ሰው ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ምላሽ “አምናለሁ”
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእምነት የመታዘዝ ዋና ምስክሮች እነማን ናቸው?
ለዚህ በጣም ብዙ ምስክሮች አሉ፤ ከእነዚህም አንዱ አብርሃም ሲሆን፣ እርሱም በተፈተነ ጊዜ “በእግዚአብሔር አመነ” (ሮሜ.4፡3) ለእርሱም ጥሪ ዘወትር የታዘዘ ሆነ፡፡ ስለዚህም “ለሚያምኑት ሁሉ አባት” ተባለ (ሮሜ. 4፡11-18) ሌላዋ ሕይወትዋን በሙሉ በእምነት የመታዘዝ ፍጹም ምሳሌ የሆነችውና “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” (ሉቃ 1፡38) ያለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡
በተጨባጭ ለአንድ ሰው በእግዚአብሔር ማመን ማለት ምን ትርጉም አለው?
በእግዚአብሔር ማመን ማለት ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር መጣበቅ፣ ራስን ለእርሱ አሳልፎ መስጠትና
እውነት የሆነው እግዚአበሔር የገለጣቸውን እውነቶች በሙሉ መቀበል ማለት ነው፡፡ ሦስት አካል በሆነው በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ማመን ማለት ነው፡፡
የእምነት ባህርያት ምንድን ናቸው?
እምነት ለደኀንነት አስፈላጊ የሆነ የላቀ ጸጋ ነው፡፡ በትሕትና የሚጠይቅ ሁሉ የሚያገኘው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ የእምነት ሥራ የሰው ሥራ ነው፤ ማለትም በፈቃዱ የተነሣሣና በእግዚአብሔር የተቀሰቀሰ፣ መለኮታዊ እውነትን በደስታ የሚቀበል ሰው የአእምሮ ሥራ ነው፡፡ እምነት በእግዚአብሔር ቅል ላይ የተመሠረተ ስለሆነ እርግጠኛ ነው፡፡
የሚሠራውም “በፍቅር አማካይነት” (ገላ.5፡6) ነው፡፡ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል በመስማትና በጸሎት አማካይነት ያለማቋረጥ ያድጋል፡፡ አሁንም ቢሆን የሰማያዊ ደስታ ቅድመ ልምድ ነው፡፡
በእምነትና በሳይንስ መካከል ቅራኔ የሌለው ለምንድነው?
እምነት ከአእምሮ በላይ ቢሆንም በእምነትና በሳይንስ መካከል ቅራኔ ሊኖር አይችልም፣ ምክንያቱም የሁለቱም ምንጭ እግዚአብሔር ነውና፡፡ የአእምሮና የእምነት ብርሃን የሚሰጠን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ “ለማወቅ አምናለሁ፤ በተሻለ ሁኔታ ለማመንም አውቅለሁ” (ቅዱስ አጎስጢኖስ)።
እናNJለን
እምነት ግላዊና ቤተክርስቲያናዊ ሥራ የሆነው ለምንድነው? እምነት ሰው ራሱን ለሚገልጠው ለእግዚአብሔር በፈቃደኝነት የሚሰጠው ምላሽ እስከሆነ ድረስ ግላዊ ሥራ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር እምነት “እናNJለን” በሚለው ቃል የሚገለጸው የቤተክርስቲያንም ሥራ ነው፡፡ በመሠረቱ የምታምነው ቤተክርስቲያን ናት፣ በመሆኑም በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የእያንዳንዱን ክርስቲያን እምነት ታስቀድማለች፣ ታስገኛለች ትመግባለች፡፡ ከዚህም የተነሣ ቤተክርስቲያን እናትና አስተማሪ ናት፡፡ “ቤተክርስቲያንን እንደ እናት ያልተቀበለ ሰው እግዚአብሔርን እንደ አባት ሊቀበል አይችልም" (ቅዱስ ቆጵሪያኖስ)
የእምነት ቀመሮች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድነው?
