MAP

የአሜሪካ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት የጸሎት እና የውይይት ጊዜያትን ለማሳለፍ በባልቲሞር ተሰበሰቡ የአሜሪካ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት የጸሎት እና የውይይት ጊዜያትን ለማሳለፍ በባልቲሞር ተሰበሰቡ 

የአሜሪካ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት ስለ ስደት እና በጀት ለመወያየት ተሰበሰቡ

የአሜሪካ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት በአውሮፓዊያኑ 2025 ለሚያደርጉት ምልአተ ጉባኤ የተዘጋጀው የአጀንዳ ሰነድ ስለ ፍልሰት፣ ስለ የአሜሪካ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት ጉባኤ በጀት፣ ስለ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ እንዲሁም ስለ ሁለት ሰዎች የቅድስና ሂደቶች በዝርዝር እንዳካተተ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ሰኞ ዕለት ከመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተውጣጡ ብጹአን ጳጳሳት በባልቲሞር፣ ሜሪላንድ ባካሄዱት ዓመታዊ ምልአተ ጉባኤ ወቅት የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያንን እየተፈታተኑ ስለሚገኙት የተለያዩ ተግዳሮቶች እንደተወያዩ እና ጸሎት እንዳደረጉ ተገልጿል።

የአሜሪካ ብጹአን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ብጹእ አቡነ ቲሞቲ ብሮሊዮ እና በዩናይትድ ስቴትስ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተወካይ ብፁዕ ካርዲናል ክሪስቶፍ ፒየር ምልአተ ጉባኤውን በንግግር ከከፈቱት ውስጥ ይገኙበታል።

ለአራት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ በስደት ጉዳዮች፣ እንደ ጎረጎሳዊያኑ ከ 2021 እስከ 2024 ሲካሄድ ስለነበረው የጳጳሳት ሲኖዶስ፣ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ እንዲሁም ስለ የአሜሪካ ብጹአን ጳጳሳት ጉባኤ የ 2025 በጀትን ያካተቱ ዝርዝር ጉዳዮች ስለያዘው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሏል ።

በጉባዔው ወቅት አዲስ የጉባኤው ገንዘብ ያዥ እና አምስት የጉባኤው የኮሚቴ አባላትን ለመምረጥ ድምጽ እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን፥ በ2025 ከሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ መገባደጃ ላይ ቢሮውን ለሦስት ዓመታት ከመያዛቸው በፊት ሊቀመንበሩ በተመረጡበት የሊቀመንበርነት ቦታ የአንድ ዓመት ጊዜ እንዳላቸው ተነግሯል።

የጉባዔው ህዝባዊ የውይይት ጊዜያት ጉባኤው ሐሙስ ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ከመዘጋቱ በፊት ህዳር 3 እና 4 በቀጥታ ስርጭት እንደሚተላለፉ ተገልጿል።
 

13 Nov 2024, 14:01