MAP

በሜዲትራኒያን ባህር ስደተኞችን የማዳን ሥራ - የማህደር ምስል በሜዲትራኒያን ባህር ስደተኞችን የማዳን ሥራ - የማህደር ምስል 

በስደተኞች ጀልባ ላይ በደረሰ ሌላ አሳዛኝ የመስመጥ አደጋ አንዲት ሴት መሞቷ እና ልጇ እስካሁን እንዳልተገኘ ተነገረ

በደቡባዊ የጣሊያን ክፍል በሚገኘው የሜድተራኒያን ባህር ደሴቶች ውስጥ አንዱ በሆነው ላምፔዱሳ ደሴት በደረሰው የስደተኞች ጀልባ የመስመጥ አደጋ የአንዲት እናት ህይወት መቅጠፉን እና ህፃን ልጇ ደግሞ እስከአሁን ሊገኝ እንዳልቻለ የተገለጸ ሲሆን፥ ይህ አደጋ ለስደተኞች ደህንነት እንዲሁም ለቤተሰብ እና ለልጆቻቸው ጉልህ የሆነ ጥበቃ አስፈላጊነትን ትኩረት መሳቡ ተነግሯል።

አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በላምፔዱሳ የባህር ዳርቻ ላይ የደረሰው የጀልባ አደጋ ስደተኞች እየተጋፈጡት ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ያሳየ ነው የተባለ ሲሆን፥ ሌሊት ላይ በደረሰው በዚህ አደጋ የሰው ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ እንዳልተገኙ እና የተቀሩት ሰማንያ ሰባት ተሳፋሪዎች የቱኒዚያ የአሣ ማጥመጃ ጀልባ እና የጣሊያን የባህር ዳርቻ ጥበቃ መርከቦች በሰላም ወደ ባህር ዳርቻ እስኪወስዷቸው ድረስ በተስፋ ጀልባዋ ላይ ተንጠልጥለው እንደነበር ተገልጿል።

የዸም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ ፍላቪዮ ዲ ጂያኮሞ “ተንሳፋፊ የሬሳ ሣጥን” ብለው በጠሩት ከብረት በተሠራው ደካማ ጀልባ ላይ የነበሩት ስደተኞች ከቱኒዚያ የተሳፈሩ መሆኑን ገልጸው፥ ጀልባው ባህሩ ላይ በነበረው ከባድ የአየር ንብረት ምክንያት አደጋ እንደደረሰባት እና አደጋው ጥገኝነትን ፈልገው በሚሰደዱ ስደተኞች ላይ በቀላሉ ሊደርሱ የሚችሉ የተፍጥሮ አደጋዎችን ያሳያሉ ብለዋል።

ይህ አደጋ የተከሰተው ከአንድ ሳምንት በፊት ህጻናት እና ነፍሰ ጡር እናቶችን ጨምሮ ሰማኒያ ስደተኞችን አሳፍራ ከሊቢያ የተነሳችው ጀልባ ላይ የደረሰውን አሳዛኝ አደጋ ተከትሎ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ ዲ ጂያኮሞ ይሄንን ጉዞ ስደተኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሳዩበትን ጥንካሬ በመጥቀስ “ድፍረት የተሞላበት” በማለት ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቅድስት መንበር ዕውቅና ከተሰጣቸው የዲፕሎማቲክ አካላት ጋር በነበራቸው ቆይታ ባደረጉት ንግግር “ማንኛውም ሰው በተለይም እጅግ በጣም ደካማ እና ተጋላጭ ለሆኑት ከጨቅላ ህፃናት እስከ አረጋውያን፣ ከሕሙማን እስከ ሥራ አጦች፣ ከዜጎች እስከ ስደተኞች የሁሉም ሰው ሰብአዊ ክብር እንዲከበር የመታገል ሃላፊነት አለበት በማለት አሳስበው፥ ብጹእነታቸው እራሳቸውንም ጭምር “የስደተኞች ተወላጅ” ብለው በመጥራት፣ ለተፈናቃዮች ርህራሄ እና ትብብር እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ከ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ከ 25,000 በላይ ስደተኞች የተሻለ ኑሮን ለማግኘት በሚያደርጉት የስደት ጉዞ መሞታቸውን ወይም መጥፋታቸውን መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን፥ በ 2006 ዓ.ም. ብቻ 1,810 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና በያዝነው ዓመት ደግሞ በግምት 542 አሳዛኝ አደጋዎች መከሰታቸው ተገልጿል።

እነዚህ ቁጥሮች ብቻ የጉዳዩን አሳሳቢነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ አሃዞች እንደሆኑ እና እያንዳንዱ አሃዝ የሰውን ፊት፣ ቤተሰብ እና መጪውን ጊዜ እንደሚወክል ዕለታዊ ማስታወሻ ናቸው ተብሏል።

03 Jul 2025, 13:23