ለመካፈል ስለሚያስችሉት ነው፡፡
የቤተክርስቲያን እምነት አንድ እምነት ብቻ የሆነው እንዴት ነው?
ቤተክርስቲያን የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና ሥርዓቶች ያሉአቸው ሰዎች ስብስብ ብትሆንም እንኳ በአንድ ድምጽ የምትገልጸው ከአንድ ጌታ የተቀበለችውንና ከአንድ ሐዋርያዊ ትውፊት የላለፈላትን አንድ እምነት ነው፡፡ የምታምነው በአንድ አምላክ፣ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን፣ የምታመለክተው የደኀነት መንገድም አንድ ነው፡፡ ስለዚህ፣ በትውፊት ወይም በጽሑፍ በተላለፈልን እና በመለኮት የተገለጠ ለመሆኑ በቤተክርስቲያን በተነገረን በቃለ እግዚአብሐር ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ በአንድ ልብና በአነድ ነፍስ እናNJለን፡፡