MAP

የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ሊቀ ጳጳስ ቲሞቲ ብሮሊዮ የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ሊቀ ጳጳስ ቲሞቲ ብሮሊዮ   (Credits: Senior Airman Kristin High)

የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባኤ አንዳንድ የትራምፕ ትዕዛዞች 'በጣም አሳሳቢ ናቸው' ማለታቸው ተገለጸ!

የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በስደተኞች፣ በሞት ቅጣት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ የወሰዷቸው አዳዲስ እርምጃዎች "በጣም አሳሳቢ ናቸው" ሲሉ የገለጹ ሲሆን በፆታ ጉዳዮች ላይ ያደረጉትን ለውጦች እና ተነሳሽነት አድንቀዋል። የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባሄ የስደተኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ በተለየ መግለጫ “ብሔራዊ የራስ ጥቅም ከሥነ ምግባር ሕግ ጋር የሚቃረኑ ውጤቶችን የሚያስከትሉ ፖሊሲዎችን አያረጋግጥም” ብለዋል ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ሊቀ ጳጳስ ቲሞቲ ብሮሊዮ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው በመጀመሪያዎቹ ቀናት የተፈረሙትን ተፈጻሚ የሚሆኑ ትዕዛዞችን አስመልክቶ ምላሽ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይ ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ ተፈጻሚ በሚሆኑ ትዕዛዞች ውስጥ የተካተቱት አንዳንድ ድንጋጌዎች "በጣም አሳሳቢ" እና "አሉታዊ መዘዞች" እንደሚኖራቸው፣ ሌሎች ደግሞ "በአዎንታዊ መልኩ ሊታዩ ይችላሉ" ብለዋል።

በሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ ለተሰነዘረው ትችት የተለዩት ቦታዎች "በስደተኞች እና በጥገኝነት ተያቂዎች አያያዝ፣ ለውጪ አገራት የሚሰጠው እርዳታ፣ በሞት ቅጣት መስፋፋት እና አካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮሩ" ነበሩ።

በሌላ በኩል “ስለ እያንዳንዱ ሰው ወንድ ወይም ሴት ሆኖ መታወቅ እንደሚኖርበት የምያመልክተውን እውነታ በመገንዘብ” እርምጃዎቹን አወድሷል።

የአሜሪካን 'ብዙ ስጦታዎች' ማጋራት

ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ አክለውም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን "ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር አትተባበርም" እና "ኋይት ሀውስን ማንም ቢይዝ ወይም በካፒቶል ሂል ላይ አብላጫውን ቢይዝ የቤተክርስቲያኗ ትምህርቶች አልተቀየሩም" ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ አፅንዖት ሰጥው የተናገሩ ሲሆን “የአገራችን አመራር የጥቂቶችን ሰብአዊ ክብር ብቻ ሳይሆን የሁላችንንም ክብር የማይጥሱ ድርጊቶችን እንደገና እንደሚያጤነው “የእኛ ተስፋ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳሱ “በብዙ ስጦታዎች የተባረከ ሀገር” እንደመሆናችን መጠን፣ የአሜሪካ ድርጊት “እጅግ ተጋላጭ ለሆኑ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን፣ ያልተወለዱትን፣ ድሆችን ጨምሮ እውነተኛ እንክብካቤን እንዲያሳይ እንደሚጸልዩ በመግለጽ ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል። ፣ አረጋውያንና አቅመ ደካሞች፣ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች መንከባከብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ስደተኞችን የተመለከተ ትእዛዝ ‘በእግዚአብሔር ላይ ጥቃት እንደ መሰንዘር’ ይቆጠራል

በተለየ መግለጫ፣ የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባሄ የስደተኞች አገልግሎት ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አቡነ ማርክ ጄ ሲትዝ፣ ተፈጻም ስለሚሆኑት ትዕዛዞችም ንግግር አድርገዋል።

"ብሔራዊ የራስ ጥቅም ከሥነ ምግባር ህግ ጋር የሚቃረኑ ውጤቶችን የሚያመጣውን ፖሊሲ አያረጋግጥም" ሲሉ ጳጳስ ሴይትስ ተናግረዋል። “ማንኛውንም ቡድን ለማንቋሸሽና ለማኮሰስ የሚጠቅሙ አባባሎችን መጠቀም፣ለምሳሌ ሁሉንም ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ‘ወንጀለኛ’ ወይም ‘ወራሪዎች’ በማለት በህግ ጥበቃ እንዳይደረግላቸው መግለጽ እያንዳንዳችንን በራሱ የፈጠረን የአምላክን ምስል ማኮሰስ ነው" ብለዋል።

ኤጲስ ቆጶሱ በተጨማሪም በርካታ ተፈጻሚ የሚሆኑ ትዕዛዞች "በተለይ በፌዴራል ህግ ውስጥ የተካተቱትን የሰብአዊ ጥበቃዎችን ለማስቀረት የታቀዱ ናቸው" በማለት አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በከፍተኛ ፍርድ ቤት የረዥም ጊዜ አተረጓጎም የሚጻረር የዜግነት መብት ህግን ለመቀየር የታቀደው አደገኛ ምሳሌ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

አቡነ ሴይትዝ መግለጫቸውን ያበቁት ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኮንግረስ አባላት ጋር “በጋራ ጥቅም ላይ የሚውል ትርጉም ያለው፣ የሁለትዮሽ የስደተኞች ጉዳይ ማሻሻያ ለማድረግ” በቅን ልቦና እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

“እኔና ወንድሜ ጳጳሳት ይህንን በምንችለው መንገድ እንደግፋለን” ሲሉ አቡነ ሲትዝ የተናገሩ ሲሆን “በሕይወት ወንጌል መሠረት ከስደተኛ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር መሆናችንን እንቀጥላለን” ሲሉ ጽፏል።

 

24 Jan 2025, 16:44