የእምነት ቀመሮች አስፈላጊ የሆኑበት ምክንያት አንድ ሰው የእመት እውነቶችን በጋራ ቋንቋ ከሌሎች ጋር በህብረት ለመግለጽ፣ ለመቅሰም፣ ለማክበርና ለመካፈል ስለሚያስችሉት ነው፡፡
የቤተክርስቲያን እምነት አንድ እምነት ብቻ የሆነው እንዴት ነው?
ቤተክርስቲያን የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና ሥርዓቶች ያሉአቸው ሰዎች ስብስብ ብትሆንም እንኳ በአንድ ድምጽ የምትገልጸው ከአንድ ጌታ የተቀበለችውንና ከአንድ ሐዋርያዊ ትውፊት የላለፈላትን አንድ እምነት ነው፡፡ የምታምነው በአንድ አምላክ፣ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ስሆን፣ የምታመለክተው የደኀነት መንገድም አንድ ነው፡፡ ስለዚህ፣ በትውፊት ወይም በጽሑፍ በተላለፈልን እና በመለኮት የተገለጠ ለመሆኑ በቤተክርስቲያን በተነገረን በቃለ እግዚአብሐር ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ በአንድ ልብና በአነድ ነፍስ እናNJለን፡፡
ክርስቲያናዊ እምነትን መግለጽ
በቅዱስ ቀለሜንጦስ የሮማ ቤተክርስትያን የሚገኘው ይህ ጥንታዊ በህብር የተሠራ ሥዕል የክርስትና እምነት ማዕከላዊ ምስጢር የሆነውን የመስቀልን አሸናፊነት ያመለክታል፡፡
አበቦቻቸውና ፍሬዎቻቸው በሁሉም አቅጣጫ የተንዠረገጉና በርካታ ትንንሽ ክብ ቅርጾችን የሠሩ የዛፍ ተክል ቅርንጨፎች በቀለም አግጠውና ደምቀው ይታያሉ ይህ ተክል ሕይወት የሚያገኘው የሰውን ልጅና ፍጥረተ ዓለምን እንደገና ለመፍጠር መሥዋዕት ከሆነው ከኢየሱስ መስቀል ነው፡፡ ኢየሱስ በሕማማቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው የውን ዳግመኛ ልደት የሚያረግጥና ሰውን ከእግዚአበሐር ጋር የሚያስታርቅ አዲሱ አዳም ነው፡፡
በሚሠቃየው ክርስቶስ ዙሪያ ኡሥራ ሁለቱን ሐዋርያት የሚወክሉ አሥራ ሁለት ነጫጭ ርግቦች አሉ፡፡ በመስቀሉ ግርጌ ማርያምና ተወዳጁ ደቀ መዝሙር ዮሐንስ ይገኛሉ፡፡
“ኢየሱስ እናቱንና ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆመው ባየ ጊዜ እናቱን “እናቴ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ” አላት፡፡ ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እናትህ ይህችውልሽ” አለው፡፡ ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት” (ዮሐ.19፡26-27)፡፡
ከመስቀሉ በላይ በኩል የአብ እጅ ተዘርግቶ በፋሲካ ምስጢር በሞት ላይ ድልን ለተቀዳጀው ልጁ የክብር አክሊል ሲሰጥ ይታያል፡፡ በተክሉ ሥር ከክፉ እባብ ጋር የሚታገል ትንሽ አጋዘን አለ፡፡
የደኀንነት ዛፍን ከሚወክለው ከዚህ ተክል ውስጥ ድኩላ ከሕይወት ውሃ ምንጭ ጠጥቶ እንደሚረካ ሁሉ ምእመናንም ጠጥተው የሚረኩባቸው የአራቱ ወንጌሎች ምሳሌ ለሆኑ አራት ቀጭን ጅረቶች ሕየወት ሰጭ ውሃ ምንጭ ይፈልቃል፡፡ እዚህ ላይ ቤተክርስቲያን እውነተኛ የሕይወት ዛፍ ከሆነው ክርስቶስ ሕይወትን ያገኘች ሰማያዊት ገነት መስላ ትታያለች፡፡
NJͭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ካጸደቁት፣ በአጭሩ ከተጻፈው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ከዋናው ከላቲን ቅጂ ከተተረጎመው መጽሐፍ ከአንቀጽ 142-284 ላይ የተወሰደ።